• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢህአዴግ በፖለቲካ ወለምታ ውስጥ!!

November 14, 2012 08:59 am by Editor Leave a Comment

ኢህአዴግ በ“ፖለቲካ ወለምታ” ውስጥ እንደሚገኝ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የኢህአዴግ ዲፕሎማት ለጎልጉል ተናገሩ። በከፊል ኢህአዴግን የተለዩ የሚስሉት ዲፕሎማት በጎልጉል የቅርብ ሰው አማካይነት ድምጻቸው ሳይቀረጽ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት የተፈጠረው የፖለቲካ ወለምታ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል አመልክተዋል። የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በመካከለኛ አመራሩ ውስጥ የመጠራጠር ስሜት መፈጠሩን በፓርቲ ግምገማ ላይ በግልጽ መናገራቸው የዲፕሎማቱን አስተያየት የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል።

የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የአቶ መለስን ሞት ደብቀው በመያዝና ማስተባበያ በመስጠት ጊዜ የወሰዱት ይኸው የተባለው የፖለቲካ ወለምታ እንዳይፈጠር ለማድረግ በማሰብ እንደነበር ዲፕሎማቱ ያስታውሳሉ። ይሁን እንጂ አቶ መለስ ሁሉንም ጉዳይና ሃላፊነት ብቻቸውን ይዘውት ስለነበር በድንገት ማለፋቸው ፓርቲው ውስጥ አሁን በየደረጃው የሚታየው የመተርተር አደጋ መከላከል ግን አልተቻለም።

የፖለቲካ ወለምታ ስለመከሰቱ ማንም ማስተባበያ ሊያቀርብ አይችልም የሚሉት ዲፕሎማት በእርሳቸው እይታና ባላቸው መረጃ መሰረት ድርጅትን መክዳት፣ ድርሻዬ በሚል ገንዘብ ማሰባሰብ፣ ቤተሰብን በተለያዩ ምክንያቶች ማሸሽ፣ በቁልፍ የመከላከያ ሃላፊዎች ላይ ማነጣጠር፣ በግምገማ  ስም ካድሬውን ማመስ፣ በስልጠና ስም የበታች አመራሮችን መደለል፣ ከሁሉም በላይ ማንኛውም ውሳኔ ሲወሰን በተናጠል እንዳይሆን የሚከለክል አሰራር መከተል የመሳሰሉት ተፈጠረ ለተባለው “ወለምታ” ዋና መግለጫዎች ናቸው።

ፓርቲያቸው ኢህአዴግ የመለሰን ምስል እየለጠፈ “የታላቁን መሪ ውርስ ሳይበረዝ እናስቀጥላለን” የሚለው ውሸት እንደሆነ በመግለጽ ተጨማሪ ማሳያ የሚያክሉት ዲፕሎማቱ፣ “ይህ ሁሉ ግርግር ካድሬውን ንዶታል፣ የምንቀራረብ ዲፕሎማቶችና ባለስልጣናት የምንቀያረውን መልዕክት ህዝብ ቢሰማ በመሪዎቹ ያፍራል። ካድሬውም ራሱን ይጠላ ነበር” በማለት ተናግረዋል።

“ዲፕሎማቶች እርስ በርሳችን ሃሜት ከጀመርን ቆይተናል” በማለት ሃሜት አንዱ የፖለቲካ ወለምታ ማሳያ እንደሆነ የሚናገሩት የኢህአዴግ ሰው፣ መለስን ታላቅ መሪ እያሉ የጋራ አመራር መሰየማቸው በካድሬውና በፓርቲው የተለያዩ አመራሮች ዘንድ ማፌዣ እንደሆነ ይጠቁማሉ። ሲያብራሩም “የመለስ መስመር ሳይበረዝ እናስቀጥላለን እያሉ እየማሉ አገሪቱ በጋራ አመራር እንደምትመራ ይፋ ማድረጋቸው አቶ መለስ በጋራ አመራር የማያምኑ፣ አምባገነን፣ የስልጣን ጥመኛ፣ የዲሞክራሲ ባህል የሌላቸው፣ ከዚህ ቀደም የተቃወሙዋቸው የሚሉት ሁሉ ትክክል እንደሆነ መቀበልና አስተዳደራዊ መልካቸው የተበላሸ እንደነበር የማወጅ ያህል ነው” ብለዋል፡፡

ኢህአዴግ መለስን በአደባባይ እያወገዘ እንዳለ ሁሉም እንደሚረዳ ማረጋገጫው በእህት ፓርቲዎች ውስጥ በተካሄደው ግምገማ ከፍተኛ ባለስልጣናት ውስጣዊ ችግር እንዳለባቸው ማስታወቃቸው እንደሆነ ያመለከቱት እኚሁ ዲፕሎማት በቅርቡ “በታሪክ አጋጣሚ ተሾምኩ” በማለት ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተመደቡትን አቶ ደመቀ መኮንን የተናገሩትን ያጣቅሳሉ።

የብአዴን ሊቀ መንበር አቶ ደመቀ ባህር ዳር በተካሄደው የድርጅት ጉባዔ ላይ የአቶ መለስ ህልፈትን ተከትሎ ተፈጠረ የሚባለውን የፕሮፖጋንዳ መነቃቃት “የዘመቻ ውጤት” ብለውታል። አያይዘውም “የልማት ሰራዊት መገንባትና ማደራጅት አልተቻለም” በማለት የሚሰራውንና ተሰራ የተባለውን ስራ “ሸንኮራ ቆረጣ” እንዳስመሰሉት አስተያየት ሰጪው ይናገራሉ።በማያያዝም የክልሉ ምክትል ሊቀመንበር “የመጠራጠር መንፈስ አለ” በማለት ስጋታቸውን መግለጻቸውን ያክልሉ። አቶ በረከትም ተመሳሳይ አስተያየት መስጠታቸውን ጨምረው ገለጸዋል።አንዳንድ የስራ ባልደረቦቻቸው እንደገለጹላቸው ከሆነ በቅርቡ ብወዛ፣ ሹም ሽርና በመተካካት ስም ማስወገድ እንደሚደረግ በማውሳት አስተያየታቸውን የሰጡት የኢህአዴግ ሰው፣ በደቡብ ክልል ኦህዴድ ውስጥ የተፈጠረው አይነት ችግር ሊፈጠር ይችላል የሚል ቅድመ ጥናት መደረጉን ይፋ አድርገዋል። ለዚህም ይመስላል በሙስና ተወንጅለው ለዓመታት ከታሰሩ በኋላ በነጻ የተለቀቁት አባተ ኪሾን መልሶ ለመሾም የማግባባት ስራ (ሎቢ) ተጀምሯል ብለዋል።

“ወደ አገር ቤት ይመለሳሉ?” ተብለው ለተጠየቁት ሲመልሱ “በተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆነ በዳያስፖራ ዘንድ ለኢህአዴግ ሰዎች የሚሆን ቦታ ስለመኖሩ ሰምተው” እንደማያውቁ በመጠቆም ለመመለስም ሆነ ለመቅረት ስጋት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ “ከተቃዋሚዎች በኩል ሁሉንም የኢህአዴግ ሰዎች በአንድነት በመፈረጅ “ወዮልህ” የሚሉ ማስጠንቀቂያዎች መብዛታቸው ለስርዓቱ ኃይል  እንደሆነው” አመለክተው “ወለምታው እኔንም ይመለከተኛል። እኔም እንደ ባልደረቦቼ ወጌሻ ያስፈልገኛል” የሚል መልስ ሰጥተዋል። አያይዘውም የተፈጠረውን ወለምታ ለመጠቀም ምላጭ ፖለቲከኛ መሆን እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ምላጭ ፖለቲከኞች ምን መምሰል እንዳለባቸው ግን አላብራሩም። አቶ መለስን አስመልክቶ ያደረግነውን ቃለ ምልልስ በቀጣይ እናቀርባለን።

ጎልጉል ባለው መረጃ በደቡብ ክልል አብላጫ ቁጥር ያላቸው የሲዳማ ብሄረሰብ ክፍሎች አሁን በቡና ንግድ የተሰማሩትን የቀድሞውን ፕሬዚዳንት አቶ አባተ ኪሾን ይቀበላል። በክልሉ ከሲዳማ ብሄረሰብ ውጪ ፕሬዚዳንት ለማድረግ እንደማይሞከር በተለያዩ ጊዜያት ስለክልሉ ሲዘገብ የተጠቀሰ ጉዳይ ነው።

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ባለፈው አርብ በመስከረም ወር ማድረግ የሚገባውን የመጀመሪያ ሩብ አመት ግምገማ በማካሄድ ያሳለፈው ውሳኔ በድርጅቱ ውስጥ አለ የተባለውን የፖለቲካ ወለምታ የሚያሳይ እንደሆነ ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ አስታውቀዋል። የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ በክልል ደረጃ አሉ የተባሉትን ችግሮች አድበስብሶ በጥንካሬ ከገመገመ በኋላ “የክረምቱ ስራ ስላለቀ፣ የበጋው ስራ ባስቸኳይ እንዲጀመር” ሲል የፖለቲካ ውሳኔ ማውረዱን ይፋ አድርጓል። አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ክረምቱ ካለቀ ከሶስት ወር በኋላ “የበጋው ስራ ይጀመር፣ ክረምቱ አልቋል” የሚል ውሳኔ ማሳለፉ ከወለምታም በላይ ነው።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://staging.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule