• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በህወሃት “የትግራይ ኩራት ተነክቷል” ባዮች አይለዋል

September 30, 2014 08:34 am by Editor Leave a Comment

የሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔያቸውን “ከኋላ” አስከትለው ከፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ያካሄዱት የፊት ለፊት ንግግር ያስደሰታቸውና ያስኮረፋቸው ክፍሎች አሉ። “በህወሃት መንደር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ የመወከል ባለጊዜው ህወሃት ነው። ህወሃት የኢትዮጵያ ምልክትና ተምሳሌት ነው” የሚሉት ወገኖች ቀደም ሲል ሲሰማ የነበረውን “የትግሬ ኩራት ተነክቷል” ስሜት በገሃድ ሲያንጸባርቁ ታይቷል።

አስገድደው ከሚመሩት ህዝብ ይልቅ ለውጪው ዓለም በመስገድና በማጎብደድ ወደር እንደሌላቸው የሚነገርረላቸው አቶ መለስ meles at g20ሰሞኑን አቶ ሃይለማርያም ያገኙትን ዕድል አላገኙም። ከታላቋ አሜሪካ መሪ ጋር በግል የፊት ለፊት ወግ አላደረጉም። በተለያዩ መድረኮች ላይ በጅምላ ተገኝተው ከመጨባበጥና ውስን ቃላቶችን ሲለዋወጡ ከመታየቱ ውጪ ያላገኙትን ይህንን ዕድል አቶ ሃይለማርያም ማግኘታቸው ቅር ያሰኛቸው ክፍሎች “መለስ ከመሬት በታች ሆነው የዲፕሎማሲውን ስራ ሰርተው መድረኩን እንዳመቻቹ አስመስለው በተለያዩ መንገዶች መግለጻቸው የዚሁ የኩራታችን ተነካ ስሜት ነጸብራቅ ነው” የሚሉ ወገኖች አሉ።

ስብሰባው በኋይት ሃውስ እልፍኝ ወይም በተባበሩት መንግስታት ሳሎን ውስጥ አልነበረም የተካሄደው። ዓለምአቀፉ ሒልተን በሚያስተዳድረው የኒውዮርኩ ዋልዶርፍ አስቶሪያ ሆቴል አንድ ክፍል ውስጥ የአሜሪካ “ባንዲራ” እና የኢህአዴግ አርማ እንዲሰቀል ተደርጎ ንግግሩ መደረጉን ያወሱ ክፍሎች፣ ፕሬዚዳንት ኦባማ ምርጫ እየተቃረበ መሆኑንን ጠቁመው “የሲቪል ማኅበረሰቡ እንዴት መንቀሳቀስ እንዳለበት መታየት አለበት” በማለት ያነሱት ሃሳብ ከስብሰባው በላይ ሚዛን አንስቷል። ኢህአዴግ የመያዶች ህግ በሚል በማተም የዘጋውን የሲቪል ማኅበረሰቡን ተሳትፎ አስመልክቶ ኦባማ ማንሳታቸው ውሎ አድሮ የሚመነዘሩ ጉዳዮችን እንደሚያስነሳ አመላክቷል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም በፌስቡካቸው የለጠፉት የዚሁ የሆቴል ክፍል ስብሰባ በርካታ አስተያየት ተሰንዝሮበታል። “ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር አንተ መሆን አለብህ” ከሚሉት የስጋና የደም አስተያየት ጀምሮ የዚሁ የፊት ለፊት ንግግር የቀድሞው “ባለ ራዕይ” መሪ “ራዕይ” ፍሬ አጎምርቶ የመታየቱ ብስራት ተደርጎ ተወስዷል፤ ታምኗል። ክብሩና ታሪኩም ለመለስ መቃብርና አጽም ህይወት ማላበሻ የአበባ ጉንጉን በረከት ሆኖላቸዋል።meles and hailemariam

የመለስ ሞት ዱብዳ የሆነበት ህወሃት፣ ከዱብዳው ማግስት ጀምሮ መርዶውን ሚስጥር ያደረገው የርዕሰ መንበሩ ወንበር ለይስሙላም ቢሆን እንዳይወሰድ አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ እንደሆነ በወቅቱ ብዙ የተባለበት ጉዳይ ነው። የመለስን የጥድፊያ ሞት “የግፍ ዋጋ፣ የአምላክ ቅጣት” በማለት ጮቤ የረገጡ ቢኖሩም፣ በህወሃት መንደር ግን ዜናው መሬት የተደረመሰ ያህል ስሜታቸውን ያራደ፣ ከሞት ጋር እልህ የተጋቡ የሚመስሉ፣ በዚሁ እሳቤ መለስ ቢሞቱም ያሉ ለማስመሰል የተደረገውና እየተደረገ ያለው ግብ ግብ “አምልኮ መለስ” ማስረጃ እንደሆነ ብዙዎች ተችተዋል።

ከዩኒቨርሲቲ የዲንነት በርጩማቸው ጀምሮ የሚያውቋቸው ሃይለማርያምን “የቆረጣ አካሄድን የተካነ” ሲሉ ይገልጹዋቸዋል። የሲዳማን ብሄረሰብ ለማስደሰት ከክልል ፕሬዚዳንትነታቸው ተነስተው አቶ መለስ ኢህአዴግ ቢሮ የተዛወሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም፣ በብሄር ውክልና ማመጣጠን ሰበብ ምክትል ጠ/ሚ ከመባላቸው ሌላ መለስ ቢሮ ለመጠጋት የሳቸው ሚና የለበትም። እንዳው አጋጣሚ ነው በሚል የሚከራከሩ ሃይለማርያም በኦባማ አስተዳደር ጫና ወንበሩን እንዲይዙ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ህወሃቶች ውሳኔው “የትግሬዎችን ኩራት የነካ” መሆኑንን በመግለጻቸው በተደጋጋሚ መመከራቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ዲፕሎማቶች ይገልጻሉ።

ለጎልጉል ቅርብ የሆኑ የአሜሪካ ዲፕሎማት ሰሞኑን እንደጠቆሙት ህወሃቶች “በኩራታችን ተወሰደ” ስሜት ሃይለማርያም ደሳለኝን በቀጣዩ ምርጫ በራሳቸው ሰው ለመተካት እየሰሩ መሆናቸውን አመልክተዋል። በተለያዩ ሚዲያዎች ቴድሮስ አድሃኖም ቀጣዩ ጠ/ሚ/ር ይሆናሉ ስለመባሉ ለተጠየቁት “ቴድሮስ የግራውን መስመር የማያውቁ በመሆናቸው አምባገነን፣ ፈላጭ ቆራጭ መሪ ሊሆኑ አይችሉም፤ መስፈርቱን አያሟሉም በሚል ፈተናውን ሊያልፉ የማይችሉ ተደርገው ስለመወሰዳቸው መረጃው አለኝ” ብለዋል።

“የህወሃት የስለላው ማሽን” የሚባሉትና በፈላጭ ቆራጭነቱ አግባብ ግንባር ቀደም እንደሆኑ የሚነገርላቸው “ዶ/ር” ደብረጽዮን ሌላው እጩ ናቸው። ለመጀመሪያ ጊዜ ጎልጉል ስማቸውን ጠቅሶ ለጠ/ሚኒስትርነት ህወሃት ወደ ግንባር እያቀረባቸው መሆኑንን መግለጹ አይዘነጋም። የመረጃችን ምንጭ የሆኑት እኚሁ ዲፕሎማት፣ “ዶ/ር” ደብረጽዮን አምባገነንና ፈላጭ ቆራጭ በመሆን መስፈርቱን የሚያሟሉ ቢሆኑም ዓለምአቀፍ እውቅና የሌላቸውና ለዚያ የሚበቁ እንደማይሆኑ በራሳቸው በህወሃት ሰዎች መታመኑን ጠቁመዋል።haile fortune

በቀጣዩ ምርጫ ህወሃቶች ዋናውን “የኢትዮጵያ ውክልና” የሚባለውን ወንበር መልሶ የመያዝ እቅድ እንዳላቸው በቂ መረጃ አሜሪካ እንዳላት የጠቆሙት ዲፕሎማት፣ ከህወሃት ቁልፍ ሰዎች መካከል ሃይለማርያም ደሳለኝ ምክንያት ተፈጥሮ በቀጣዩ ምርጫ እንዳይወዳደሩ የማድረግ ዕቅድ ስለመኖሩ መስማታቸውን ጠቁመዋል። “ለጊዜው መረጃው ጥሬ ነው” ሲሉም ዝርዝር ውስጥ ለመግባት እንደማይችሉ አመልክተዋል።

የመለስ ሞት ይፋ በሆነበት ቅጽበት አቶ ሃይለማርያምን ከህወሃት እውቅና ውጪ ያነገሱት በረከት ስምዖን “የወንበሩ የወቅቱ ባለንብረት ህወሃት ነው” በሚሉት ክፍሎች ጥርስ ተነክሶባቸው እንደነበር ምንጭ እየጠቀሱ በርካታ ሚዲያዎች መዘገባቸው አይዘነጋም። በመተካካት ከኢህአዴግ መንበር ይወገዳሉ ወይም ተወግደዋል የሚባሉት አንጋፋ የድርጅቱ መሪዎች ጥላቸውና እጃቸው መዋቅሩን ነክሶ በመያዙ አሁንም በቀጣዩ ምርጫ የሃይለማርያም ጉዳይ በነዚሁ ሰዎች እጅ እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://staging.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule