• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ለእገሌ ሚ/ር እናገራለሁ፤ ለእገሌ ደኅንነት እደውላለሁ እያሉ አያስፈራሩን”

October 13, 2014 06:43 pm by Editor 1 Comment

  • “አማካሪዎቼ ዓላማዬን የሚጋሩና የሚያስፈፅሙልኝ ሰዎች ናቸው፤” አቡነ ማትያስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ተጠርቶ የተካሔደው ስብሰባ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ወቅታዊ ሁኔታ የማይገልጽ፣ መዋቅሩን ያልጠበቀ እና ጽ/ቤታቸው የማያውቀው መሆኑን በመግለጽ ተቃወሙ፡፡ “የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልጸግ” በሚል ርእስ ከትላንት በስቲያ (መስከረም 29፤2007) በመንበረ ፓትርያርኩ አዳራሽ የግማሽ ቀን ስብሰባ በተደረገበት ወቅት፣ የፓትርያርክ አቡነ ማትያስን የመግቢያ ንግግር ተከትለው የተናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ÷ “አሁን ወደ ስብሰባው ስገባ ነው መልእክቱን የሰማሁት፤ አጀንዳውም ከመቅረቡ በፊት ከቋሚ ሲኖዶሱ ወይም ከእኔ ጋራ ምክክር አልተደረገበትም፤” በማለት ስብሰባው ከመዋቅሩና ከዕውቅናቸው ውጭ የተጠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ባስተላለፈው የቃል ትእዛዝ መጠራቱ በተገለጸው በዚሁ ስብሰባ÷ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመምሪያዎች ዋናና ምክትል ኃላፊዎች፣ የድርጅቶች ዋናና ምክትል ሥራ አስኪያጆች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአስተዳደር ኃላፊዎች፣ የዋና ክፍሎችና የክፍሎች ኃላፊዎች፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ዋናና ምክትል ሥራ አስኪያጆች መሳተፋቸው ተገልጧል፡፡

በ2001 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴ መጠናከሩን ተከትሎ የቀድሞው ፓትርያርክ መዋቅሩን ሳይከተሉና ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋራ ሳይመክሩ ወስደዋቸው ነበር ያሏቸውን ርምጃዎች በመቃወም በወቅቱ የአሜሪካ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት የአሁኑ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በብዙኃን መገናኛ የሰጡት መግለጫ በማስረጃነት ተይዞ እንደሚገኝ ያስታወሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ “ቅዱስነትዎም በምትካቸው ሲቀመጡ መዋቅሩን ሊጠብቁ ይገባል፤ መዋቅሩን ሳይከተሉና ከሚመለከተው አካል ጋራ ሳይመክሩ የሚሠሩት ሥራ ቤተ ክርስቲያኒቱን አደጋ ላይ የሚጥል ነው፤” እንዳሏቸው ተመልክቷል፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ “ውድቀት እንዳይደረስብዎ አማካሪዎችዎ ሊያዝንልዎ ይገባል፤” ማለታቸውን የገለጹት የስብሰባው ተሳታፊዎች አያይዘውም “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በአማካሪዎቻቸው ምክንያት ከዕድሜያቸው ዐሥር ዓመት አሳጥረዋል፤ እርስዎም በአማካሪዎችዎ የተነሣ ዕድሜዎ እንዳያጥር ያስቡበት፤” ሲሉ መምከራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ውይይቱን በሰብሳቢነት የመሩት ፓትርያርኩ በበኩላቸው፤ በሥራ የሚያግዛቸው ባለማግኘታቸውና ብቻቸውን በመኾናቸው” ስብሰባውን ወደ ታች ወርደው ለመጥራት እንደተገደዱ አስረድተዋል፡፡ ፓትርያርኩ ባቀረቡት በጽሑፍ የተደገፈ ገለጻ÷ በቤተ ክህነቱ የመልካም አስተዳደር ዕጦቶች እንዳሉ፣ በሙሰኝነት፣ በዘረኝነትና በአድሏዊነት የሚገለጹ የብልሹ አሠራር ሒደቶች እንደሚታዩ ዘርዝረዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ስም የሚደራጁ ማኅበራትና ግለሰቦች፣ ሕግና ደንብ እየጣሱ መዋቅሯን እየተፈታተኗት እንደሆነና ከመዋቅራዊ ቁጥጥር ውጭ የሚንቀሳቀስ ሀብትና ንብረት እያካበቱ በመሆኑ አካሔዳቸው ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ጥንካሬና ህልውና ፍጹም አደጋ እንደኾነ አብራርተዋል፡፡

መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አንጻር ሁሉም የሥራ ኃላፊዎች ራሳቸውን በመፈተሽና በማጽዳት ችግሩን በዘላቂነት ለማስወገድ በሚደረግ ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ ያሳሰቡት ፓትርያርኩ፤ የማኅበራት አካሔድ ሥርዓት መያዝ እንዳለበት ጠቁመው ተገቢ ያልሆነውን አካሄድ ሁሉም ሊቃወመው ይገባል ብለዋል፡፡ “አማካሪዎቼ ዓላማዬን የሚጋሩና የሚያስፈፅሙልኝ ሰዎች ናቸው፤” ያሉት አቡነ ማትያስ፤ “አሁንም የምቀጥልበት መሆኑን አሳውቃለሁ” ብለዋል፡፡ “ብቻዬን ነኝ፤ በሥራም አልታገዝሁም” ለሚለው የፓትርያርኩ ንግግር “ቅዱስነትዎ አዝዘው ምን ያልተፈጸመ ነገር አለ?” በሚል ምላሽ የሰጡት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ “ያልተፈጸመ ነገር ካለ ለጉባኤው በይፋ ይገለጽ” ሲሉ ጠይቀዋቸዋል፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግርና የችግሩ መገለጫዎች በርግጥም እንዳሉ ያልሸሸጉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ መምሪያዎችና ድርጅቶች የበጀት ዓመቱን ዕቅድ በማውጣት፣ የክንውን ሪፖርት በአስተዳደር ጉባኤ በወቅቱ እንዲያቀርቡ፣ ድክመቶች እንዲስተካከሉና ጠንካራ ጎኖች ታቅበው እንዲቀጥሉ መደረጉን በመግለጽ በፓትርያርኩ ጽሑፍ የቀረቡትን መረጃዎች ወቅታዊነት ሞግተዋል፡፡

በልማት ተግባራትና በሠራተኛ አያያዝ ባለፈው በጀት ዓመት የተፈጸሙ ተግባራትን የዘረዘሩት የጽ/ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አባ ኃይለ ማርያም መለሰ በበኩላቸው፤ ቀጣይነት ባላቸውና በጥናት በተደገፉ የመልካም አስተዳደር ማሻሻያዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችና የተጉላሉ ባለጉዳዮች አለመኖራቸውን የገለጹ ሲሆን፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን የፋይናንስ ሥርዐት ዘመናዊው ለማድረግ ዝግጅቱ መጠናቀቁን ጠቁመው የፓትርያርኩን መረጃዎች አግባብነት እንደጠየቁ ታውቋል፡፡

አንድ የስብሰባው ተሳታፊ “አንድ ጣታችንን ወደሌላው ስንጠቁም ሦስቱ ወደኛ እንደሚያመለክት አንዘንጋ” በማለት ፓትርያርኩ ከሙስናና ብልሹ አሠራር ጋር በተያያዘ በዙሪያቸው ስላሉ አማካሪዎችም እንዲያስቡበት ጠቁመዋቸዋል፡፡ መንግሥት የሲቪል ማኅበራትን የሚከታተለው ሕግ አውጥቶና ተቋም መሥርቶ መሆኑን፣ በሕጉ የሚተዳደር አብሮ እንደሚጓዝና አልፈልግም ያለ እንደሚወጣ የተናገሩት አቡነ ማቴዎስ፤ ቤተ ክርስቲያን ግን መንፈሳውያን ማኅበራት የሚቋቋሙበት ሕግ እንዳላወጣችና የምታቅፍበት መዋቅር እንዳልዘረጋች ገልጸዋል፡፡

በአገልግሎት ላይ ያሉትን መንፈሳውያን ማኅበራት በሕገ ወጥነትና በመዋቅር ባለመታዘዝ ለመጠየቅ በቅድሚያ ሕጉ ወጥቶ በሥራ ላይ ማዋሉ መቅደም እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ “ለኢትዮጵያ በረሃ ወርደው፣ ብረት አንሥተው የታገሉትና ዋጋ የከፈሉት ሁሉም ሕዝቦች ናቸው፤ ሕገ መንግሥት ለሁሉም እኩል ነው፤ ለእገሌ ሚኒስትር እናገራለሁ፤ ለእገሌ ደኅንነት እደውላለሁ እያሉ አያስፈራሩን፤” በማለት ዋና ሥራ አስኪያጁ ፓትርያርኩን እንዳሳሰቧቸው የስብሰባው ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

አቡነ ማትያስ ቀደም ሲል ከቋሚ ሲኖዶሱ ጋራ ሳይመክሩ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአድባራትና ገዳማት አለቆች ጋራ ባደረጉት ስብሰባ፤ ሊቃነ ጳጳሳቱን ማዘለፋቸውን የጠቀሱት አቡነ ማቴዎስ በዚኽም ሁሉም አባቶች ቅሬታ እንደተሰማቸውና እንዳዘኑባቸው ተናግረዋል፡፡ ፓትርያርኩ ዓመቱን በሙሉ በየደረጃው እቀጥልበታለሁ ባሉት ስብሰባ÷ አጀንዳዎች መዋቅር ሳይጠብቁ፣ ጥናት ሳይደረግባቸውና ሳይብላሉ ውይይቱ ለሚዲያዎች ክፍት መደረጉ ቤተ ክርስቲያኒቷን ለአጉል ትችት ያጋልጣታል ሲሉ ተሳታፊዎች አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ (በርዕሱ ማሻሻያ ተደርጓል፤ ምንጭ፤ አዲስ አድማስ)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. dereje says

    October 16, 2014 11:13 am at 11:13 am

    ያ ጳውሎስ የተባለ ጎረምሳ ፓትርያርክ ፈጣሪ ምን እንደሆነ ሳያውቅ ፈጣሪ ወሰደው። ማትያስ የተባልከውም ፓትርያርክ ተብዬ ህወሀት በጠመንጃ ከሚጠብቀው ቤትህ አጥር ሥር ክርስቶስ ወድቆ ይጠብቅሀልና እሥኪ ወጣ ብለህ አናግረው። ገና እኮ ጎረምሣ ነህ። ጠቢቡ ሰለሞንም “በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ “ይላልና።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule