• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ስብስብ በሰሜን ካሊፎርኒያ

July 18, 2016 05:44 am by Editor 1 Comment

የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሸባሪውና በፋሽስቱ ወያኔ ቁጥጥር ሥር ወድቆ 25 የመከራና የፍዳ ዓመታትን አሳልፎ 26ኛውን ጀምሮዋል:: በዚህ ረጅም የመከራ ዓመታት አንድም ቀን ወያኔን ከመታገል የተቆጠበበት ጊዜ ግን አልነበረም:: ወያኔም ባደራጀው የመጨቆኛ መሳሪያው: በወታደሩ: በስለላ መረቡ እና በመሳሰሉት የዘረኝነት አገዛዙን ለማራዘምና ኢትዮጵያን የማጥፋት ተልኮውን ከፍጻሜ ለማድረስ ከዚያም የኔ የሚለው አዲስ አገር ለመመስረት ባለው እቅድ ሕዝባችን በዘርና በሃይማኖት ከፋፍሎ እርስ በርሳችን ለማባላት ያደረገው ሙከራ በሕዝባችን እምቢተኝነትና አገር ፍቅር ከመከፋፈል ይልቅ አንድነትን በመምርጡ ያቀደውን ከግብ ለማድረስ ቀላል አልሆነለትም::  ይህን ተልኮውን ከግብ ለማድርስ መጀመሪያ ዓማራውን ለይቶ በሌሎች ጎሳወች ለማጥቃት ሞከረ: አልሆን ሲለው ደረጃ በደረጃ ወደሌሎች ጎሳወችም ፊቱን አዞረ:: በመሆኑም ኦሮሞውን: አፋሩን: ሱማሌውን: ጋምቤላውን ወዘተ ማጥቃቱን ቀጠለ:: በእያንዳንዱ ጎሳ ላይ ያደረሰውን ግፍና በደል ከዚህ ላይ መዘርዘሩ ለቀባሪ ማርዳት ስለሚሆን እናልፈዋለን:: አንድ ነገር ሳንጠቅሰው ማለፍ የማንፈልገው ነገር: ባለፉት ሳምንታት በአዲስ አበባ መኖሪያ ቤታቸውን በላያቸው ላይ ያፈረሰባቸውን ወገኖቻችንን ነው:: መንግሥት በሕዝብ ተጠያቂ በሆነበት አገር: ክረምትና ብርድ ሲመጣ መንግሥት ቤት ለሌላቸውና በጎዳና ለሚያድሩ ጊዜአዊም ቢሆን መጠለያ አዘጋጅቶ ያስጠልላል:: ወያኔ ግን በክረምት ቤት ያላቸውን ሰዎች ቤታቸውን በላያቸው ላይ አፍርሶ ባልቴቶችን: አዛውንቶችን: ህፃናትንና ገና ሳምንት ያልሞላቸውን ጨቅሎችን ለዝናብና ለብርድ አጋልጦአቸዋል:: ይህን አይነት ጭካኔ ለመግለጥ ቃል ወይም ቃላት ፈልገን ለማግኝት አልቻልነም::

በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስም አርሶ አደር ወገኖቻችን አፈናቅሎ መሬታቸውን ለመዝረፍ ሲዘጋጅ የወላጆቻቸውን መሬት መነጠቅ በሰላማዊ መንገድ የተቃወሙ ወጣቶችን በጭካኔ ገደለ አሰረ አሰደደ:: ወያኔ ገና ሲጀምር ኢትዮጵያን አጥፍቶ አዲስ አገር ለመመስርት በነደፈው እቅድ መሰረት አዲስ አበባን በተቆጣጠረ ማግስት ከጎንደርና ከወሎ ለምና ሰፊ መሬት ወደትግራይ ከለለ:: የአካባቢውን ነዋሪና ተወላጅ የሆኑትን የወልቃይት: የጠገዴና የጠለምት ዓማራወችን ብትፈልጉ ትግሬነትንና የእኛን የበላይነት ተቀብላችሁ ኑሩ ካልሆነ መሬቱን እንጅ እናንተን አንፈልጋችሁም በማለት የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ዘመቻውን ቀጠለ:: የነዚህ ወረዳወች ነዋሪ የሆኑት ዓማራወችም ማንነታቸውን ለማስከበር መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አቁዋቁመው ራሱ ወያኔ ህገመንግስቴ በሚለው መንገድና ህጉን ተከትለው  ያደረጉትን ሙከራ እንደድፍረት በመቁጠር: የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ጎንደር ከተማ በሌሊት መጥቶ በማፈን: የገደለውን እየገደለ የያዘውንም እየያዘ ባለበት ጭቆናውና ግፉ ያንገፈገፈው የጎንደር ከተማና የአካባቢው ሕዝብ ሆ ብሎ ወጥቶ ወያኔን በመፋለም ላይ ይገኛል:: ወያኔም እንደለመደው ያለርህራሄ እየገደለ ነው ለመግደልም ተዘጋጅቶአል::

እኛ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ስብስብ በሰሜን ካሊፎርኒያ (ESNNC) አባላት የኢትዮጵያ ሕዝብ በጠቅላላ በተለይም ባሁኑ ጊዜ የጎንደር ሕዝብ ለዲሞክራሲያዊ መብቱና እንደሕዝብ ለመኖር ዋስትናው እያደረገ ያለውን ፍትሃዊ ትግል ሙሉ በሙሉ እንደግፋለን:: በምንችለው ሁሉ እገዛ ለማድረግም ዝግጁ ነን:: ቃልም እንገባለን:: ሌላውም ወገንና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ አሁኑኑ ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ ጥሪአችን እናስተላልፋለን::

የኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሉ መብቱን ያስክብራል ነፃነቱንም ይቀዳጃል!!

ETHIOPIAN SOCIETY NETWORK IN NORTH CALIFORNIA (ESNNC)
P.O. Box 612956
San Jose, CA. 95161
ethiopiansociety1@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. gud says

    July 23, 2016 04:43 pm at 4:43 pm

    Even failure has a name( check the Title $

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule