• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢህአዴግ ከምርጫ ቦርድ ጋር “የምርጫ ግብረ ኃይል” ጥርነፋ እያካሄደ ነው

January 13, 2015 06:32 pm by Editor 1 Comment

ብአዴን/ኢህአዴግ በምስራቅ ጎጃም ዞን “የምርጫ ግብረ ኃይል” በሚል አደረጃጀት የምርጫ ቦርድን ስራ እየሰራ መሆኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ፀኃፊ አቶ ሳሙኤል አወቀ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የብአዴን ካድሬዎች በምስራቅ ጎጃም በተለይም ደብረማርቆስ ከተማ ላይ ቤት ለቤት እየዞሩ ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ በሚቀሰቅሱበት ወቅት የምርጫ ካርድ አልወስድም የሚሉ ዜጎችን “አልወስድም ስትል ፈርም” እያሉ እያወከቡ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ “የምርጫ ግብረ ኃይል” በተሰኘው መዋቅር የምርጫ ካርድ እንደማይወስዱና እንደማይፈርሙ ስለሚገልጹት ዜጎች ከሌሎች መረጃ በመጠየቅ ለማስፈራራት እየሞከሩ መሆንን ገልጸውልናል፡፡

ከዚህም ባሻገር ካድሬዎቹ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ለምርጫ ጽ/ቤት አቅጣጫ እንደሚሰጡ፣ የምዝገባ ሰነዶችም በእነሱ እጅ እንደሆኑና የምዝገባ ሂደቱን እያከናወኑ እንደሚገኙ ተግልጾአል፡፡ ካርድ የማቅረብና የመመዝገብ ኃላፊነት የምርጫ ቦርድ ስራ ሆኖ እያለ ሞጣ አካባቢ የምርጫ ካርድ አለቀ ሲባል በብአዴን ካድሬዎች ትዕዛዝ ከጎዛመን ወረዳ የምርጫ ካርድ ወደ ሞጣ መላኩን በመጥቀስ ብአዴን/ኢህአዴግ ምርጫ ቦርድን ተክቶ እየሰራ መሆኑን ኃላፊ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል የብአዴን ካድሬዎች ሰማያዊ፣ አንድነትና መኢአድ ከፓርቲነት ተሰርዘዋል እያሉ እያስወሩ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን በተለይ በየገጠሩ “ሰማያዊ ፓርቲ እውቅና የለውም፡፡ እውቅና ከሌላቸው ሌሎች ፓርቲዎች ጋርም ህገ-ወጥ ትብብር ፈጥሮ እየሰራ ነው፡፡ በመሆኑም ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ከመስራታችሁ በፊት ህገ-ወጥ መሆኑን ልታውቁት ይገባል፡፡ ራሳችሁን ችግር ላይ እንዳትጥሉ” እያሉ እየቀሰቀሱ መሆኑን አቶ ሳሙኤል አወቀ ገልጸዋል፡፡ በተለይ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ዘመቻ ተከፍቷል ያሉት ፀኃፊው ብአዴኖች በከተማና በገጠር በሚኖረው ህዝብ ውዥንብር ለመንዛት እየጣሩ እንደሆነ ታዝበናል ብለዋል፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ ፌስቡክ ገጽ)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. sayint says

    January 15, 2015 03:28 am at 3:28 am

    abo deg adergu beadinoch-diros ye agasses sibisib yehonut-andinet, semayawi ena me ead amarawin ende feres lemegaleb yifeligalu-enasa enjam wegidu linlachew yigebal. rbana besoch ena ye hager shekimoch! be andinet sim ke eze befet be amaraw biher sitnegidu neber! ke ahun bewala dar yizachu asalafe hun!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule