• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለአህመዲን ጀበል ህክምና ስጡት፣ ፍቱትም!

November 16, 2017 03:29 pm by Editor Leave a Comment

  • በግፍ አስሮም ህክምና መንፈግ ለምን?
  • ሀሳብን የደፈረው ጀግና  …!

የወንድም ኡስታዝ አህመዲን ጀበልን በእስር ላይ ህክምና መነፈጉን ከተለያዩ ምንጮች ለማረጋገጥ ችያለሁ። በእስር ላይ ያሉ ወገኖችን በህገ መንግስትና በአለም አቀፍ ህግ የተደነገገ እየተጣሰባቸው ነው። በህግ ስር ባለው ኡስታዝ አህመዲንና በብዙ ታሳሪዎች መንግስት የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸመባቸው ተደጋግሞ ተመልክተናል። ዛሬ አደባባይ በአህመዲን ያየነውም ይህንኑ ነው። በኡስታዝ አህመዲን ሰውነት ላይ የሚታየውን ጉዳትና መጎሳቆል ስመለከት የተሰማኝ ስሜት ደስ አይልም።

አሳሪው መንግስት ደጋግሞ “ኡስታዝ አህመዲንና ጓደኞቹ የታሰሩት በህግ ጥሰት ነው!”  ቢልም የታሰረበት በመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴነቱ ብቻ እንደሆነ አምናሁ። ከታሰሩት በርካታ የመፍትሔ አፈላላጊዎች ኮሚቴ አባላት መካከል  ኡስታዝ አህመዲንን ጨምሮ ጥቂቶች ተለይተው ሲቀሩ ዋና ዋና የተባሉት ተከሳሾች በነጻ ተፈትተዋል። ዛሬ ጎልማሳው ወንድም አህመዲን እንደቀሩት ወንድሞቹ እኩል ከወህኒ እንዲወጣ ባይፈቀድለት እንኳ ህክምና የማግኘት መብቱ ሊከበርለት ይገባል እላለሁ!

በእስር ላይ ሆኖ ህክምና አለማግኘት ቀርቶ ህክምና እያገኙ ኑሮን መግፋት እጅግ የከፋ መከራ ስለመሆኑ ከ4 ዓመት በፊት በወራት የሳውዲ ወህኒ ህይዎቴ አውቀዋለሁ። “ከአረብ ሀገራት በተሻለ መልኩ የሰብአዊ መብት ይዞታ ተከብሯል”  በምትባለው ኢትዮጵያ ሀገራችን መሳሪያ ያላነሳ ታሳሪን ህክምና ነፍጎ ማሰቃየትን የመሰለ የከፋ ግፍ ሲፈጸም ደጋግመን ተመልክተናል። ይህ መራራ እውነት እጅግ በጣም ያሳዝናል! ልብን በሀዘን ይሰብራል! ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በአስቸኳይ ህክምና ይደረግለት ዘንድ የዜጋ ድምጼን አሰማለሁ!

ሀሳብን የደፈረውን ጀግና ፍቱት …!

ወንድም ኡስታዝ አህመዲን ጀበልን ሳስታውስ ብዙ ነገሩ  ትዝ ይለኛል። ኡስታዝ አህመዲን ለቆመበት አላማ ጽኑ ነው። የህዝብ ከበሬታ ያሰጠው አስተምህሮት መሆኑንም ለመረዳት ብዙ ጊዜ አልፈጀብኝም። ኡስታዝ አህመዲን በሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ተመርጦ በወቅቱ ለነበረው ሁከት መፍትሔ አመንጭ ከነበሩት መካከል አንዱ ነበር። ዳሩ ግን ለመፍትሔ የተወከሉት “ወንጀለኛ” ተብለው ዘብጥያ ሲወርዱ አህመዲን ክራሞቱ ወህኒ ሆነ። በእሱና በቀሩት ወንድሞች እስር አዘንን።

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል

ኡስታዝ አህመዲን የሀገሬ ሰው ለማንሳትና በአደባባይ ለመሞገት ይፈራቸው የነበሩ የሙስሊም ጉዳዮችን በስራዎቹ እያነሳ የማይደፈር ሀሳብን የደፈረ በመሆኑ አደንቀዋለሁ። በጋዜጦችና በየአደባባዩ ሀሳብን ሲያቀርብና ሲሞግት፣ ከዚያም የታሪክ ድርሳናትን ፈታትሾ ለንበብ  ሲያቀርብ ተመልክቻለሁ። አህመዲን የማህበረሰቡ ውስጥ ይንሸራሸር የነበረውን ሀሳብ በአደባባይ ማውጣቱና መነጋገሪያ ማድረጉን አደንቃለሁ!

የኡስታዝ አህመዲንን የጻፋቸውን መጻሕፍት ደጋግሜ ካነበብኳቸው ውስጥ ቀዳሚዎቹ ናቸው። “ስለ ሙስሊሙ ጉዳት ያገባኛል” ማለቱንና ሀሳቡን በነጻነት መግለጹን አከብርለታለሁ። በመጽሐፍቱ ያሰናዳቸውን ሀሳቦችና ምልከታዎቻ ጋር ግን ብዙም አልስማማም። በሀሳብ ልዩነት አምናለሁ፣  የሀሳብ ልዩነት አለን ማለት ሰብአዊ መብቱ ሲጣስ ዝም እላለሁ ማለት አይደለም።

ጎልማሳው ኡስታዝ አህመዲን የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል ሆኖ እያለ ሲጀመር መንግስት ሆደ ሰፊ በመሆን መፍትሔ አብሮ እንደመፈለግ ማሰሩ ምን ጠቀመ? በግፍ አስሮም ህክምና መንፈግስ ለምን? ብየ ደጋግሜ ራሴን ጠይቄያለሁ። አጥጋቢ መልስ ግን የለኝም። በህግና ስርአት እስር ላይ ያለን ፍርደኛ ህክምና ነፍጎ ማንገላታትና እንዲህ እንዳየነው ከሰው ተራ ማውጣት ግለሰብን ብቻ ሳይሆን ዜጋን መናቅ ማለት ነው። እናም የታሳሪውን ስቃይ ስሰማ ከተናቁት ዜጎች መካከል መሆኔ ተሰምቶኛል። ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል ህክምና ከማድረግ በላይ በህዝብ ውክል በመውሰዱ ለወህኒ የተዳረገ ወጣት ነውና በአስቸኳይ ትፈቱት ዘንድ የዜጋ ድምጼን አሰማለሁ!

ፍትህ ለኡስታዝ አህመዲንና በግፍ ለሚሰቃዩት ታሳሪዎች!

ወዳጄ ኡስታዝ አህመዲን ሆይ ምህረቱን ይላክልህ! (ፎቶዎቹ ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኙ ናቸው)

እስኪ ቸር ያሰማን

ነቢዩ ሲራክ

ህዳር 7 ቀን 2010 ዓም


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions, Social Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule