• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች

June 25, 2013 08:40 am by Editor Leave a Comment

በጅዳ መጠለያ አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች

በሪያድ “ኢትዮጵያዊቷ አሰሪዎቿን ለመበቀል የ6 አመት ህጻን ገደለች” የሳውዲ ጋዜጣ ዘገባ

ኮንትራት ስራ መጥተው ተፈናቅለው በጅዳ ቆንስል መጠለያ ከሚገኙት ቁጥራቸው ወደ 80 ከሚጠጉት እህቶች መካከል አንዷ እህት ከሁለት ቀናት በፊት  እሁድ ጁን 23 ቀን 2013 በጅዳ ቆንስል ግቢ በር  ራሷን አንቃ መግደሏ ታውቋል። ጉዳዩን ለማጣራት  የዚህችው እህት ሬሳ ከቦታው ሲነሳ በቦታው ነበሩ ወደ ተባሉት በጅዳ ቆንስል የዲያስፖራና ተፈናቃይ ዜጎች ሃላፊ ወደ ሆኑት ቆንሰል ሙንትሃን በስልክ ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም።

ስለተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት አካባቢው ከነበሩ የአይን እማኞች ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ሟች በኮንትራት ስራ ከወሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ መጥታ ከአመት በላይ ከሳውዲ አሰሪዎች ቤት ስትሰራ ከቆየች በኋላ በስራ ብዛት እግሯን ስላመማት ከስራ መፈናቀሏንና ወደ ጅዳ ቆንሰል መጠለያ መጠጋቷን ገልጸውልኛል። ያም ሆኖ በመጠለያው ትኖር የነበረች ይህችው እና የአእምሮ ሁከት ይስተዋልባት ያልነበረው እህት ባልታወቀ ምክንያት ሊነጋጋ ሲል ከቆንስሉ ግቢ በር ታንቃ መገኘቷን እንዳስደነገጣቸው እማኞች በእንባ እየታጠቡ አስረድተውኛል።

“መረጃ ለጋዜጠኛ ከሰጣችሁ ከመጠለያ ትባረራላችሁ!” የሚል ማስጠንቀቂያ ከመጠለያ ሃላፊዎች የተሰጣቸው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት እኒሁ የአይን እማኝ ተፈናቃዮች “ታመው የሚሰቃዩት እና እያበዱ የሚመጡት አህቶች ሁከትና ረብሻ የቀረነውን ሊያሳብደን ነው” ሲሉ ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ ገልጸውልኛል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሟች ማንነትና ተዛማጅ መረጃዎችን ለማሰባስብ ባደረግኩት ሙከራ ሟች ከመሞቷ ከአስር ቀን በፊት ከቆንሰሉ በመጠለያ ስትጨናነተቅ ያገኟት አንድ ኢትዮጵያዊ በጉዳዩ ተቆጭተው በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ያነሱትን ምስል አግኝቼ ተመልክቸዋለሁ።  በዚሁ ተንቀሳቃሽ ምሰል ቪዲዮ ላይ ሟች የመጣችው ከወሎ ሃይቅ አካባቢ መሆኑን ያስረዳች ሲሆን አንድ አመት ከሰባት ወር የሰራችበትን ደመወዝ አረቦች ሰጥተው ከመጠለያው ቢጥሏትም ገንዘቧ የት እንደ ገባ እንደማታውቅ በትካዜ ስትገልጽ ትታያለች። የምትፈልጊው ምንድን ነው ብለው ሲጠይቋትም ወደ ሃገሯን ለመግባት ብትፈልግም ሊሳካላት አለመቻሉን ተስፋ ቆርጣ ስታስረዳ የተቀረጸው ተንቀሳቃሽ  ምስል ያሳያል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ከበርካታ ወራት በፊት አንድ ወንድም ወደ ቆንሰሉ ግቢ እንዳይገባ ተከልከሎ በቆየበት በር ህይወቱ ማለፉ አይዘነጋም ። አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በቆንስሉ ግቢ አትገቢም ተብላ በመታገዷ ራሷን ስታ እንደነበር ይታወሳል። ይህችው እህት ከቆንሰሉ አካባቢ በሚገኝ ዛፍ ተንጠልጥላ ሶስት ቀናት ከቆየች በኋላ ያለቸበት ሁኔታ ታውቆ ከዛፉ እንድትወርድ ሲያግባቧት አሻፈረኝ በማለት ራሷን ከዛፉ ወደ መሬት ወርውራ መግደሏ ራሷን አጥፍታለች።

ከሳምንት በፊት ታዋቂው የሳውዲ እለታዊ ጋዜጣ ሳውዲ ጋዜጥ ተቡክ ተብሎ በሚታወቀው የሳውዲ ግዛት አንድ ኢትዮጵያዊት ራሷን መግደሏን ማስታወቁን በቁጥር 2 ዝንቅ መረጃየ ላይ ዘግቤው ነበር። በተመሳሳይ ዜና በዚያው ከሳምንት ካሚስ ምሽት ተብሎ በሚታወቅ አንድ የሳውዲ ግዛት አንዲት እህት “ራሷን ገድላለች” ተብሎ ሬሳዋን ወደ ሃገር ቤት ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆኑንም መረጃውን አቀብየ እንደነበር አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዋና ከተማዋ በሪያድ አንዲት ኢትዮጵያዊት የ26 አመት ወጣት የኮንትራት ሰራተኛ “በአሰሪዎቿ ደረሰብኝ የምትለውን አስከፊ እንግልት ለመበቀል የ6 አመት የአስሪዎቿን ሴት ህጻን መግደሏን አምናለች” የሚል አንገት ሰባሪ ዜና የተሰማው ትናንት ሲሆን ዛሬ የወጡት የሳውዲ ጋዜጦችም መረጃውን ይፋ አድረገዋል።

በኮንትራት ሰራተኞች ዙሪያ ሊሰሙት የሚዘገንን መረጃ መተላለፍ ከጀመረ አመታት የተቆጠረ ቢሆን መንግስት ትኩረት ስላልሰጠበት ችግሩ ሲባባስ ቆይቷል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ግን በስደቱ እየሆነ ላለው በሚመለከት ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ ዘጋቢ ፊልም ከታየ ወዲህ መንግስት ጉዳዩን ለመቆጣጠር ቁርጠኛ አቋም እንደሚወስድ ቃል መገባቱ አይዘነጋም።

ከኮንትራት ስራ ጋር በተያያዘ በሳውዲ አረቢያና ኢትዮጵያ መካከል የኮንትራት ሰራተኛን በሚመለከት የሁለትዮሽ ስምምነት እንደሌለ የጅዳው ቆንስል አቶ ዘነበ ከበደ በጀርመን ራዲዮ “እንወያይ” ፕሮግራም ተጋብዘው ባደረጉት ውይይት ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ከሶስት አመት በፊት በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 120 ሺህ ገደማ ይገመት የነበረ ሲሆን የኮንትራት ሰራተኞች ያለ ሁለትዮሽ ሰምምነት መምጣት ከጀመሩበት ካሳለፍነው ሶስት አመት ወዲህ የኢትዮጵያውያኑ ቁጥር 500 ሺህ መድረሱ ይገመታል።

(ነቢዩ ሲራክ በፌስቡክ ገጹ “ከዝንቅ መረጃ” አምዱ ካቀረበው የተወሰደ)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule