• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ድንጋይ ቢቆሉት አይሆንም ቆሎ”

July 8, 2014 12:54 am by Editor 2 Comments

ሉቃ ም.14 ከቁ.15-24 “በእግዚአብሔርመንግስት እንጀራ የሚበላ ብፁዕ ነው አለው፡፡ እርሱም ግን አንድ ሰው ታላቅ እራት አዘጋጅቶ ብዙዎችን ጠራ፡፡በእራትም ሰዓት አሁን ተዘጋጅቷልና ኑ እንዲላቸው ባሪያውን ላከ ሁላቸውም በአንድነት ያማካኙ ጀመር ይላል፡፡” የሚገርመው የነዚህ ሰዎች ምክንያት ተራና የውሸት ምክንያት መሆኑ ነው “ፊተኛው መሬት ገዝቻለው ወጥቼ ላየው በግድ ያስፈልገኛል” አለ፡፡ ሰው መሬትን መርምሮ የሚያየው ከመግዛቱ በፊት እንጂ ከገዛ በኋላ ነው? ሁለተኛውም “አምስት ጥማድ በሬዎችን ገዝቼአለው ልፈትናቸው እሄዳለሁ”አለ፡፡ በሬን የሚገዛ ሰው በሬውን የሚፈትነው ቀንበር መሸከም መቻሉን አለመቻሉን አይቶ ማረጋገጥ ያለበት ከመግዛቱ በፊት ነው ወይስ በኋላ? በተጠቀሰው መጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ ላይ ታሪኩ በሰፊ ይገኛል፡፡ ምክንያተኛ ሰው ሌላው ቀርቶ እግዚአብሔር ሲጠራው ይቸገራል፡፡

ምክንያት ለሰው ልጅ ለየትኛውም እንቅስቃሴ አስፈላጊ ከመሆኑም ባሻገር ተፈላጊም ጭምር ነው፡፡ ምክንያት አያስፈልግም ከሚል መደምደሚያ የሚያደርስ የማናቸውም ሰው ክርክር ዉሃ የማይቋጥር ጉንጭ አልፋ ሙግት ነው፡፡ ለማድረግ ወይም ላለማድረግ የቀረበው አመክንዮ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? ለማለት ምክንያታዊ አስተሳሰብን መሠረት በማድረግ መሞገት፣ ተመራጭ አሳብን ለማቅርበ እድል ይሰጣል፡፡

በመሆኑም የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውህደት፣ ቅንጅት እና ትብብር በተጠና መልኩ ከተከናወነ ውጤት አለው ተብሎ እንደሚነገረው ሁሉ እራስን ከማታለል እና ድክመትን በሌላው ከመሸፈን ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም የሚል አቋም እንዳለም የሚታወቅ ሃቅ ነው፡፡ የየትኛውም ወገን ክርክር “ለሃገር የቱ ይጠቅማል?” ከሆነ፣ ምክንያቱ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው ብሎ ለመቀበል አዳጋች አይሆንም፡፡ ነገር ግን ክርክሩ ከነምክንያቱ “ለፓርቲዬ የቱ ይጠቅማል ከሆነ?” ችግሩ የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ ክርክር ምክንያት አልባ ከመሆኑ ባለፈ የስብህና ዝቅጠትም ይሆናል፡፡ የዚህ ጹሑፍ ዋና ዓላማ እነዚህን ሁለት ምክንያቶችን መነሻ በማድረግ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውህደት፣ቅንጅት እና ትብብር በመጠኑ ለመዳሰስ ነው፡፡

ምርጫ 97 በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ስርአት ውስጥ የራሱን አዎንታዊ እና አሉታዊ አሻራዎች ጥሎ ያለፈ የ10 ዓመት የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ በወቅቱ የአራት ፓርቲዎች ስብጥር የፈጠረው ቅንጅ ለጠላትም ለወዳጅም የሁሉ ጊዜ የቤት ስራ ሰጥቶ ያለፈ ነው፡፡ ይህን ለማለት የሚያስደፍረው ከምርጫ 97 በኋላ እስከ ምርጫ 2002 አዲስ የተቋቋሙት እንዲሁም ነባሮቹ አካሄዳቸው አንዱ ሌላውን በሴራ ፖለቲካ ውጦ ከማስቀረት የዘለለ አደባባይ ተይዞ የተወጣ አንዳችም ቁሙ ነገር አልታየም፡፡ ህብረተሰብም በምርጫ ሰበብ ከደረሰበት የልብ ስብራት አገግሞ ስለ አገር እና ፖለቲካ ለማሰብ እና ለመተግበር የነበረው ዝግጁነት እጅግ በጣም አናሳ የነበረበት ወቅት ነው፡፡ በአንጻሩ ገዥው ኢሕአዴግ (የወያኔ) መንግስት በሁሉ መልኩ ራሱን በይበልጥ በአምባገነናዊ ስርአት በማደራጀት በእኩይ ተግባሩ የተጠመደበት የሞት ሽረት ትግል ለማድረግ ተጠቅሞበታል፡፡

ምርጫ2002 እንደ ምርጫ 97 በፖለቲካ ይዘቱም ሆነ ዓይነቱ ፍፁም የተለየ ለይምሰል የተደረገ አገር አቀፍ የምርጫ ሠሌዳ መረሀ-ግብር ለመሸፈን የተካሄደ ምርጫ ነው፡፡ ይህ ምርጫ ውጤት እንደማይኖረው ከበቂ ምክንያት ጋር በማስደገፍ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ይሞግቱ የነበሩ ሰዎች ስለመኖራቸው ስንቶቻችን እናስታውስ ይሆን?! በተለይ አንድነት ፓርቲ የመርህ እና የህግ ጥሰት በመፈፀሙ ከፓርቲው አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆነው በፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም ይመራ የነበረው “የመርህ ይከበር” ስብስብ ምርጫ 2002 ፓርቲዎች በተለይ አንድነት ወደ ምርጫው ከመግባቱ በፊት ሊያጤናቸው የሚገባ ነጥቦች እንዳሉ በማስገንዘብ በውይይት ለመርታት ሙከራ አድርጓል፡፡ በወቅቱ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሂደቱን ክሽፈት ለማፋጠን የያኔው አንድነት ፓርቲ የአንበሳውን ድርሻ በፍቃደኝነት ወስዷአል፡፡

በወቅቱ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ውጤቱ የተተነበየለት ምርጫ 2002 ኢሕአዴግ (ወያኔ) ይህ ቀረ የማይባል የአፈና ሃይሉን ተጠቅሞ የፓርላማ መቀመጫ ጠቅልሎ በማግኘት ሲንፏለልበት ለማየት ግድ ሆኗአል፡፡ በምርጫ 2002 እድሜያቻው ለመምረጥ ከደረሱ ኢትዮጵያዊያን መካከል 33%ኢሕአዴግ (ወያኔን) የመርጡ ሲሆን የእያንዳንዱ ተቃዋሚ ፓርቲ ማለትም አንድነት፣ መኢአድ፣ ኢዴፓ እና ሌሎችም በምርጫው የተሳተፉ በድምሩ ያገኙት ድምፅ 15% ነው፡፡ በአጠቃላይ 48 % የሚሆኑት በምርጫው በመሳተፍ ለሚፈልጉት ፓርቲ ድምፅ የሰጡ ናቸው፡፡ ነገሩን ይበልጥ አስገራሚ የሚያደርገው የተቀሩት 52% የሚሆኑት ድምፃቸውን ለማንም አልሰጡም፡፡ በሌላ አገላለፅ በምርጫው ከተሳተፈው ይልቅ ያልተሳተፈው ይበልጣል ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በገዥው መንግስት እንዲሁም በተቃዋሚዎች 52% የሚሆኑ መራጮች ተስፋም እምነትም አልነበራቸውም ማለት ነው፡፡ ይህ ሒሳባዊ ቀመር ከመርጫ ቦርድ የተገኘ መረጃ ሲሆን መረጃው የቁጥር ልዩነት አለው ቢባል እንኳን መሰረታዊ ሃቁን የሚያስቀይር አይደለም፡፡ በመሆኑም መረጃውን መሠረት በማድረግ እንዲሁም የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታከግምት በማስገባት ምርጫ 2002 ቅድመ ምርጫ፣ የምርጫ ወቅት እና ከምርጫ በኋላ የተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የገዥው መንግስት እንዲሁም የህብረተሰብ ተሳትፎ በተለይ የነጻ ሚዲያ አስተዋጾ በጥቅል እና በተናጥል በመመልከት ምርጫው “ቅርጫ” ስለመሆኑ ማመላከቻ ነው፡፡

ከላይ በስሱ ለማየት የተመከረው ሁለት አገር-አቀፍ ምርጫ ከፊት ለፊት እየጠበቅን ላለው ምርጫ 2007 ለተቃዋሚ ፓርቲዎች በገዥው መንግሰት የፖለቲካ ንድፈ-ሃሳብ ሠነድ እንዳለ የሚነግረን ነገር ይኖረዋል፡፡ይህን መነሻ በማድረግ በመጪው ምርጫ 2007 የገዥው መንግስት ባሪያ የሆኑትን በስመ ተቃዋሚ ተመዝግበው ከአሳዳሪያቸው ቀለብ የሚሰፈርላቸውን ወደ ጎን በመተው ፡፡ እውነተኛ ተቃዋሚ ነን የሚሉ የኢሕአዴግ (ወያኔ) ንቅዘትና በዘር ከፋፍለህ ግዛው ፖሊስ የሚቃወሙ እንዲሁም ዴሞክራሳዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት ቁርጠኝነቱ አለን የሚሉ ፓርቲዎች ወሣኝ ትግል ሊደረግበት የሚገባው ወቅት ነው፡፡

ይህን ትግል በተልካሻ ምክንያት ውጤት አልባ እንዳይሆን የፖለቲካ ሊሂቃን ብቻ ሳይሆን ስለ አገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ሁሉ ሊመክሩበት፣ውሳኔ ሊሰጡበት እና ተግባራዊ ሊያደርጉት የሚገባ ታላቅ ስራ ነው፡፡ በተለይ የዓላማ አንድነት ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች በመጪው 2007 አገር-አቀፍ ምርጫ የሞት ሽረት ሠላማዊ ትግል የሚያደርጉበት ነው፡፡ በእርግጠኝነት ከወዲኹ መገመት እንደሚቻለው ምርጫ 2007 በአገራች እየታየ ያለው ሰላማዊ ትግል ተስፋ ሰጪ የሚሆንበት ወይም ተስፋ የሚጨልምበት ታሪካዊ ወቀት ነው፡፡ ታሪክ መስራት ደግሞ በተቃዋሚ ፓርቲዎች እጅ የሚወድቅ ሃላፊነት ነው! ይህ አገራዊ ሃላፊነት ከቂም እና ከጥላቻ ፣ ከተሳሳተ ሂሣባዊ ቀመር፣ ከአገር በላይ ለፓርቲ ማድላትእንዲሁም ከራስ ወዳድነትና ከስልጣን ጥማት ራስን በመግታት ትውልድ ተሻጋሪ የሆነ ታሪክ በመስራት የአገራችን ዕጣ ፈንታ የሚወሰንበት የምርጫ መጨረሻ መጀመሪያ ነው፡፡ በአርግጥ ይህ ሃላፊነት የፓርቲዎች ብቻ ሣይሆን ለውጥ ፈላጊ የሆነ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሃላፊነት ጭምር ነው፡፡

የዚህ ጽሑፍ ዋና ማጠንጠኛ እውነተኛ ተቃዋሚዎች እና የዓላማ አንድነት ባላቸው ፓርቲዎች መካከል ሊተባበሩ ወይም ሊቀናጁ ከተቻለ ውህደት ሊፈጥሩ እንደሚገባ ለማመላከት ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ አንድነት እና መኢአድ ቅድመ ውህደት መፈፀማቸው እጅግ በጣም አስደሳች ከመሆኑ ባለፍ ለሌሎችም ተስፋ ሰጪ ነው፡፡ ከፈፀሙትም ቅድመ ውህደት ወደዋናው ውህደት የሚያደርጉት ጉዞ የተሳካ እንዲሆን ከመመኘት ባለፈ ለውህደቱ አስታዎፆኦ ሊያበረክት የሚችል ማናቸውም ነገሮች መተግበር ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በባለፈው ሳምንታት የብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ጥልቀት ያለው ውይይት በማካሄድ ፓርቲው ከመቼው ጊዚ በላይ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በትብብር ለመሥራት መዘጋጀቱ መግለጹ ይበል የሚያስብል መልካም ጅማሮ ነው፡፡

በመሆኑም እውነተኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ነን የሚሉና በህብረተሰብ ተቀባይነት ያላቸው ፓርቲዎች በሙሉ፤ ደግመው ደጋግመው እልህ አስጨራሽ ሂደቱን ተከትለው ሊተባበሩ ወይም ሊቀናጁ ከተቻለ ውህደት ሊፈጥሩ ይገባቸዋል፡፡ ይህን የሚያደርጉት ተባባሩ ወይም ተሰባበሩ የሚባለውን ለመሸሽ ወይም ለመጋፈጥ ሳይሆን እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ በጥልቀት እራሱን በመፈተሸ ጠንካራና ደካማ ጎኑን በመለየት ከሚዲያ ፍጆታ ባለፈ መሬት የያዝ ስራ ምን ሰራሁ ? ምንስ ይቀረኛል ? በማለት ጉድለት የሚሞላበት ስኬት ለሌላው የሚያስተላልፉበት የትብብር፣ የቅንጅት እና የውህደት ጊዜው አሁን ነው!!! የማይካድ ሃቅ ቢኖር የፓርቲዎች ትብብር፣ ቅንጅት እና ውህደት መካከል አጋፋሪዎች መኖራቸው ነው፡፡ እነዚህን በጥንቃቄ በመለየት እና በማስረዳት ካልተቻለም በመነጠል አሸናፊ ለመሆን ትጋትን የሚጠይቅ የጎን ለጎን ስራ ያስፈልጋል፡፡ በይበልጥ ደግሞ ትብብር፣ ቅንጅት እና ውህደት ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ለዚህ ጽሑፍ በመግቢያነት የተጠቀሰው ዓይነት ወንዝ የማያሻግር ተልካሻ ምክንያቶችን በመደርደር ለሰላማዊ ትግሉ እንቅፋት ላለመሆን እራስን መጠበቅ የተሻለ ነው፡፡

ይድነቃቸው ከበደ
ይድነቃቸው ከበደ

በመጨረሻም የዚህ ጽሑፍ ማጠቃለያ የሚሆነው በባለፈው ምርጫ 2002 ክስተትን በማስታወስ ነው፡፡ እሱም ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በተወዳደሩበት አካባቢ 2ኛ ሆነው ነው የተሸነፉት 1ኛ የወጣው የወያኔ ተላላኪ የበለጣቸው 130 ድምፅ ነው፡፡ በዚያው አካባቢ መኢአድ ወክለው የተወዳደረው ከ400 በላይ ድምፅ አግኘተው ነበር፡፡ ከዚህ የበለጠ ስለትብብር፣ ቅንጅት እና ውህደት ምን ጥሩ ማሳያ ይኖራል በማለት መደምደም ባይቻልም እንደግብአት ለመጠቀም ግን የተሻለ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህን እና መስል ሃቆችን ግምት ውስጥ በማስገባት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጉዞ “ድንጋይ ቢቆሉት አይሆንም ቆሎ” ከመባል እና ተተፍቶ ከመጣል እራስን ማዳን ምንኛ መታደል ነው፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Hus says

    July 11, 2014 05:21 am at 5:21 am

    እንዲህ ነበር ምኞታቸዉ! ነበር ዋጋ የለዉም እንጂ የግንቦት 7 የሰሞኑ የዉግያ ስልት 00አንደርጋቸዉ ኦፕሬሽን ይሳኘል00 ከመኃል ሰማያዊና የአንድነት እግራኛ ብርጌድ ከደጃን በሁሉም ሀገራት የሚገኙ የዞረባት ድያስፎራ ተስፈኛዉ ሽላቃ በምስራቅና ምዕራብ ኦነግን ነፈቅ ጣባቡ የተሳኛዉ መድፈኛ በሰሜን ትምክህታኛ በመባል የሚተዋቅ የረጃ ኮመንዶ የዉግያዉ ቦታ በፌስ ቡክ ዓዉደ ግንበር ዓለማዉ የጦር አዛዠቸዉን አንደርጋቸዉ ፅጌን በኦፕሮሽን የፌስ ቡክ ሁከት ማስለቃቅ እንደ ሆነ ከእሳት ጠብያ አፈትልኮ የወጣ መራጀ ይገልፃል:: ለመብራራዉ 000000 ድረ ገልፅን ይመልከቱ!በቁማቸዉየሞቱ ደጋፍዎቻቸዉ እንደ ነገሩኝ

    Reply
  2. shimon says

    July 11, 2014 10:05 am at 10:05 am

    ፅፈህ ሞተሀል! የወያኔ ተላላኪ ብሎ ስለዲሞክራሲ ማውራት የኢህአዲግ ደጋፊዋችን መብት ሳትጠብቅ ስለሌላው ማውራትህ ዳንቴልነትህን ያሳያል
    ኢህአዴግ! ምርጫውን በጉጉት የሚጠብቅ የተመዘገበ ሰላሳ ምናምን ሚሊየን አባል አለው አጋር ድርጅቶችን ሳይጨምር .. እንድ ሚሊየን ለማይሞላ ደጋፊ ብሎም አንባቢ ስለፃፍ በቃ ልብህ ጥፍት ብሎዋል ይልቅ ምርጫው ሲያምርህ ይቅር! የተበላ ዕቁብ መሆኑን አምነህ ስለእንትን (?) ፃፍ..
    “ረጅም እድሜ ለኢህአዴግ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule