• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት 3ሺ ህጻናትን በትኖ ሊዘጋ ነው!

June 12, 2014 06:01 am by Editor Leave a Comment

በስደት አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ህጻናት በተመጣጣኝ ዋጋ ተቀብሎ በማስተማር ከፈተኛ ስተዋጾ እያበረከተ የሚገኘው በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ላለትፉት ሁለት አስርት አመታት ሪያድ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚመኩበት እና የሚኮሩበት ተቋም ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ በወላጆች እና በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች መሃከል በተፈጠረው አለመግባባት ት/ቤቱ እንደተቛም ህልውናውን ጠብቆ ወደፊት መቀጠል እንደተሳነው የሚናገሩ ምንጮች።  ሰሞኑን የት/ቤቱ የኪራይ ዘመን እና የት/ቤቱ ህጋዊ  ፈቃድ የግዜ ገደብ በመጠናቀቁን ተከትሎ በተቋሙ ህልውና ላይ የጋረጠው አደጋ አሳስቢ መሆኑን በመጥቀስ ከወራት በፊት በማን አለብኝነት ት/ቤቱን በበላይነት ተቆጣጥረው እንዳሻቸው ሲዘውሩት የከረሙት በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሹማምንቶች በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ተከሰቱ የተባሉትን የተወሳሰቡ ችገሮች ደረጃ በደረጃ መቅረፍ ተስኗቸው እራስቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን የፌታችን አርብ ጁን 13 2014 አስቸኳይ የወላጆች ስብሰባ መጥራታቸውን ይገልጻሉ።

በአምባሳደር መሃመድ ሃሰን አቀነባሪነት በዲያስፖራው ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር አስፈጻሚነት ወላጆች በት/ቤቱ ጉዳይ አንድነት እንዳይፈጥሩ በብሄር ከፋፍለው በማጋጨት ዲፕሎማቱ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ በሾማቸው የቦርድ አባላት ያለምንም ኦዴት የት/ቤቱ ገቢ እና ወጪው ሳይታወቅ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ «ሪያል» ዘረፋ እንደተፈፀመበት የሚናገሩ እንዚህ ምንጮች ዛሬ ት/ቤቱ አመታዊ ኪራይ መክፈል ተስኖት ጉዳዩን ወደ ወላጆች ማምጣት እራስን ከተጠያቂነት ለማዳን ከሚደረግ እሩጫ ተለይቶ የማይታይ መሆኑንን ይናገራሉ። 3000 የሚሆኑ የስደተኛውን ማህበረሰብ ልጆች እንደሚያስተናገድ የሚነገርለት ይህ ት/ቤት ከእያንዳንዱ ተማሪ በወር እስከ 3 መቶ ሪያል በነፍስ ወከፍ እንደሚሰበስብ የሚገልጹት ውስጥ አዋቂዎች የት/ቤቱ ወረሃዊው ገቢ ብቻ ት/ቤቱ የራሱ የሆነ ህንጻ በማስገንባት ከኪራይ ነጻ መሆን ያስችለው እንደነበር አስታውሰው ከባለቤቱ በላይ አዋቂ ሆነው ት/ቤቱን በሞግዜትነት በሃይል ሲያስተዳደሩ የከረሙት እነዚህ ዲፕሎማቶች የት/ቤቱ ወላጆች እና የአካባቢው ማህበረሰብ በአንድ ወቅት ት/ቤቱን ከኪራይ ጥገኝነት ለመላቀቅ የራሴ ነው ብለው የሚመኩበትን ት/ቤት ለማስገንባት እንቅስቃሴ ላይ እያሉ በአምባሳደር መሃመድ ሃስን ትዕዛዝ መታገዳቸውን ይናገራሉ።

cominty 12ይህ በዚህ እንዳለ ለዚህ ተግባር የሚውል ከወላጆች ከአካባቢው ማህበረሰብ  ለመሰብሰብ ታቅዶ ከነበረው 10 ሚልዮን ሪያል «በአሁኑ የኢትዮጵያ ምንዛሪ ከ50 ሚልዮን የሚበልጥ ብር» ውስጥ ግማሽ ያህሉ መሰብሰቡን የሚያስታውሱ ወላጆች ለገዘቡ ደህነት ሲባል በወቅቱ  በአምባስደር መሃመድ ሃሰን ስም ከ 3 አመት በፌት አንድ ሳአውዲ አረቢያ የሚገኝ ባንክ ቤት ገቢ መሆኑን ይገልጻሉ። ዛሬ ት/ቤቱ እንደዚህ አይነት የተወሳሰቡ ችገሮች ውስጥ ባለበት ወቅት አመታዊ የኪራይ ገንዘብ አጥቶ አደጋ ላይ መውደቁን ለወላጆች ለማርዳት ዲፕሎማቱ እያሰሙ ያለው ጩሀት ተቀባይነት የሌለው እና ከ3000 በላይ የሆኑ ህጻናትን ሜዳ ላይ በትኖ ት/ቤቱን ለመዝጋት የሚደረገው ጥረት ከጀርባው  ድብቅ አጀንዳ ያለው መሆኑ ይነገራል።

ከዚህ ባሻገር ዘንድሮ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያወጣውን አዋጅ ለመተግበር  ማንኛውም መምሀር የመኖሪያ ፈቃዱ በት/ቤቱ ሰር እንዲሆን ለማስቻል ት/ቤቱን በእጅ አዙር በባለቤትነት የተቆጣጠሩት ዲፕሎማቶች በጀመሩት ዘመቻ ከት/ቤቱ ካዝና አህዙ በትክከል የማይታወቅ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ያለምንም ማስረጃ ህገወጥ በሆነ መንገድ ወጪ መደረጉን የሚገልጹት ለጉዳይ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለመምህራኑ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ተመድቦል ተብሎ ለይስሙላ በቦርድ አባላቱ ከተነገረው 70 ሺህ ሪያል እና ለኮሚኒቲው ካፍቴርያ ድጎማ በብደር መልክ ተሰጥቷል ተብሎ ከት/ቤቱ ካዝና በሚስጠር ውጪ ከተድረገው ከ2 መቶ ዘጠናሺህ ሪያል ወይም «ከግማሽ ሚልዮን ብር» በተጨማሪ ቁጥሩ በወል የማይታውቅ ጥሬ ገንዘብ የት እንደገባ እና ለምን አገልግሎት እንደዋለ በግልጽ እንደማይታወቅ  ይገልጻሉ።

ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በተለያዩ ዝቅተኛ ስራዎች ላይ ተመደበው ከሚሰሩ የውጭ ሃገር ዜጎች ያነስ ደሞዝ እይተከፈላቸው የስደት አለሙን ህይወታቸውን ለማሸነፍ የሚባዝኑት የት/ቤቱ መምህራን እና ሰራተኞች የመኖሪያ ፈቃዶቻቸውን በት/ቤቱ ስር ለማድረግ ከያንዳንዱ መመህራን የወር ደሞዝ እስከ ሁለትሺህ እና ከዛ በላይ መቆረጡን ያረጋገጡ ምንጮች  መምህራኑ ህጋዊ ለመሆን ባላቸው ጉጉት ከሆድ ከማታልፍ ደሞዛቸው በየወሩ የህን ያህል ከፈሉ እይተባለ የሚጣልባቸው እዳ ከወር ደሞዛቸው ዝቅተኝነት ጋር ተዳምሮ በኖራቸው ያስከተለውን ቀውስ ለመታደግ ተጨማሪ ገቢ ፍለጋ በትርፍ ግዜያቸው የተለያዩ ተማሪዎችን በክፍያ በማስጠናት አሊያም ያለ እረፍት በተለያዩ የጉለብት ስራዎች ላይ ለምሰማራት መገደዳቸው በት/ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደት ላይ አሉታዊ ተፀእኖ በማሳደሩ ወላጆች በት/ቤቱ ላይ የነበራቸው ተስፋ መጨለሙ ይነገራል።

ይህ በዚህ እንዳለ የሳውዲ አረቢያ ት/ሚንስቴር መ/ቤት ቀደም ብሎ ማንኛውም  ተቋም በስሩ ት/ቤቶችን መከፈት ከፈለገ ጥራቱን የጠበቀ በሳውዲ አረቢያ የት/ሚ/ር ህግ መሰረት የተለያዩ ማስፈርቶችን ያሞላ ከኪራይ ነጻ የሆነ የግል ህንጻ ሊኖረው እንደሚገባ ባወጣው መመሪያ መስረት በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒ ት/ቤት ዲዛይኑ ለመጋዘን መዋል የሚገባው የመጸዳጃ እና የተማሪ እረፍት ቦታዎችን ያላሞላ ከመሆኑም በላይ ህጻናቱ ይማሩበታል የሚባለው ህንጻ በማርጀቱ በተማሪዎቹ ህይወት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አሰቃቂ አደጋ ከግመት በማስገባት የሳውዲ እሳት አደጋ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ከፍል ከሳውዲ ትምህርት ሚ/ር ጋር በመተባበር የት/ቤቱ ፈቃድ እንዲሰረዝ መወሰናቸውን ተከትሎ ት/ቤቱ በቀጣይ የትምህረት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱን መቀጠል እንደማይችል ከት/ቤቱ የሚወጡ ሚስጥራዊ መረጃዎች ያመለክታሉ ። (Ethiopian Hagere ጂዳ በዋዲ ለጎልጉል የላኩት)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule