• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል

July 8, 2014 12:01 am by Editor Leave a Comment

የአቶ ጌታቸው ረዳን የአማራ ነገድ ጋዜጠኞች እና ልሂቃኖች አማራውን በማዳከም የወያኔ መጋዝ ይዘው በግዝገዛው ሴራ ላይ እየተሳተፉ ናቸው። “ኢሳት” ጭምር። ጌታቸው ረዳ የሚለውን ጽሁፍ ሳነብ፣ ምንም እንኳ ከስብሰባው አዘጋጅ ከሞረሽ ወገኔ መግለጫ ይወጣል ብዬ ስጠብቅ እስካሁን ባላይም፣ በኢሳት ሴራ በጣም ማዘኔንና፣ የሞረሽ ወገኔን ደግሞ “እሰጥ – አገባ” ውስጥ አለመግባት የድርጅቱን በራስ መተማመን ያሳየኝ ክስተት መሆኑን መግለጽ እወዳለሁ።

ሞረሽ ስብሰባውን ሲጠራ በማስታወቂያው፡-

በኢትዮጵያና በአማራው ነገድ ላይ እየተፈጸመ ስላለው ጥፋት እና ጥፋቱን ለመከላከል አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ማድረግ ስላለበት ተግባር ለመመካከር የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ጥልቅ እውቀት ያላቸውን ሶስት ምሁራንን ፕሮፌሰር ጌታቸው ሓይሌን፣ ዶክተር ሃይሌ ላሬቦ እና አቶ ጌታቸው ረዳን በአስረጅነት ጋብዘናል። ይልና በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲገኝ ይጋብዛል።

በሞረሽ ወገኔ የግብዣ ጥሪ ላይ እንደምናየው፣ ኢትዮጵያዊውን ሁሉ ለውይይት ሲጋብዝ ቅሬታም ካለ ቅሬታን በመድረኩ ላይ ተገኝቶ እንደማሰማት፣ ለምን ሰው ወደ ስብሰባው እንዳይሄድ ኢሳት በዚያው ሰዓት እና በዚያው ቀን ስብሰባ መጥራት መረጠ? ብሎ መጠየቅ ከጀሌነት ራስን ነጻ ማውጣት ብቻ ሳይሆን፤ ሰው ለኢሳት ለሚያደርገው የገንዘብ አስተዋጽኦ የመጠየቅ መብቱም ነው ብዬ አምናለሁ።

ሞረሽ ወገኔ በጁላይ 27 “ቅሬታን ስለማሳወቅ” ብሎ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ቦርድ በጻፈው ደብዳቤ እንዲህ ይላል።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በ፴፩ኛው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ዝግጅት ለሰኔ ፳፮ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. (July 3, 2014) ሕዝባዊ ስብሰባ መጥራቱን ኢሣት እያወቀ፣ ማስታወቂያውንም በራሱ ዝግጅት ከሦስት ጊዜ በላይ ለሕዝብ አሰምቶ እያለ፣ የኢሣትን ዓመታዊ የገንዘብ ማሰባሰቢ ዝግጅት ድሮ ያደርግ የነበረበትን ቀን ትቶ፣ ሞረሽ-ወገኔ ሕዝባዊ ስብሰባ በሚያዘጋጅበት ቀን እና ሰዓት ለማድረግ መወሰኑ፣ “ጠብያለሽ በዳቦ” ሆኖ ተሰምቶናል። ይህም የኢትዮጵያውያን ተቋሞች እንዲጠናከሩ እንጂ፣ እንዳለፉት ሁሉ ተቋሞች እንዳይፈርሱ ዓላማቸው አድርገው የተነሱትን እንደሞረሽ ያሉ ድርጅቶችን የጠነከረ አቋም የሚፈታተን ሆኖ ተሰምቶናል።

ስለሆነም፦

1. ኢሣት በሣንሆዜ ሊያደርገው ያሰበውን ዝግጅት ቀኑን ለሌላ ቀን እንዲደርግ አጥብቀን አበክረን እንጠይቃለን።

2. በዐማራው ላይ የሚፈጸሙ ግፎች እና በደሎችን ኢሣት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ባላነስ መልኩ የዜና ሽፋን እንዲሰጠው ከማክበር ጋር እናሳስባለን።

ይህ አቤቱታ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ቦርድ ይድረስ እንጂ ቦርዱ ለቅሬታ ማሳወቂያው መልስ ከመስጠት ይልቅ የሞረሽን ስብሰባ ለማደናቀፍ ካቀደው ሴራው አልተቆጠበም። ለምን?

ኢሳት በኢትዮጵያኖች የገንዘብ እርዳታና ተሳትፎ የተቋቋመ እስከሆነ ድረስ ኢትዮጵያኖችን በጋራና በእኩልነት የሚያሳትፍ ከመሆን አልፎ ወገን በመለየት ለአንዱ አቀንቃኝ ለሌላው እንቅፋት መሆን አልነበረበትም። ኢሳት የራሱ ባለቤትነት የሌለው፤ ግንቦት 7 እና የአክራሪ ብሄረተኞች በውስጥ ሆነው በበላይነት የሚያሽከረክሩት ነው እየተባለ ለሚታማው ማስተማመኛ ካልሆነ በቀር በሞረሽ ስብሰባ ላይ ያሳየው ተንኮልና ሴራ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም።

ኢሳት ከአማራው ህዝብ የሚፈልገው ገንዘቡን እንጂ የአማራውን ህዝብ አይደለም የሚባለውን ወሬ ከዚህ በፊት እንዳልታመነ ወሬ ሰምተን ከማለፍ ይልቅ ቆመን ኢሳትን ከመጠየቅና ከመጠራጠር አልፈን የሳንሆዜው የኢሳት ድርጊት ለወሬው ማስተማመኛ ከመሆን ያለፈ ለኢሳት የፈየደለት ነገር ያለ አይመስለኝም። በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ኢትዮጵያዊነት በአንድ መድረክ ተገናኝቶ እንዳይነጋገር  እንቅፋት እየሆኑ ከኢትዮጵያኖች በተለይም ከአማሮች የገንዘብ እርዳታ መጠየቅ “ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል” እንደሚሉት፣ አይን ያወጣ የሰው ንቀት ይሆናል። የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ደግሞ አማራው ኢሳትን በገንዘብ እስከረዳ ድረስ፣ በኢሳት ቴሌቪዥን ጣቢያ በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን መፈናቀል፣ መገደልና መታሰር ወዘተ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ እኩል ትኩረት ሰጦ ማስተናገድ ይገባል። “ከአማራው ህዝብ ገንዘቡን ብቻ ነው የምንፈልገው” የሚለው ፈሊጥ በሂደት የኢሳትን ማንነት መፈታተኑ እንደማይቀር ኢሳትና ደጋፊዎቹ ሊያስቡበት ይገባል። “እዩኝ! እዩኝ! ያለች ደብቁኝ! ደብቁኝ ትላለች” እንደሚባለው፣ ዛሬ መድረኩን ይዘናል ተብሎ የአንድን ህዝብ መፈናቀል፣ መገደልና መታሰር ህዝብ እንዳያውቅ የሚደረግ ተንኮልና ሴራ ነገ ያስጠይቃል።

tasewanete@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule