• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች የስደተኞችን ሻንጣ ዘረፉ!

February 9, 2015 07:21 am by Editor Leave a Comment

ከአንድ አመት በፊት የሳውዲ አረቢያ መንግስት በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ዜጎች  ግዛቱን  ለቀው እንዲወጡ ያስቀመጠው የግዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ አያሌ ኢትዮጵያውያን ጅዳ እና ሪያድ ከተማ ወደሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ መጉረፋቸው ይታወሳል።

eth emb saudi
የቆንስላው ጽ/ቤት ዲፕሎማቶችና ሠራተኞች

በወቅቱ ከነበረው ስርዓት አልበኝነት ህይወታቸውን ለመታደግ አቅሙ የቻለ ጎረምሳ ልብሶቹን በሻንጣ አጭቆ እግር አውጭኝ ሲል አይን ያልገለጹ ህጻናት ልጆቻቸውን በወጉ መሰብሰብ ያልቻሉ እናቶች ለክፉ ቀን ትሆነኛለች ብለው ገዝተው ያስቀመጡጥን ወርቅ እና የተለያዩ ጌጣጌጦቻቸውን የያዘች አነስተኛ ሻንጣ አንጠልጥለው ከቀማኞች ይታደገናል ወዳሉት በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ቅጠር ግቢ በማቅናት ለተውሰኑ ቀናቶች በመጠለል ሻንጣዎቻቸው በካርጎ ጭነት እንደሚላክ ቃል ተገብቶላቸው ብጣሽ  ጨርቅ እንኳን ሳይዙ  ባዶ እጃቸውን ወደ ሃገር ቤት  ማቅናታቸው ይነገራል።

በወቅቱ  በዚህ መልክ ወደ ቆንስላ ጽ/ቤት ቅጠር ግቢ የሚመጣውን  ወገን  ሃብትና ንበት በሃላፊነት ተረክቦ ወደ ሃገር መላክ የሚችል አካል ባለመኖሩ በጅዳ እና አካባቢው የሚኖሩ ታዋቂ ግለሰቦች  ከዲፕሎማቱ ጋር በመተባበር “ወገን ለወገን” የሚል አንድ ኮሚቴ በማዋቀር ኢትዮጵያኑ በሰላም ሃገር እንዲገቡ ሰፊ የማስተባበር ዘመቻ ይካሄድ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ይህ ኮሚቴ ወደ ሀገር ተመላሽ ወገኖችን ስምና አድራሻ እየመዝገበ በአደራ ተቀብሎ ከሚሰበስበው ንብረት ባሻገር በተለያዩ ግዜያት በአሰሪዎቻቸው ተደብድበው ተድፍረውና ደሞዛቸው ተነጥቆ ወደ ቆንስላው ቅጠር ግቢ የሚመጡ እህቶች ጉዳይ ተድበስብሶና በደልን ተሸክመው ወደ ሃገር መሸኝት እንደሌለባቸው በማመን የቆንስላው ባለስልጣናት በዚህ ዙሪያ አንድ አይነት ሚና መጫወት እንደሚገባቸው ያደርግ በነበረው ግፊት ኮሚቴው ከተሰጠው ሃላፊነትና ተግባር አፈንግጦል በሚል ቅሬታ በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎችና የአሰሪ እና ሰራተኛ ኤጀንሲ ደላሎች በተፈጠረው አለመግባባት  የማህበሩ መስራቾች  በቆንስላው ዲፕሎማቶች ትዕዛዝ ወደ ቆንስላው ግቢ እንዳይገቡ በመታገዳቸው የወገን ለወገን  ህልውና ገና ከጅምሩ በአደራ የተረከበውን ንብረት ሜዳ ላይ በትኖ ከስመ።

በዛኔው መንገደኛ እና ሻንጣ በተለያዩበት የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት  የጎዞ መስተንግዶ አሳዛኝ ድራማ በተፈጠረው ስርአት አልበኝነት የተጠቀሱትን ሻንጣዎች ከአደጋ ለመከላከል ባሉበት ሁኔታ ሸራ ለብሰው ቀሩ።  እህቶች ለአመታት ይደርስባቸው የነበረውን  እንደወላፈን የሚፋጅ የአረብ ወይዛዝርት ቁጣ እና ግልምጫ ተቋቁመው ባገኙት ደሞዝ  የሸመቱት ወርቅና የተለያየ ጌጣጌጦችን የያዙ ሻንጣዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ አገልግሎት አቆመ በሚል ሰንካላ ምክንያት ወደ ሃገር እንዳይልኩ በቆንስላው ዲፕሎማቶች እገዳ ተጣለበት። የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ቅጠር ግቢ ተቆልሎ የሚታየው ይህ  ሻንጣ ለወራት  ዝናብ እና ፀሃይ እይተፈራረቀበት ባለቤት አልባ ሆኖ ድፍን አመት ካስቆጠረ በኋላ  ሰሞኑን  በሻንጣዎቹ ላይ አስነዋሪና አሳዛኝ ተግባር መፈፀሙ ተስማ። በተለይ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ግቢ ውስጥ ከተደረደሩ ሻንጣዎች ውስጥ የአባዛኛው ቁልፍ መሰበሩን የሚናገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ሻንጣዎቹ ላይ የተፈፀመው ዘረፋ የዲፕሎማቱ እጅ እንዳለበት በመረጃ አስደገፈው ይናገራሉ። ድርጅታዊ ጉባኤ የምትለዋን ቃል እንደ  መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ማታ ማታ ያለወትሯቸው ቆንስላው ግቢ  የሚያድሩ  ከዲፕሎማቱ ጋር የቀርብ ግንኙነት ያላቸው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አባላት ግንባር ቀደም የዚህ ወንጀል ተዋናይ ሳይሆኑ እንደማይቀር ይጠረጠራል። እስክሁን ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ የተለያዩ ሻንጣዎች ቆልፍ እየተሰበረ በጥንቃቄ ብርበራ እንደተካሄደበት በተጨባጭ፡ ማረጋገጥ ተችሏል።

ይህ በዚህ እንዳለ  ሰሞኑን የሰማያዊ  “ማንዋል” ፓስፖርት የአገልግሎት ዘመን ማብቃቱን ተከትሎ ፓስፖርት ለማስለወጥና ለማሳደስ  የጅዳ ቆንስላ  ጽ/ቤት በተከስተው የባለጉዳዩች መጨናነቅ ዲፕሎማቱ  ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ቆንስላ ጽ/ቤት ለሚገባው ተስተናጋጅ የ3 ወር እና ከዚያ በላይ ቀጠሮ እየተሰጠው ሲሸኝ  በሌላ አቅጣጫ ለሚስተናገድ  ባለጉዳይ ከ5 ቀን ባልበለጠ ግዜ ውስጥ ሁሉም ነገር እንዲሚያልቅለት የሚናገሩ ባለጉዳዩች ዲፕሎማቱ  እየሰጡ ባለው  በሙስና የነቀዘ አገልግሎት ክፉኛ መማረራቸውን ይናገራሉ፡፡

በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ውስጥ የበጎ ፈቃድ አገልጋዩች በሚል ሽፋን ከዲፕሎማቱ ጋር ጥብቅ ቁረኝት ያላቸው የዚህ ወንጀል ተባባሪ ደላሎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።  በዚህ ዙሪያ ለማነጋገር በቅርቡ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ሃላፊ ሆነው የተሾሙትን አምባሳደር ውበሸትንም  ሆነ ዲፕሎማት ሼሪፍ ኬሬን በአካል  ለማገኘት ያደረኩት ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

(Ethiopian Hagere Jed Bewadi ለጎልጉል የላኩት – ፎቶ በቆንስላ ቅጠር ግቢ የተቆለለው ሻንጣ)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule