• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በኤርትራ መንግሥት አልተገለበጠም

January 22, 2013 03:08 am by Editor 5 Comments

“ኩዴታ ሲደረግ በቅድሚያ በቁጥጥር ስር ሊውል የሚገባው የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያ ነው። በአስመራ  ይህ ስለመሆኑ የተባለ ነገር የለም። ታዲያ እንዴት ነው ኩዴታ ተከናውኗል ሊባል የሚችለው? በርግጥ ገለልተኛና ነጻ የውጪ ሚዲያዎች አለመኖራቸው የመረጃውን መጠንና ጥራት ቢገድበውም እስካሁን የሚወጡት መረጃዎች እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ እንጂ የማስገደድ አይመስልም። በዚህ መነሻ ኢሳያስ ሙሉ በሙሉ አደጋ ውስጥ ናቸው ማለት አይቻልም። ግን የመደራደር ነገር ሊኖር ይችላል” አውሮፓ የሚኖር ኤርትራዊ ለጎልጉል የተናገው ነው።

አስር ሺህ የሚደርሱ የፖለቲካ እስረኞች እንዳሏት የሚነገርላት ኤርትራ ዛሬ አመሻሹ ላይ አዲስ ዜና አሰምታለች። የተቀየሙ የጦር ሃይሎች የማስታወቂያ ሚኒስቴርን ከበው የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ በማስገደድ ላይ እንደሆኑ የተለያዩ የዓለም መገናኛዎች እየዘገቡ ነው። የመፈንቅለ መንግሥት መደረጉንና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እንዳበቃላቸው የገለጹም አሉ። ተቃዋሚዎችን ጨምሮ፡፡

የጎልጉል ዝግጅት ክፍል በቀጥታ አስመራ በመደወል ባገኘው መረጃ መሰረት ዋናውን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቁጥራቸው ከፍተኛ የተባለ ወታደሮች ተቆጣጥረውታል። ወታደሮቹ አፍቃሪ ኢሳያስ የሚባሉት ይሁኑ፣ አፈነገጡ የተባሉት ለማጣራት ግን አልቻለም። “ከተለመደው ውጪ በርካታ ወታደሮች ይመላለሳሉ። አውሮፕላን ጣቢያው ጤነኛ እንቅስቃሴ አይታይበትም” በማለት የተመለከተውንና የታዘበውን ይገልጻል። አያይዞም በከተማዋ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከወትሮው የተለየ እንደሆነ ተናግሯል።

የቴሌቪዥን ጣቢያ የአገር ውስጥ ስርጭቱ እንደተቋረጠ የነገረን የአስመራ ነዋሪ፣ ህዝቡ ሁኔታውን የተረዳና አንድ ነገር እንደሚፈጠር የተረዳ በሚመስል መልኩ ተረጋግቶ ሁኔታዎችን እየተከታተለ እንደሆነ አስታውቋል። በኤርትራ ሁለተኛ ታላቅ ከተማ የምትባለው ባጽዕ (ምጽዋ) ኩዴታ ባከናወኑት ሃይሎች እጅ እንደሆነች መስማቱንም ይናገራል።

አዲስ አበባ መቀመጫቸውን ያደረጉት የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ተቃዋሚዎች ለአልጃዚራ እንደተናገሩት የጦር ሃይሉ በኑሮ ውድነት ተማሯል። እለት እለት እየተባባሰ በመጣው የኑሮ ቀውስ መንግስትና ወታደሩ አለመተማመን ደረጃ መድረሳቸውን ከመጠቆም ውጪ በትክክል ምን እየተደረገ እንደሆነ አልገለጹም።

አስመራ የውጪ አገር መገናኛዎችና ገለልተኛ የዜና ወኪሎች ባለመኖራቸው እስካሁን ትክክለኛና ሁሉንም ወገኖች ያካተተ መረጃ አልተሰማም። ይሁን እንጂ በተባበሩት መንግስታት የኤርትራ አምባሳደር አርአያ ደስታ “ምንም ችግር የለም፣ ሁሉም ነገር መፍትሄ ተበጅቶለታል። ሁሉም ነገር መልካም ነው” ሲሉ ለአልጃዚራ አስታውቀዋል።

ታዛቢዎች እንደሚሉት የታሰሩት የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ከሚጠይቁት ውጪ የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት እንደማይታይ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ግን ኢሳያስ አስመራ እንደማይገኙና ምን አልባትም ምጽዋ እንደሚገኙ የሚጠቁሙት ክፍሎች የኤርትራ መንግስት ኮማ ውስጥ ስለመሆኑ ከበቂ በላይ ምልክቶች እንዳሉ ይናገራሉ። ከአስመራ በስልክ ያነጋገርነው የከተማዋ ነዋሪ እንዳለው ባጽዕ (ምጽዋ) ያለው ሃይል ከከዳ በርግጥም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ችግር ውስጥ ናቸው ማለት እንደሆነ ገልጾዋል።

በመጨረሻ ባገኘነው መረጃ ኤርትራ ውስጥ መንግስት እንዳልተገለበጠና መንግስትን ለመገልበጥ የሚያስችል እንቅስቃሴ አለመስተዋሉን ነው። ፕሬዚዳንቱ በትክክል ያሉበት ባይገለጽም በቅርብ በመከታተል መመሪያ በመስጠት ላይ እንደሆኑ ከአስመራ በስልክ ሰምተናል። አፈንጋጮቹን ለሚመሩት  የጦር መኮንኖች የፖለቲካ እስረኞች የሚፈቱበት አግባብ እንደሚመቻች ቃል መግባታቸውም ተነግሯል።

የአሜሪካ ሬዲዮ አላዝቦ ያቀረበው ዜና  አማጺ ያላቸው ወታደሮች የማስታወቂያ ሚኒስቴርን በመቆጣጠር የታሰሩ እንዲፈቱ፣ እኤአ በ1997 የተዘጋጀው ህገመንግስት ይከበር የሚል መግለጫ በማስገደድ ማስነበባቸውን አስደምጧል።ዘግይቶ የደረሰን ዜና በማለት አሜሪካ ዜጎቿ ወደ አስመራ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲገድቡ ትዕዛዝ መስጠቷን ተናግሯል።

አፈንጋጮቹ በግዳጅ ላይ ካለው የጦር ሃይል ዘንድ ስላላቸው የጠበቀ ግንኙነት እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ የማስታወቂያ ሚኒስቴርን በመቆጣጠር አስገድደው ያስነበቡትን መግለጫና የፖለቲካ አስረኞች ይፈቱ ጥያቄ ተከትሎ ከዋናው ስቱዲዮው በመቀበል ዜናውን የሚያሰራጨውን መስመር (ዋናውን አንቴና) እንዲቋረጥ በታዘዘው መሰረት ዜናው የጦር ሃይሉና ህዝብ ጆሮ በሚፈለገው ደረጃ እንዳልተዳረሰ ለማወቅ ተችሏል። አስመራ ያልተለመደ የወታደሮች እንቅስቃሴ ከመታየቱ በቀር ሁሉም ነገር የተረጋጋና የመንግስት ማስወገድ እንቅስቃሴ አለ የሚያስብል አይስተዋልም።

(ፎቶ፡ madot)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://staging.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Ast says

    January 22, 2013 04:30 am at 4:30 am

    Fair and balanced reporting from an Ethiopian website. gd job

    Reply
    • Milkias berhane says

      January 22, 2013 12:31 pm at 12:31 pm

      Be eritrea guday lay mizanun yetebek report ke ethiopian web lay saneb lemejemeria new thank yuo GOLGUL

      Reply
  2. Jimma says

    January 23, 2013 04:03 pm at 4:03 pm

    For a simple argument let us say the current government of Eritrea is gone. What good will that bring to the nation? Can we not learn what is happening in the rest of the world with likes of Somalia, Libya, Egypt and the mess we see in Syria. I am not a supporter of removing Mr. Isaias by force. It will create a huge problem that will not be resolved in years to come. Think people! Hardship is better than bloodshed!!

    Reply
  3. Azeb says

    January 24, 2013 10:02 pm at 10:02 pm

    The photo is dated!

    Reply
  4. andnet berhane says

    February 20, 2013 11:33 pm at 11:33 pm

    ባጠቃላይ የነበረው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ድራማ ለመሆኑ ከይዞቱና አቶ ኢሳያስ ቃለመጠየቅ እምንወስዳቸው ቁምገሮች አሉ ለመሆኑ በብዙ ሃገራት ኩዴታ በሚካሄድበት ብዙ የደም መፍሰስና አለመረጋጋት ይኖራል ሆኖም ግን በኢሳያስ አባባል እንቅስቃሴውን ሲያደርጉ ቁጭ ብለን እንከታተለው ነበር ሲሉ ተደምጠዋል እነኛም ኩዴታ ሊያደርጉ የተነሰት የዜና ማእከኑን በመቆጣጠር የነበራችቸውን ጥያቄ ማለት ፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ሕገመንግስቱ ይሻሻል የሚል ተናግራእ ወደ ጦር ሰፈራቸው ትመለሱ ይልና የኩዳታው አነሳሽ የነበሩት አንዱ ራሱን ገደለ የተቀሩት ይቅርታ አሳስተውን ነው የሚል ነበር በቃል ምልልሱ የሰጡት፡ ኩዴታ ማለት የኳስ ግጥሚያ የሰፈር ልጆች ጥል ሳይሆን ሕገመንግስትን መጣስ በመሆኑ በይቅርታ የመታለፉ ጉዳይ አነጋጋሪ ሲሆን ከሁሉም የሚደንቀው ለጉዳዩ መግለጫ ለመስጠት ያልፈለግንው ሕዝቡን ላለ መረበሽ ነው ይላሉ በሌላው በኩል እኛ የምንሰራው የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ያለረፍት እየሰራን ወሬኞች በሩቅ ሆነው ይዋሻሉ ሕዝብን ይቆሰቁሳሉ እኛግን ስራችንን እየሰራን ነው ይሉና አንድ አስደናቂ የሆነ የአረብኝ ምሳሌ ተናግራዋል “ለልክዛብ ገድም ለልባብ” ውሸታምን እስከበር ሸኘው ማለት ነው ስለዚህም እንደ አቻቸው የትግል ጓድኛቸው መለሰ ድራማ መስራት ያውቁበታል ፡ እንዲሁም የሚቀናቀኑዋቸውን ለማጥፋት ምክንያቶች በመፍጠር እነኝህ መቶ የሚሆኑ መኮንኖች እነማን ናቸው ብሎ መጠየቅና ለማወቅ አስቸጋሪ አይሆንም ከበረሃ ጀምረው ያደጉ የትምሕርት እድል ያላገኙ ኢሳያስን እንደ ጣኦት የሚያመልኩ የሱ ታዛዞች በመሆናቸው ድራማውን እንዲተውኒዩ ተደርጋው እነኛም ተጠርጣሪዎች ወደቄራ መውረዳቸው የታወቀ በመሆኑ ፡ ለዚህ ምንም አይነት አሰሳና መረጃ አያስፈልግም የሚል እምነት አለኝ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule