• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኦፌኮ ከለዘብተነት ወደ ነውጠኝነት

January 20, 2020 08:13 am by Editor Leave a Comment

ህግ ያልገዛውን ሀይል ይገዛዋል

ዛሬ ጦርነቱ ግልፅ ሆኗል። ኦፌኮ መንግሥትን ምንም አታመጣም እስኪ የምታደርገውን አይሃለሁ እያለው ነው። ኦቦ መረራ በስተርጅና ዋልታ ረገጥ ሆነው ፈንድተዋል። ሀይማኖት ውስጥ ያሸመቁ መናፍቃን ባደባባይ ፖለቲካውን ተቀላቅለዋል። ነውጠኛው ጃዋር ራሱን እንደ አሜባ አራብቷል። ጦርነቱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ብቻ ላይ አይደለም ያጠነጠነው የሀገሪቱን መሰረት የመፈነቃቀል ስትራቴጂ ፊት ለፊት አንግቦ እንጂ።

ይህ ሀገር ላይ የተመዘዘ ሰይፍ የቱንም እምነት አይምርም። ሀገር ሳለች ነው እምነት፣ ክብርም፣ ራሱ መኖርም። ማንም ራሱን ካላሞኘ በስተቀር፣ ሁሉም በሰላም በማይኖርባት አገር ውስጥ የብቻዬን የሰላም ደሴት እፈጥራለሁ ሊል የሚቻለው አይደለም። እነሆ ዛሬ አንዳች ስውር፣ አንዳች ያልተገለጠ ምስጢር የለም። ዕቅዱ በገሀድ መተግበር ጀምሯል።

የባንዲራ መቃጠል፣ መረገጥና መዋረድ ሀገሪቱን ሊገጥማት ከሚችለው አደጋ አኳያ እየተስተዋለ ይሰጠው የነበረው አፀፋ እጅግ የለዘበ ነበር። ይህ አስተውሎና ሀላፊነት የተሞላው እሳቤ የነውጠኞችን ልብ ከማሳበጥና የአሸናፊነት ስነልቦናን እንዲጎናፀፉ ከማድረግ በቀር አንዳች ሲፈይድ አልታየም።

ዘለግ ብሎ ላሰበው ይቺ ሰንደቅ የተቀዳችው ከማርያም መቀነት ነው መባሉ የልዩነት ብሎም የመካረር ምክንያት ባልሆነ ነበር። እናታችን ማርያም በሁሉም ሀይማኖቶች ቅድስት ነችና። ቀስተዳመናም ቢሆን ለሁላችን አንድ በሆነው ሰማይ ላይ የሚዘረጋ፣ ላይናችን ትሩፋት፣ ለልባችን ትፍስህት የሆነ የፈጣሪ ድንቅ ጥበብ ነበር። አሁን ማ ይሙት ሰማዩ በቀስተዳመና ጥለት ሲጎናፀፍ ተመልክቶ ሀሴት የማያደርግ ሰብአዊ ፍጡር ለመሆኑ ማን ይሆን?

ጎበዝ ነገሩ ሁሉ እንዳይጥም እንዳይጥም እየሆነ ነው። እስኪ አሁን ይቺ መከረኛ ቤተክርስቲያን ማንን አሳልማ ነው ማንን የነፈገችው? እውን ለብርሀኑ የተዘረጋ መስቀል ለመረራ ታጠፈ? እስኪ አሁን መራራን የትኛው ካህን፣ የትኛው ደብር ነው መስቀል እንዳይሳለሙ ያቀባቸው?

ሰማእቱ አባታች ብፁእ አቡነ ጴጥሮስ “ምነው ኢትዮጵያን ጨከንሽባት፣ ምነው መቀነትሽን ታብቂባባት” አሉ እንጂ የት ጋር ነው ኦሮሚያ የሚል ቃል ካንደበታቸው የወጣው? ከነከሳት መርዝ ልቅመስ በፈጃት እቶን ልንደድላት ያሉት ለእምዬ ኢትዮጵያ እንጂ ለኦሮሚያ ነበርን?

አገር ከፈረሰ፣ እምነት ከተፋለሰ በኋላ ምን ላይ ተቆሞ ነው ዴሞክራሲውስ የሚገነባው፣ ፍትሁስ የሚበየነው? መንግስት ባለበት ሀገረመንግስት ባደባባይ የምፅአት ቀን ሲታወጅ ለማን አቤት ይሏል።

የኦሮሚያ ፖለቲካ የመናፍቃን ዋሻ ሆኗል። የአክራሪዎች ሰይፍ በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ ተመዟል። ሸዋ በራሱ ቤተክርስቲያን ላይ ጦር እንዲሰብቅ ክተት ተብሏል። ክርስቲያን በክርስቲያን ላይ እንዲነሳ ነጋሪት ተጎስሟል። የገብረጉራቻ ህዝብ አባት አያቱ በደም ሳይቀር፣ በነብስ ሳይቀር የተዋጁላትን እምነቱን እንድትዋረድ፣ እንድትመክን የጃዋር አበጋዝ የእርኩሰት መነባንቡን ሲያዝረበርብ ተስተውሏል። ደብረሊባኖስ በፅንፈኞች መዳፍ ስር እንድትወድቅ በፒኮሎው ጃዋር በኩል ቄሮና ቀሬ ክተቱ ተብለዋል። ይህ እየሆነ ያለው ኦፌኮ በሚዘውረው፣ ጃዋር በሚሾፍረው የአክራሪዎች ጎራ ነው።

እዚህ ከተደረሰ ቀጣዩን ለመተንበይ ጠንቋይ መሆን አያስፈልግም። ካህናትን እረዱ፣ ምእመናንን ጨፍጭፉ፣ አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥሉ መባሉ ሳይታለም የተፈታ ነው።

እቺ ቤተክርስቲያን ጠላቶቿ ተበራክቷል። ከከፍታዋ ለማውረድ፣ ክብሯን ለመናድ፣ ህልውናዋን ለማጥፋት ረጅም፣ በጣም ረጅም መንገድ ተኬዷል።

መላው የእስልምናም፣ የፕሮቴስታንትም ሆነ የዋቄፌታ አማኞች ከዚች ግፉእ ቤተክርስቲያን ጎን ልትቆሙ ይገባል። የአንዱ መኖር ለሌላው ዋስትና እንጂ ጠር አይደለም። ካንዱ በደል ሌላው ቢያጎል እንጂ አይከስብም።

ቤተክርስቲያንም ብትሆን ምእመኑን ከአመፅ ማቀቧ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከአመፅ በመለስ ባሉ ማናቸውም ተቃውሞዎች ጎምዘዝ ኮምጨጭ ማለት አለባት። አባቶች የጀመሩትን እስኪጨርሱ ድረስ መዘናጋት የለባቸውም። ስሜት ሲንር ጠብቆ የሚፈነዳ፣ አንዴ ቦግ አንዴ እልም የሚል ሳይሆን ግብ ሳይደርስ የማይቆም ትግል ያስፈልጋል። ፅንፈኞች የሚዘሯቸው መርዞች በህግ አግባብ እየተነቀሱ በሰላማዊ መንገድ ለህግ አስፈፃሚ አካላት እንዲቀርቡ ሊደረግ ይገባል።

የፖለቲካ ድርጅቶችም ከትርምስ ለማትረፍ፣ ጠላትን ለመቀጥቀጥና ሌላ ፅንፍ ለማደራጀት ከመጠቀም ይልቅ መንግስት ላይ ጠንካራ ተፅእኖ በማሳረፍ፣ ለምርጫ ቦርድ የተሰነዱ መረጃዎችን በማቅረብ፣ ጠቅላይ አቃቤ ህግም በነዚህ ወንጀለኞች ላይ ክስ እንዲመሰረት ለማድረግ በዚህና በዚህ መሰል እውነቶች ላይ አንድነት ልትፈጥሩ ይገባል። ለምርጫ ቦርድም እንዲህ አይነት አካሄዶችን በዝምታ ማለፍ ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊቶችን ማስከተሉ አይቀርምና፣ አሁን ያልተወሰደ እርምጃ ለወደፊቱ በሚደረጉ ተመሳሳይ ድርጊቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሞራል ልእልናን ያሳጣልና፣ ጠንከር ያለ ህጋዊ እሮምጃ መውሰድ የጊዜው አይታለፍ ጥያቄ ነው።

መንግስት እንደመንግሥት መከበር፣ መታፈር አለበት። መንግሥት እንደ መንግሥት መከበርና መታፈር ካልቻለ የሚዋረደው ህዝብ ነው፣ የሚደፈረው ሀገር ነው። ስለዚህ ለህግ አንገዛም ላለ ሞገደኛ ሀይል ጉልበት አማራጭ ሆኖ ሊገራው ይገባል። ያለችን አንድ ሀገር ናት፣ ልንኮራባትና ልንታበይባት ሲገባን እስከመቼ ተሸማቀንና ተሸምቀን እንኑርባት። እስከመቼ ባበጡ ተረኞች አንገታችን ይሰበር፣ ልባችንስ እንክት ይበል። መረጥንህም አልመረጥንህም ሀገራችን በእጅህ ናትና ትጠብቃት ትታደጋት ዘንድ ግዴታም አደራም አለብህና ኢትዮጲያ ከነውጠኞች ከአክራሪዎች ፍላፃ ጠብቃት። ጉልበት ለጉልበተኞች ግድ ነው። ህግ ያልገዛውን ሀይል ይገዛዋል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን አብዝቶ ይባርክ

Wondemagegnehu Addis


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions, Social Tagged With: hailemichael, jawar massacre, ofc, Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule