• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዳዊት ጠጠር!

March 24, 2017 05:11 am by Editor Leave a Comment

ሰዉ በሀገሩ እንደ ዜጋ እኩል ተወዳድሮ ለመኖር ከአንድ ብሔር መወለድ ወይንም በጥብቅ መዛመድ የቅድሚያ መመዘኛ ሲሆንበት፤ ወዶ ያላመጣዉ፣ ፈቅዶ ያልተዛመደዉ ብሄሩ የተፈጥሮ ዉበቱ ሳይሆን እርግማን ሲሆንበት፤ ተምሮ ማወቅ አዉቆ መጠየቁ፣ ለሀገሩ መቆርቆሩ በቅን ሳይታይለት ቀርቶ መጨረሻዉ እድለኛ ከሆነ ማዕከላዊ አለያም ቅሊንጦ መግባትና ሰዉሰራሽ ሲኦልን ማየት ማሳረግያዉ ሲሆን በለስ ያልቀናዉ ደግሞ በዚች ምድር የመኖርያ ቀኑ በአንባገነኑ ስርዓት ሲወሰንለት፤ አፈር ገፍቶ ለፍቶ ግሮ ጥሮ ሳይማር ያስተማረዉን ማህበረሰብ በዉቀቱ ለማገልገል በአምስት ለአንድ መጠርነፍ ግዴታ ሲሆንበት፤ በተወለደበት ሀገር እንደ ሁለተኛ ዜጋ መታየት፣ በገዛ ሃገሩ ባዕድ መሆንን፣ ተወዳድሮ ማሸነፍ ሳይቻል ሲቀር ስደትን አማራጭ የሌለዉ መፍትሄ አድርጎ ለመዉሰድ ይገደዳል ይሰደዳልም፡፡ እውነተኛ መግቢያ ባታገኝም ነብሱ ለግዜውም ቢሆን ማረፊያ በማግኘቷ በሀገሩ ካደመነበት ጥቁር ጭጋግ በመራቁ ለጊዜዉም ቢሆን ነብሱ እፎይታ ይሰማታል ነገ የሚል ተስፋ በልቡም ያጭራል:: ሆኖም የተፈጥሮ ጉዳይ ነዉና ሰው ከበቀለበት አፈር ተነጥሎ ሌላ ቦታ እስኪያፈራ ግዜ እንደሚወስድበት ሁሉ በስደት የሚኖርበት ባህል አፈር እና አየር አለመመቸት ከሀገር እና ከቤተሰብ ናፍቆት ጋር ተደምሮ ነፍሱን ምቾት ይነሳዋል፤ ሃሳቡና ቀልቡ ሁሌም ወደተወልደበት፣ አፈር ፈጭቶ፣ ጭቃ አቡኩቶ፣ የበሬ ጭራ ጎትቶ፣ ቦርቆ ወዳደገበት ቀየዉ ሽምጥ ይጋልበበታል በትዝታም ይቆዝማል፡፡

የወገን ጨዋታ በአይኑ እየዞረ ከዛሬ ነገ ይሻላል በሚል ተስፋ ከዚያም ሲያልፍ የኔንስ ሕይወት አንዴ ዉሃ በልቶታል ግን ወገኔን ቤተሰቦቼን ለምን ብሎ ሰዉነቱን ረስቶ ከክብሩ ዝቅ ብሎ ክብሩንና ማንነቱን ከማያዉቁለት በግ መሰል ተኩላዎች ጋር የተናጠቃትን ስጋ መሰል ጥሪት ተስፋ ወዳጣባት ሃገሩ መልሶ በሚልከዉ ገንዘብ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በሙስና ሀንጎቨርና በዘረኝነት አዙሪት የሚመራት መንግስት ነኝ ባይ ወንበዴ ዋነኛዉ የዉጭ ምንዛሬ ምንጭ ከመሆኑም ባሻገር ለወያኔ እብት ማስተንፈሻ ብሎም ከሰዉ በታች ሆኖ በላካት ጥሪት ለወንድሙ ሕይወት ቀነ ቀጠሮ መቁረጫ ምላጭ መግዣ መሆኑን ስረዳ ልቤ በሃዘን ይርዳል እረ ለመሆኑ ይህች ሀገር የማን ናት ብሎ ዉስጤ ይጠይቃል

ይህ ባለ ብዙ ጥያቄና ባለብዙ መልስ ባለቤት የሆነዉ ሃገሩን ናፋቂ ስደተኛ ለህዉሃት መራሹ አንባገነን መንግስት የዉጭ ምንዛሬ አቅም የመጀመሪያዉን ዱላ አቀባይ በመሆን መንግስት ከአሜሪካና አዉሮፓ ከሚያገኝዉ አመታዊ የገንዘብ ተፋሰስ ሰዎስትና አራት እጥፍ በዓመት በአማካኝ ከ3.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ያደርጋል፡፡ ይህም ከዉጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ከሚገኘዉ ገቢ ሲነፃፀር በ4 እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን ወደዉጭ ሸቀጥ በመላክ የሚገኘውን  ገቢ 93 በመቶው ይሆናል ማለት ነዉ፡፡

ታድያ በንደዚህ ሁኔታ የተገኘን የዉጭን ምንዛሬ በመጠቀም ለሀገር እድገት ለልማት እንዲሁም በሀገራችን የሚታየዉን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለምፍታት ከመጣር ይልቅ ወንበዴዉና በወንበዴዉ ዉስጥ የተሰገሰጉ ሆዳችዉ የማይጠረቃ ቆዳቸዉ ከጅብ ጅማት የተሰሩ ነገራቸዉ ሁሉ እንብላዉ እንብላዉ የሆኑ በእብሪት የታበዩ ለማይረባ አይምሮ የተሰጡ የሀገር ሸክም ወንበዴዎች ጥቅማቸዉን ለማስጠበቅ ሌት ተቀን በወገኖቻችን ላይ ያማያባራ የግፍ ጎራዴዎቻቸዉን ከአፎቱ ከመዘዙ አመታት ተቆጠሩ::

ወገን በሰዉ ሀገር የብሶትና የናፍቆት እንባ ወደዉስጥ ያነባል፤ ከዛ ማዶ የአንድ ክልል ሰዎች ዳንኪራ ይረግጣሉ ዉስኪ ይራጫሉ ባንተ ገንዘብ ባንተ ምንዛሬ በተገዛ እርሳስ  ወንድምህ ለትምህርት እንደወጣ በዛዉ ጠባብተኛ፣ ትምክህተኛ፣  ሽብርተኛ፣  አብዮተኛ ተብሎ በወጣበት ይሰረዛል፤ ላይመለስ ይሸኛል:: ትላንት አንተ የላከዉ ገንዘብ የህዉሃት ወዳጆችና አጋፋሪዎች ደረታቸዉን በእብሪት አሳብጦ እንደ ጎልያድ የገዘፉ እንዲመስላቸዉ አድርጉአቸዋል፤ የህዝብ ሮሮ፣ የህዝብ ዋይታ፣ የህዝብ ጩሀት፣ የህዝብ ብሶትን የሚሰሙበት ጆሮ የሚያሰላስሉበት አይምሮ ተደፍኗል፤ ይልቁንስ ከህዝብ ይልቅ በሲንጋፖር፣ በቻይና፣ በታይላንድ እንዲሁም በአሜሪካና በተለያዩ የአዉሮፓ ሃገራት የሚገኙ አለማቀፍ ባንኮች ዉስጥ በድብቅ ያከማቹት የህዝብ ሀብት ያሳስባቸዋል፣ ያስጨንቃቸዋል::

እዉነታዉ ይህ ነዉ እነሱ ሐገራቸዉን በማይተረቃ የነዋይ ፍቅር አሳልፈዉ ሰተዋል! ለነሱ ሕዝብ ማለት የሀገር ሀብት ሳይሆን ለገቢ ምንጭነት የሚያገለግል ግኡዝ አካል የፋብሪካ ጥሬ ዕቃነት የበለጠ ዋጋ እንደሌለዉ ለማሳየት እሩቅ መሄድ ስያስፈልገን ያለፉትን አስራ አንድ ወራት መለስ ብሎ ኦሮሚያን፣ አማራን እንዲሁም ደቡብን ማሰብ በቂ ነዉ! ሃይ ባይም ያሻዋል:: ዛሬ በሀገር ዉስጥ ስላለዉ ትግልና ምላሹ እንዲሁም በላያችን ላይ ስለተደነገገዉ የአስቸቁአይ የግዜ አዋጅ በማተት ጊዜአችሁን አላጠፋም:: ግና ለወንበዴዉ ጉጀሌ አንዱ የአቅም ምንጭ ሰልሆንነዉ በስደት የምንኖር አገር አልባ ባላገሮች ወይም መንግስት አቆላምጦ የሚጠራን ዳያስፖራዎች በጋራ በመሆን ሕዉሃት መራሹ መንግስት ነኝ ባዩ ላይ የዉጪ ምንዝሬ ምንጭ ላይ ከፍ ያለ ጫና በመፍጠር ለዉጥ ማምጣት ስለሚቻልበት እዉነታ ጥቂት ማለትወደድኩ

በዉጪ ያለዉ የሀገሬ ሰዉ ሊገነዘበዉ የሚገባዉ ነገር ቢኖር ኪሱን አራቁቶ የሚልካት ገንዘብ የዳዊት ጠጠር መሆኗን የመረዳት ጉዳይ ነዉ::

ታድያ ምን ይደረግ? የሚለዉ አንገብጋቢ ጥያቄ ይመስለኛል. . . .

የመተባበሩ ጉዳይ ካለ ሁሉም ጋር መልሱ ያለ ይመስለኛል፤ “የሃገርህን ሰርዶ በሀገር በሬ” እንዲሉ አበዉ እራሱን እንደጎልያድ በትቢት የካበዉ ህዉሃት መራሹ አንባገነኑ መንግስት የቆመበት አንደኛዉ የገንዘብ ምሰሶ መሰረት መሆናችንን ለማሳየት ወደ ሀገር ቤት የምንልከዉን የዉጭ ምንዛሬ መሐለቅ በማቀብ በእብሪትና በማናለብኝነት መሰረታዊና እንደሰዉ የመታየት ብሎም ተፈጥሮአዊ መብቶቻቸዉ እንዲጠበቁላቸዉ የጠየቁ ወገኖችችን ላይ ያለ ሕግ አግባብ ሕፃን ሴት አዝዉንት ወጣት ሳይል የሚወስደዉን የአፈና፣ የድብደባ፣ የእሰራትና፣ ግድያ እንዲያቆም ጫና እንፍጠር!! ብሎም በሀገራችን ዉስጥ የአንባገነን ስርዓት ያበቃ ዘንድ ከዛም የሁሉም ለሁሉም የሚሆን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የበኩላችንን በመወጣት ከአባቶቻችን በአደራ የተቀበልናትን የደም ዉርስ በመጠበቅ ልጆቻችን የሚኮሩበት ሃገራዊ ቅርስ እናኑር:: በሀገራችንም የህዝብን ጥይቄ መሰረት ያደረገዉ የእንቢተኝነት እንቅስቃሴ ተሳታፊ በመሆን የለዉጥ ሂደቱ ላይ አሻራችንን በማኖር ከትዉልድ ተወቃሽነት እንዳን፤ ለመጭዉ ትዉልድም ከዘረኝነት የፀዳችና ልዕልናዋ የተከበረ ዲሞክራሲያዊት ሃገር በጋራ እንመስርት እላለሁ::

ሰላም ለሀገራችን!!

(መብራቱ ከስቶክሆልም – soranet2011@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule