• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ተጋሩን አትንኩት!

July 20, 2016 07:58 am by Editor Leave a Comment

የኢትዮጵያ ፖለቲካ በገባኝ መጠን፡- በአሁኑ ሰዓት ሀገሪቱን የሚመራት ቡድን ራሱን ወደ ገዥ መደብነት ቀይሯል፡፡ በገዥ መደብ ውስጥ የህወሓታዊያን ኃይል ገኖ የወጣ መሆኑ ለክርክር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይሁንና ገዥ መደቡን “ያጸኑት”’ ሌሎች ኃይሎች እንዳሉ መካድ ያስተዛዝባል፡፡ የፖለቲካ ኃጢያት ትንሽ የለውም፡፡ የምንግዜም የደረጃ ሁለት ተፋላሚዎች የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች፤ የአድርባዮ ኦህዴድ ባለ ስልጣናት፤ ሚዛን አስጠባቂዎች የዲኢህዴን ሰዎች እና የአጋር ድርጅቶች ተቀጥላ ምሁራን (auxiliary elites) አሁን ላይ ወደ ዝግ አምባገነንነት እያዘገመ ላለው ገዥ መደብ ማንአህሎኝ ባይነት የራሳቸዉ የሆነ የማይናቅ ሚና አላቸዉ፡፡ የነዚህ ድርጅቶች ቁንጮ መሪዎች የገዥ መደቡ መሐንዲሶች ናቸው፡፡ ዛሬ ላይ ላለዉ በደልና ጭቆና ዋነኛ ተጠያቂዎችም የገዥዉ መደብ የፖለቲካ መሀንዲሶች ናቸዉ፡፡

በርግጥ አገዛዙ አራት ኪሎ ላይ እግሩን ከተከለበት ግዜ በተለይም ካለፈው አስር ዓመት ወዲህ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተጋሩዎች የኢኮኖሚ የበላይነት አሳይተዋል፡፡ አንጻራዊ የመንግስት ቁልፍ ቢሮክራሲ ቦታዎችንም ተቆጣጥረዋል፡፡ ግና፤ እነዚህ የገዥው መደብ አባሪ ተባባሪዎች ብዙሃኑን ተጋሩ ይወክላሉ (?) ብሎ ማሰብ የወቅቱ ጥያቄ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት በአባይ ወልዱ ክልላዊ መንግስት መረጃ መሰረት ስምንት መቶ ሰባ ሺህ የሚሆኑ ዜጎች የምግብ እህል እጥረት አጋጥሟቸዋል፡፡ በየጊዜው ስንዴ፣ ዘይትና አልሚ ምግቦችን በቤተሰብ ብዛት ልክ የሚረዱ ናቸው፡፡ በአንፃሩ የተሻለ አምራች ነው የሚባለው የምዕራብ ትግራይ አካባቢ እንኳ በ2007/8 የምርት ዘመን አጥጋቢ ምርት ወደ ገብያ ሊያወጣ አልቻለም፡፡ ምስራቁን የትግራይ ክፍል እንኳ ብንረሳው ይሻላል፡፡ በከተሞች የሥራ አጡ ቁጥር ከክልሉ ህዝብ ብዛት አኳያ ሲታይ አስፈሪ ያደርገዋል፡፡ ስደት ብቸኛው መፍትሔ እስኪመስል ድረስ ብዙ ትግራዋያን ወጣቶች በሱዳን በኩል እየወጡ የሳራህ በርሃና የሜዲትራሊያን ባህር ሲሳይ በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡ የተሳካላቸው “ኤርትራዊ ነኝ” በሚል በምዕራቡ አለም ለጥገኝነት ጎዳናዎችን ያጨናንቃሉ፡፡

በበኩሌ ትግራዋያንን ባሰብኩ ቁጥር ከመለስ ዜናዊ አገር አፍራሽነት ይልቅ ራስ ስዩም መንገሻ ለሀገረ-መንግስት ግንባታው የከፈለው ዋጋ ጎልቶ ይታየኛል፤ ከሽማግሌው ስብሐት ነጋ ከፋፋይ የፖለቲካ ሚና በተሻለ መልኩ የገሰሰ አየል (ስሁል) የትግል አበርክቶ አይረሴ ይሆንብኛል፡፡ ከሳሞራ የኑስ የትግራይ ብሔርተኝነት ማንአህሎኝነትና ትምክህት በላይ የኃየሎም አርዓያ አልበገር ባይነት ደምቆ ይታየኛል፤ ከነጋዴዋ አዜብ መስፍን የላሸቀ ስብዕና ይልቅ የአደይ አረጋሽ አዳነ የትግል ፅናትና ህዝባዊ ፍቅር ውስጤን ያሞቃዋል፡፡ ከጌታቸው ረዳ ረብ-የለሽ ድስኩር እነ አብረሃ ደስታ፣ አስራት አብረሃም፣ አምዶም ገ/ሰላሴ … ህዝባዊ ስሜትና የመረጃ ተደራሽነት ትጋት በሀገሬ ፖለቲካዊ ተስፋ እንዳልቆርጥ ብረታት ይሰጠኛል፡፡

ትግራይ በቀደመው ዘመን የኢትዩጵያ የስልጣኔ ራስ ነበረች፡፡ ትግራይን አልባ የኢትዩጵያን ቀደምት ስልጣኔ ማስታወስ ከፊልነትን የተሻገረ ሙሉ ቅዥት ነው፡፡ የኢትዩጵያን የቀደመ የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት አስጠብቆ ለማቆየት ከተዋደቁ ጀግኖች ውስጥ፡-

‹‹…ከነፋስ የፈጠነ

በወንድነቱ የተማመነ

ክንዱ ብርቱ እንዳንበሳ

በጠላት ሠፈር የሚያገሳ››

የተባለለት ጀግናው አዋጊ ራስ አሉላ አባነጋን ጨምሮ ብዙም ያልተዘመረላቸው የኢትዮጵያ ግዛትና ሉዓላዊነት ባለውለታዎች ከትግራይ ምድር እንደፈለቁ መካድ ከህዋሓት የክህደት ጉዞ የሚተናነስ አይደለም፡፡ የባንድነት ቃለ-ትርጓሜ ተጋሩን አስታኮ ‹‹እየተብራራ›› መምጣቱ ብሎም ጉዳዩ ከኢ-መደበኛ ወግ ወደ መደበኛነት ለመሸጋገር መውተርተሩ የተካደውን መካድ (denial of defrayal) በሚባለው የታሪክ በሽታ ተጠቂው እየበዛ ለመምጣቱ አብይ ማሳያ ይሆናል፡፡ የሀሳብ ተገላባባጩ አፈወርቅ ገ/የሱስ (ለኢጣሊያን ያደረ ባንዳ) ጎንደሬ እንደነበረ ብዙ ግዜ ሲጠቀስ አይታይም፡፡ በሌላው አካባቢ የአደባባይ ሰዎች ከነበሩት ውስጥ ለባዕድ ስርዓት ተገዥና አስገዥ የነበሩ ሰዎች የተጋሩዎችን ያህል ስማቸው ሲነሳና ሲወቀሱ አይስተዋልም፡፡ ምሁራዊ ድባቡ ማንነትን ማጠንጠኛው እያደረገ በመጣበት በአሁኑ ሰዓት የፕሮፖጋንዳ ማሽኖች የአንድ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን ለማጥቃት ሲባል የብዙሃኑን ታሪክ መደፍጠጥ አመክንዮ የጎደለው ደካም እርምጃ ነው፡፡ የትም የማያደርስ፡፡ አንካሳ፡፡

አንድ እውነት እንቀበል፡፡ ኢትዩጵያ የበዙ የቀደሙ የመበታተን የታሪክ ፈተናዎችን አልፋለች፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የትግራዋያን ሚና ቀላል አልነበረም፡፡ በትግራውያን ከተበደልነው በላይ የተጠቀምነው ያመዝናል (የቀደመውን የኢትዩጵያን ታሪክ ከዘውጋዊ ማንነት የታሪክ ማስተንተኛ ማዕቀፍ ውጪ ለማየት የሚሞክር ነፃ ግለሰብ የማይክደው ሃቅ ነው) ዛሬ ላይ ዋነኛው በዳያችን የገዥ መደቡ ምሰሶ የሆነው ህዋሓት ነው፡፡ በዳዩን ለይቶ ማጥቃት የተበዳይ ጥልቅ መሻት ነውና በዳዩ ላይ ትኩረት ማድረጉ የተሻለ ነው፡፡ ህዋሓታዉያኑ የሚጋሩትና ሊሞቱለት የሚፈቅዱት አንድ ቡድናዊ ምክንያት አላቸው፡፡ እርሱም፡- በገዥው መደብ ውስጥ ያላቸውን የፖለቲካ የበላይነትና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማስቀጠል፤ ብዙሃኑ ተጋሩ ግን ከሌላው የኢትዩጵያ ህዝብ ጋር የሚጋራውና ሊሞትለት የሚችል የነፃነት ጥማት አለው፡፡

ሌላ እዉነትም እንመርምር፡- ያች የስልጣኔ እምብርት ዛሬ ላይ በህወሓት አጋፋሪነት የፖለቲካ ደናቁርትና የኢኮኖሚ በዝባዥ ጠቅላይ አገልጋዮች መፍለቂያ ብትሆንም ለኢትዩጵያችን አብርሆትን የሚመኙ ባህሩያን (ሊሂቃን) እንዳሉ መዘንጋት የለብንም፡፡ ደናቁርትና በዝባዦች ብዙሃኑን አይወክሉም፡ ብዙሃኑ ተጋሩ ራሱን ከገዥ መደቡ ህወሓት የነጠለ መሆኑን በተግባር እንዲያሳዩ መንገዱን መጥረግ ብሎም አስተቃቃፊ የህዝባዊ ንቅናቄ አጀንዳዎችን መቅረጽ የጋራ የቤት ሥራችን ሊሆን ይገባል፡፡ በተረፈ ብዙዎች እየወደቁለት ያለዉን የነፃነት ትግል ኪ-ቦርድ በመነካካት ለማቃለል መሞከርም ሆነ የነፃነት ትግሉን አንድ ብሔር ለመጨፍለቅ ያለመ አድርጎ መተርጎሙ ‹‹ያላዋቂ ሳሚ…›› እንደሚሉት ይመስላል፡፡ እናም የሳይበር አርበኞች ኳስ በመሬት አድርጉ፡፡ ሁሉም ማህበራዊ ፍትህ ናፋቂ፣ የነፃነት ረሀብተኛ ጣቱን ተጋሩ ላይ ከመቀስር ይልቅ የገዥው መደብ በተለይም የፖለቲካ መሀንዲሶቹና የኢኮኖሚ ጥቅመኞቹ  ላይ ትኩረት በማድረግ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ማቀጣጠሉ አብይ የቤት ሥራችን ይመስለኛል፡፡ የወልቃይት ጠገዴ የአማራነት የማንነት ጥያቄ ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ነዉ፡፡ ጉዳዮ ከገዥዉ መደብ ውድቀት በኃላ በህዝበ ዉሳኔ እልባት እንዲያገኝ ማድረግ ይቻላል፡፡ አሁን ባለዉ ነባራዊ ሁኔታ ታሪካዊ ሰነዶችንም ሆነ ህዝባዊ ፍላጎቱን መሰረት ያደረገ መፍትሄ ይሰጣል ብሎ ማሰብ የወህነት ይመስላል፡፡ ለግዜዉም ቢሆን የወልቃይት ጠገዴ የአማራነት የማንነት ጥያቄ በመላ አገሪቱ ለታፈነዉ አመጽ ማነቃቂያ ደወል ሆኖ እያገለገለ ነዉ፡፡ምናልባትም የፌደራሊዝሙ ዲያሌክቲክ ኢ-ተቀልባሽ በሆነ መንገድ ገኖ እየወጣ እንደሆነ የሰሞኑ ጉዳይ ጉምቱ ማሳያ ይሆነናል፡፡ ዲያሌክቲኩን በማጎን አቻቻይ የፖለቲካ ሥርአት የሚወልድ ሲይንቴስስ (synthesis) ለመፍጠር እንደሌላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ማህበራዊ ፍትህና ነጻነት የተጠማዉን ተጋሩ የዲያሌክቲኩ (ቴንሰሱ) አካል ማድረግ አቋራጭ የድል መንገድ ነዉ፡፡ በፖለቲካዉ አለም ከስሜት ይልቅ ስሌት የድል ማፍጠኛ ነዉ እናም ተጋሩን ለቀቅ የገዥዉን መደብ ምሰሶ ጠበቅ ማድረጉ የተሻለ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule