• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአዲስ አበባውና የአሜሪካው ኢህአዴግ ቢሮ አይተዋወቁም

March 21, 2016 07:02 am by Editor 2 Comments

በሳምንቱ አጋማሽ የተሰማውን ዜና ያደመጡ፣ ከቅርብ ሆነው የሚከታተሉና ለጉዳዩ የቀረቡ እንደሚሉት የአዲስ አበባው ኢህአዴግና አሜሪካ ያለው የኢህአዴግ ቢሮ የማይተዋወቁበት ደረጃ ደርሰዋል። ኢህአዴግ በደብዳቤ የተረከባቸውን ስደተኞች በብሔር መትሮ “ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም” በሚል ወደ አሜሪካ መመለሱ የእለት ጉርስና የዘመን መሻገሪያ ድርጎ የምትመድበውን አሜሪካንን አስቆጥቶ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል።

ኢህአዴግ እንደ “አሸባሪ” የፊጥኝ አስሮ ከፍሎሪዳ ጠቅላይ ግዛት ማያሚ እስር ቤት ወደ ኢትዮጵያ የወሰዳቸው ወገኖች ከአገራቸው የወጡበትን ጊዜ ሳይቆጥር አሜሪካ ለመድረስ ብቻ እስከ አስራ አራት ወራት ፈጅቶባቸዋል። ስደተኞቹ በብራዚል፣ በኮሎምቢያ ጫካ ፣ በፓናማ ወንዝ አሳብረው፣ በሜክሲኮና በድምሩ 16 የሚደርሱ አገራትን አልፈው ነበር አሜሪካ ጥገኝነት የጠየቁት። እነዚህ ወገኖች ህጉ ከሚፈቅደው ውጪ ከስድስት ወር በላይ በፍሎሪዳ ጠቅላይ ግዛት ማያሚ እስር ቤት መቆየታቸውን ጎልጉል መዘገቡ ይታወቃል። በአስራ አንደኛው ሰዓት ለአቶ ኦባንግ ሜቶ የላኩት “የድረሱልን” ደብዳቤ ነገሩን ሁሉ ይፋ አደረገው።

በዚህ መካከል ነበር አቶ ግርማ ብሩ የሚመሩት የህወሃት የአሜሪካ ቢሮ ስደተኞቹን “ዜጎቼ ናቸው” ብሎ ጠርቶ ሲያበቃ፣ ስም ዘርዝሮ፣ ቢመለሱ ምንም አይሆኑም፣ ምንም አይደርስባቸውም፣ ሰላማዊ ኑሮ መኖር ይችላሉ፣ ወዘተ በማለት ደብዳቤና አዘጋጅቶ በሰጠው የመጓጓዣ ሰነድ አማካይነት ወጣቶቹ ተላልፈው ተሰጥተውታል።

ጎልጉል ከተመላሾች ባገኘው መረጃ መሰረት፣ የአሜሪካ ልዩ የፖሊስ አባላት ማያሚ እስር ቤት ሌሊት መጡ፤ ተነሱ አሏቸው፤ እጃቸውን አሰሩ፤ በመኪና ተጫኑ። አቅራቢያ ባለ አየር ማረፊያ በተዘጋጀ አነስተኛ የግል አውሮፕላን ተጫኑ። ከአስራ አንድ ሰዓት በላይ በረራ ካደረጉ በኋላ ሴኔጋል ዳካር አረፉ። አውሮፕላንዋ ነዳጅ ስትሞላ እነሱም ውሃና የሚቀመስ አግኝተው ባሉበት ቆዩ። ከዚያም ወደ “አገራቸው” ኢትዮጵያ አቀኑ። አዲስ አበባ ሲደርሱ የህወሃት ነፍጥ አንጋቾች ተረከቧቸው። ጉዞው በህወሃት አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ለጉዞው አሜሪካኖቹ ከፍተኛ ወጪ አውጥተዋል።

ርክክቡ ከተጠናቀቀ በኋላ ሁሉም በየተራ ቃለመጠይቅ ተደረገላቸው። መከረኛው የብሔር ጥያቄ ቀረበ። ጠያቂዎቹ የህወሃት ሰዎች የብሄር ጥያቄውን ተከትሎ ወጣቶቹን እንደ እህል በዘር መደቧቸው። እናትና አባታቸው የኢትዮጵያ ሶማሌና አማራ፣ ሃረሪና ኦሮሞ የሆኑት ሁለቱ፣ እንዲሁም ሁለት የጅጅጋ ነዋሪዎችና የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች እና ሙሉ በሙሉ የሃረሪ ተወላጅ እንደሆነ የተናገረውን ጨምሮ አምስቱ ተመርጠው “አማርኛ በደንብ ትችላላችሁ ግን ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም” ተብለው ወደ አሜሪካ እንደተመለሱ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባው አሜሪካ ኤምባሲ ከከፍተኛ የህወሃት መሪዎች ጋር ዘለግ ያለ ንትርክ አካሂደዋል። ራሱ “ዜጎቼ” ብሎ ደብዳቤ በመጻፍ ተላልፈው እንዲሰጡት ጠይቆ ሲያበቃ፣ ራሱ የጉዞ ሰነድ አዘጋጅቶ፣ ራሱ እስር ቤት ድረስ ሄዶ እጅና እግር አስሮ፣ ራሱ ነፍጥ አንጋች አሰልፎ አቀባበል አድርጎ፣ ከአንድ የትግራይ ልጅ በስተቀር ሁሉንም በአማርኛ አነጋግሮ በስተመጨረሻ አምስቱን “ኢትዮጵያውያን አይደላችሁም” ብሎ ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ ማድረጉ “አውራ ፓርቲ” የሚባለውን ኢህአዴግን ቅሌት ውስጥ እንደጣለው ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩ አመልክተዋል።

“አሜሪካ ያለው ኢህአዴግና አዲስ አበባ ያለው ኢህአዴግ የማይተዋውቁበት ደርጃ ደርሰዋል” ሲሉ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል የአሜሪካ ዘጋቢ ገልጸዋል። አክለውም “ይህ የሚያሳየው ድርጅቱ በተግባር መዋቀሩ የተሽመደመደ፣ ማዕከላዊነት የሚባል ነገር መጥፋቱን፣ ሁሉም በየፊናው ሩጫ መጀመሩን፣ እንደ አገር የክስረት ማመላከቻ ነው” ሲሉ በተፈጸመው ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።deportee letter

ከተመለሱት መካከል ያነጋገሯቸው እንዳሉ ያስታወቁት ኦባንግ፤ ካሁን በኋላ ልጆቹ እስር ቤት የሚቆዩበት አንዳችም ምክንያት ባለመኖሩ እንደሚፈቱ ጠቁመዋል።

“ኑሮዬ ሳይስተካከል የት እንዳለሁ እንኳን ለቤተሰቦቼ አልገለጽኩም። እናትና አባቴ ልሙት፣ ልኑር አያውቁም፤ ከተለየኋቸው ጊዜ ጀምሮ ስልክ ሳልደውል አራት አመት ከአስራ አንድ ወራት አልፈውኛል” በሚል የድረሱልኝ ጥያቄ ጨምሮ ዘጠኙን ወገኖች ለማስፈታት አቶ ኦባንግ ባለቀ ሰዓት መረጃው ደርሷቸው የሚቻላቸውን ሁሉ ጥረው ነበር። “የድረሱልን ጥሪውን እንደተቀበልኩ ወዲያውኑ ስደተኞቹን የሚወክል ጠበቃ ያዝኩ። የወጣቶቹ ከስድስት ወር በላይ መታሰር ከህግ አንጻር አግባብ ባለመሆኑና ስደተኞቹ ሊመለሱ እንደማይገባ ለማውቃቸው እንደራሴዎችና ሴናተሮች በማስረዳት የእስር ውሳኔ ላስተላለፉት ዳኛ ደብዳቤ ሊላክ የሰዓታት ዕድሜ ሲቀር ነበር የመላካቸውን ጉዳይ የሰማሁት” በሚል ነበር ሃዘናቸውን የገለጹት።

ቀደም ሲል በአስራ አንደኛው ሰዓት ጉዳዩን የያዘው ጠበቃ የልጆቹን መመለስ ሲሰማ መገረሙን፤ ሌሎችም አካላት በተመሳሳይ በሰሙት ሁኔታ በኢትዮጵያ በመንግሥት ደረጃ ያለው ሥርዓት አልበኝነት ያስደነገጣቸው መሆኑን ያመለከቱት ኦባንግ፣ ጉዳዩ ህጉ በሚያዝው መሰረት እንደሚከናወን አመልክተዋል። በርግጠኛነት ልጆቹ በቅርቡ እንደሚፈቱም አክለዋል። በሌላ መልኩ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በሚገኙ እስር ቤቶች ተመሳሳይ የድረሱልኝ ጥሪ ያሰሙ ወገኖች መኖራቸውንና እነዚህን ወገኖች ለመርዳት በሳቸው በኩል የሚደረገውን ሁሉ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሊቢያ ዜጎች ስልክ ሲደውሉ ጆሮዋቸው ላይ በመዝጋት፣ ስልክ እንዳይደውሉ በመከልከል፣ በተለያዩ አረብ አገራት እህቶቻችን ላይ ሰቃይ ሲደርስና ሲገደሉ፣ በደቡብ አፍሪቃ በዜጎች ላይ ተመሳሳይ አደጋ ሲደርስ ህወሃት ያሳየውን ቸልተኛነት ያስታወሱት ኦባንግ “ብሔርን፣ ዘርን፣ ወገንን፣ … ለይቶ የሚፈጸሙ ጥፋቶች ፈር እየለቀቁ የማንመልሰው ደረጃ ከመድረሳቸው በፊት ለናርቃቸው ይገባል” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። ዜጎች ከዘር ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ በመስጠት እርስ በርስ መደጋገፍ ላይ እንዲያተኩሩም አሳስበዋል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://staging.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. moon says

    March 23, 2016 08:18 am at 8:18 am

    What do you really need .
    If accepted , you say they were sent to woyane
    If deported , you say they are denied access to ETHIOPIA . Confused guys !

    Reply
  2. Yikir says

    March 29, 2016 10:41 pm at 10:41 pm

    Enem ende h/aram 1 ayin mehone inji ethiopiawi negni.A A YALEW “WEYANE “SIHON U S A YALEW KETARIK ANITSAR TINISH MORAL YELELEW BANDA YE ETHIOPIA EMBASSY NEW. 100% ethiopian yemiwekilu embasiwoch bemulu 666 nachew.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule