• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ገሃዱ አሰቃቂ ረሃብ እና የማወናበጃው “የልማት ዕድገት” በኢትዮጵያ

November 26, 2015 11:45 pm by Editor Leave a Comment

በያዝነው ዓመት በአገራችን በኢትዮጵያ አስከፊ የርሃብ አደጋ እንደተስፋፋ ከተለያዩ የዜና አውታሮች ይደመጣል። በተቃራኒው ደግሞ የትግሬ-ወያኔ የሚቆጣጠራቸው የመገናኛ ብዙሃን በአገዛዙ ጥረት ስለተገኘው የልማት ትሩፋት ይለፍፋሉ። በአንድ አገር በአንድ ጊዜ ሁለት እጅግ ተቃራኒ ሁኔታን የሚያንጸባርቁ ዜናዎች ሲደመጡ እውነቱን አንጥሮ ማሣዬት ተገቢ ነው። ስለሆነም በዚህ መግለጫ ዕውነቱ የትኛው እንደሆነ ብቻ ሣይሆን የመፍትሔ ኃሣቦችንም ለማመልከት ተሞክሯል።

በአገራችን በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ጊዜያት ከፍተኛ የርሃብ አደጋዎች ተከስተዋል። በዚሁ ሳቢያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን አልቀዋል፤ አሁንም እያለቁ ነው። ለአብነት ያህል በንጉሡ ዘመን በ1958 ዓ.ም. እና በ1965-66 ዓ.ም. እንዲሁም በደርግ ጊዜ በ1977 ዓ.ም. የተከሰቱት የርሃብ አደጋዎች በአስከፊነታቸው እና በሕዝብ ጨራሽነታቸው የሚጠቀሱ ናቸው። በትግሬ-ወያኔ የአገዛዝ ዘመን ርሃብ አልፎ አልፎ የሚመጣ ሣይሆን በየዓመቱ ከ7 እስከ 25 ሚሊዮን የሚደርሱ ኢትዮጵያውያንን ለችጋር ማጋለጡ እና የሰው እጅ ተመልካች እንዳደረጋቸው ይታወቃል። ይህም ሆኖ እንደ ዘንድሮው እጅግ የከፋ አልነበረም። በመሆኑም በዚህ ዘመን ርሃብ በኢትዮጵያውያን ላይ ቤቱን ሠርቷል ለማለት ያስደፍራል። ስለሆነም ሦሥቱም ተከታታይ አገዛዞች አንዱ ካለፈው ገዢ ስህተት ሊማር ባለመቻሉ ችግሩ እየተባባሰ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም።

በሦሥቱም የአገዛዝ ዘመኖች ለርሃቡ መንስኤ ተደርጎ የሚቀርበው ድርቅ ነው። ከፍተኛ የዝናብ እጥረት ሲከሰት ድርቅ ይፈጠራል። ስለዚህ ድርቅ የተፈጥሮ ክስተት በመሆኑ ምንጊዜም የአየር ንብረት አካል ነው። ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወንዞች እና ሐይቆች ያሏት፣ በተፈጥሮ ኃብት የታደለች አገር ናት። ስለሆነም ሕዝብን የሚወክል እና ሕዝባዊ ተሳትፎ ያለው ሥርዓት ካለ፤ የድርቁን ተፅዕኖ ለመቋቋም ይቻላል። ይኽውም፥ ወንዞችን በመገደብ እና የሐይቆችን ውኃ በመጠቀም ከፍተኛ የመስኖ እርሻ ማስፋፋት ይቻላል። እንደሚታወቀው ከ85% የማያነሰው የአገራችን ሕዝብ ከእጅ-ወደ-አፍ በሆነ የግብርና ኢኮኖሚ ዘርፍ የተሰማራ ነው። ይኽ የአገራችን ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነው ዘርፍ እስካሁን ድረስ የሚዘወረው ከጥንት ጀምሮ ባልተቀየረ ኋላቀር የበሬ እርሻ ነው። «ይህ ኋላቀር የእርሻ ዘይቤ ሣይቀየር አገሪቱ እንዴት በልማት ትሩፋት ልተምነሸነሽ ትችላለች?» ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል።

አሁን በአስከፊ ሁኔታ የተከሰተው ርሃብ በሥልጣን ላይ ያለው ፀረ-ሕዝቡ እና ፋሽስቱ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የፈጠረው ነው። እንዴትስ ፈጠረው? ምክንያቶቹ፥

  • የኢትዮጵያ መሬት ብቸኛ ባለቤት የሆነው የትግሬ-ወያኔ ገዥ ኃይል ገበሬውን እጅግ አነስተኛ በሆነ የእርሻ መሬት ስለወሰነው፣ ገበሬው በቂ ምርት ማምረት አልቻለም።
  • ገበሬው የተበላሸ እና ጊዜው ያለፈበት ማዳበሪያ በግድ እንዲገዛ በመደረጉ መሬቱ ተጎድቷል፣ ለምነቱም ቀንሷል።
  • ገበሬው በቀላሉ ገንዘብ የሚገኝበት ሰብል (cash crop)፥ እንደ ጫት፣ አበባ ወዘተርፈ …. እንዲያመርት በሥርዓቱ በመገፋፋቱ የምግብ እህል ምርት አሽቆልቁሏል።
  • በወያኔ የዘር ማጽዳት ፖሊሲ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ገበሬዎች፣ በተለይም ዐማሮች፣ ከነቤተሰቦቻቸው ከቀያቸው በመፈናቀላቸው ምክንያት አምራቾች ሣይሆኑ የዕለት ምግብ የሚመፀወቱ ምንዱባን ሆነዋል።
  • በፍጥነት እያደገ የመጣው የሕዝብ ብዛት የእርሻ መሬት ጥበት በማስከተሉ፣ ሥራ ለመፈለግ ከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሰውን ገበሬ ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል። ይህም በእርሻው ኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ውድቀት አስከትሏል።
  • የትግሬ-ወያኔ ሆን ብሎ ከፍተኛ የደን ክምችት ያላቸውን ቦታዎች በየጊዜው በእሳት በማጋየቱ ምክንያት የአገራችንን የተፈጥሮ ሚዛን እና የአካባቢ አየር ንብረት በማዛነፉ ድርቅ በተደጋጋሚ እንዲከሰት አድርጓል።
  • የትግሬ-ወያኔ ከፍተኛ ለምነት ያላቸውን የእርሻ መሬቶች እስከ መቶ ዓመት በሚደርስ የጊዜ ገደብ በሊዝ መልክ ቸብችቧል። መሬት በሊዝ የሚገዙት ራሱ የፈጠራቸው የአገር ውስጥ ከበርቴዎች እንዲሁም የውጭ አገር ከበርቴ ግለሰቦች እና ኩባንያዎች ናቸው። እነዚህም ከበርቴዎች እና ኩባንያዎች የሚያመርቷቸውን ምርቶች የሚያቀርቡት ለአገር ውስጥ ፍጆታ ሳይሆን በቀጥታ ለውጭ አገሮች ገበያ እና ሸማች ይልካሉ። ስለሆነም ኢትዮጵያውያን በእጅ-አዙር ቅኝ አገዛዝ ሥር ወድቀው የበይ ተመልካቾች በመሆናቸው እና በአገራቸው ውስጥ የሥራ እድል ሊያገኙ ስለአልቻሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣት አምራች ኃይሎች ለሥራ እድል ፍለጋ ወደ አረብ አገሮች ለመሰደድ ተገድደዋል።
  • ለተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተብሎ በእርዳታ እና በብድር መልክ ከውጭ የሚገባው ብዙ ቢሊዮን ዶላር፤ እንዲሁም የአገራችን አንጡራ ኃብት በትግሬ-ወያኔዎች ያለማቋረጥ ይዘረፋል። ይህም ድህነት እንዲሠራፋ አድርጓል።
  • የድርቅን አደጋ ተቋቁሞ ርሃብን በዘላቂነት ለመግታት ሠፋፊ የመሠረተ-ልማት ግንባታዎች ማከናወን ወሣኝ ነው። ሆኖም ባለፉ አገዛዞች ከነበረው አዝጋሚ የመሠረተ-ልማት ግንባታ በከፋ ሁኔታ በዘረኝነት መንፈስ የትግራይ ክልል የተባለው ብቻ ተጠቃሚ እንዲሆን ይደረጋል። ከዚህ በተጨማሪም የአገዛዙ ሥርዓት ዕድሜውን ለማራዘም ከአገሪቱ በጀት ከግማሽ የማያንሰውን ለስለላ ሥራ ያውላል። ስለዚህ በርሃብ ወቅት ሕዝቡን ከአደጋ ለመታደግ የሚያስችሉ ከፍተኛ የእህል ጎተራዎች አልተሠሩም፤ ጤና ለመጠበቅ የሚያስችሉ ተቋሞች አልተገነቡም፣ እንዲሁም ወደ ገጠሩ እንደልብ ለመግባት የሚያስችሉ የገጠር መንገዶች አልተዘረጉም።
  • የትግሬ-ወያኔ በሚከተለው የከፋፍለህ-ግዛው ፖሊሲ ምክንያት ሕዝባችንን በዘር፣ በጎሣ እና በኃይማኖት እየለያየ ያጫርሳል። የእርስ በርስ ግጭቶች እና ጦርነቶች በተለያዩ አካባቢዎች በመከሰት ላይ ናቸው። ለአብነት ያህል፥ በጎንደር፣ በወሎ፣ በሸዋ፣ በጎጃም፣ በአርሲ፣ በወለጋ፣ በባሌ፣ በኦጋዴን፣ በጋምቤላ፣ በሲዳሞ፣ በጋሙ-ጎፋ፣ በከፋ፣ ወዘተርፈ …. በተደጋጋሚ ጊዜያት ሕዝብ እርስ በእርሱ እንዲጫረስ ተደርጓል። ይህም የአምራቹን ኃይል ቁጥር የሚያመናምን፣ በተቃራኒው ለርሃብ አደጋ የሚጋለጠውን ዜጋ የሚያበዛ ነው።

ርሃብ እና ችጋር እንደ ደራሽ ጎርፍ በድንገት አይመጡም። በመጀመሪያ ድርቅ ሲከሰት ሰብሎች ይጠወልጋሉ፣ ምርትም አይገኝም፤ ይህ በትንሹ ከሦሥት ወራት ያላነሰ ጊዜ ይወስዳል። በድርቅ ጊዜ ከብቶች በግጦሽ ሣር እና በውኃ እጦት ይኮሰምናሉ፣ ከዚያም በገፍ ያልቃሉ። ይህ ሁሉ በአንድ ቀን ጊዜ አይከሰትም። ስለዚህ ከድርቅ ጋር የተያያዘን ችጋር ለመቋቋም በአንድ አገር የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ እና የዝግጁነት ሥርዓት ካለ ሕዝብ ለርሃብ አይጋለጥም። ይህ ተሞክሮ ረሃብን ታሪክ ለማድረግ በበቁ አገሮች በተግባር ታይቷል። በእኛም አገር ለአጭር ጊዜም ቢሆን ምልክቱ ታይቶ ነበር። በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ግን የሚደረገው ሆን ተብሎ የዚህ ተቃራኒ ነው። በአፄ ኃይለሥላሤ ዘመን «የድርቅ ኮሚሽን» በመባል የተቋቋመው መሥሪያቤት በደርግ ዘመን እጅግ ጎልብቶ የአገሪቱን ሕዝብ ከከፍተኛ የርሃብ መቅሰፍት ለመታደግ የሚያስችል ተቋም ለመሆን በቅቶ ነበር። በተደጋጋሚ በርሃብ ሲጠቁ የነበሩ ዜጎችን ለም እና ለኑሮ ተስማሚ የሆነ የአየር ንብረት ባላቸው አካባቢዎች በማስፈር ከተረጂነት ወደተትረፈረፈ ምርት አምራችነት ለመቀየር ተችሎ ነበር። ዛሬ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ከገጠር እስከ ከተማ፣ በሁሉም ሥፍራ የዕርዳታ እህል የማይሠፈርለት ዜጋ በቁጥር ነው። ያም ቢሆን ውጭ አገር ያሉ ዘመዶቹ ገንዘብ የሚልኩለት፤ አልያም የወያኔ ሹመኛ ከሆነ ብቻ ነው። በተለይ ደግሞ ዐማራውን ለይተው ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በዘር ማጽዳት ዘመቻ በማፈናቀል በርሃብ እና በችጋር ይፈጁታል። «ለወያኔ አገዛዝ አንንበረከክም» ያሉትን አፋሮችን እና ሶማሌዎችን በርሃብ ይቆላሉ። በአጠቃላይ ለርሃብ እና ለችጋር የሚያጋልጠው ብልሹ እና ኃላፊነት የጎደላቸው አገዛዞች የሚፈጥሩት ችግር እንጂ ድርቅ ብቻውን ሊሆን አይችልም። ድርቅ ብቻውን ርሃብ የሚያመጣ ቢሆን ኖሮ የዝናብ ጠብታ የማያውቁ አገሮች ዜጎች ገና ጥንት ከምድረ-ገፅ ይጠፉ ነበር።

አንዳንድ ጸሐፊዎች «ፖለቲካ እና ሰብዓዊነት መያያዝ የለበትም» የሚለውን ኃይለ-ቃል ደጋግመው ይናገራሉ። ሆኖም ይህን የሚናገሩት በአፄ ኃይለሥላሤም ሆነ በደርግ የአገዛዝ ዘመኖች ለተከሰቱት የርሃብ ችግሮች ምንጮቹ የአገዛዝ ሥርዓቶቹ መሆናቸውን ሲያስተጋቡ የኖሩት ናቸው። ዛሬ ታዲያ ካለፉት ሁለት የአገዛዝ ሥርዓቶች እጅግ በከፋ ሁኔታ ኢትዮጵያውያንን ለማያባራ የርሃብ ችግር የዳረጋቸው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ሆኖ ሳለ ከዚህ ፍርድ እንዴት ሊያመልጥ ይችላል? የትግሬ-ወያኔዎች ኢትዮጵያውያንን በርሃብ እያቆራመዱ ዶላር ለመሰብሰብ የበሰለ ምግብ ወደ ውጪ አገሮች ይልካሉ። በአገር ቤት ግን ዜጎች የሚጣል የምግብ ትርፍራፊ በጉርሻ መልክ እየገዙ ሕይዎታቸውን ለማቆየት ይፍገመገማሉ። በየዓመቱ በርሃብተኛው ስም በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ በዕርዳታ መልክ ከውጪ የሚለገሣቸው ወያኔዎች ገንዘቡን ወደ ውጪ አገሮች መልሰው እያሸሹ እነርሱ ቢሊዬኔሮች ሆነዋል፤ አሁንም ግን በርሃብተኛው ስም ከውጪ ዕርዳታ ይለመናል። ስለዚህ ኢትዮጵያውያን በማንኛውም የአገር ውስጥም ሆነ ዓለም-አቀፍ ድርጅት አማካይነት በርሃብተኞች ስም የሚደረገውን ዕርዳታ ፋይዳው ምን እንደሆነ ቆም ብለን ልናስብብት ይገባናል። ለወገን ደራሹ ወገን ነውና ለርሃብተኛ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ካለማንም ጣልቃ ገብነት በቀጥታ የዕርዳታ እጃችንን እንዘርጋላቸው። ሞረሽ-ወገኔም ለዚህ የተቀደሰ ተግባር አስፈላጊውን መሠናዶ ያደረገ ስለሆነ ዕርዳታችሁን በተገቢው ሁኔታ ለማድረስ ዝግጁዎች ነን፤ በአድራሻችን ጠይቁን። ሆኖም ምንጊዜም ማስታወስ ያለብን ዘለቄታዊ መፍትሔ የሚመጣበትን መንገድ ነው። የትግሬ-ወያኔ ካለ፣ ርሃብ እና ችጋር ይቀጥላል። ስለሆነም ለዚህ ዓይነቱ ሁኔታ የዳረገን የችግራችን ሁሉ ምንጭ የሆነው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ መወገድ አለበት። ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ በአንድነት ተንቀሳቅሰን የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ የሆነውን የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ለማስወገድ ቆርጠን እንነሣ።

ርሃብን ታሪክ ለማድረግ ቆርጠን እንነሣ!

የትግሬ-ወያኔን አገዛዝ በተባበረ ክንድ እናስወግድ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት            

ማክሰኞ ኅዳር ፲፬ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፫

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule