• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሰቆቃ በማዕከላዊ

July 16, 2015 08:15 am by Editor Leave a Comment

‹‹እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡››

አበበ ካሴ

እኔ አበበ ካሴ እባላለሁ፡፡ የሰሜን ጎንደር ተወላጅ ነኝ፡፡ በማዕከላዊ እስር ቤት ከ5 ወር በላይ ታስሬለሁ፡፡ ከዚህ መካከል 4 ወር ከ25 ቀናት በጨለማ ቤት ተቆልፎብኝ ቆይቻለሁ፡፡ ማዕከላዊ በነበርኩበት ወቅት የሁሉም እግርና እጆቼ ጥፍሮች ተነቅለዋል፡፡ አንዳንድ ቀን እጄ ላይ የሆነ ነገር ስለሚወጉኝ ጥፍሮቼ ሲነቀሉ አላውቅም፡፡ ስነቃ ነው መነቀላቸውን የማውቀው፡፡ ከዛም ቁስሉን እየነካኩ ያሰቃዩኛል፡፡ ማደንዛዣ ለምን እንደሚወጉኝ አላውቅም፡፡ ጥፍሮቼን ሲነቅሉኝ ብቻ ሳይሆን ሌላ ጊዜም ራሴን እንድስት ያደርጉኛል፡፡ እጅና እግሬን አስረው እንደ ፍሪጅ ያለ እቃ ውስጥ ያለ በረዶ ውስጥ ያስቆሙኛል፡፡ ለብዙ ሰዓት በጣም ቀዝቃዛ የሆነ ቦታ ላይ እስክደነዝዝ ቆሜ እውላለሁ፡፡ እስኪበቃቸው ከደበደቡ በኋላ እጅና እግሬን አስረው ከምርመራ ክፍሉ በታች በሚገኝ ምድር ቤት ክፍል ውስጥ ያለ ጉድጓድ ላይ ጥለውኝ ይሄዳሉ፡፡ ጉድጓዱ ጉንዳንን ጨምሮ ተባዮች ያሉት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እግሬንና እጄን አስረው ዘቅዝቀውኝ ይሄዳሉ፡፡ የመጣው ሁሉ ዝዋዥዌ እንደሚጫወት ህፃን ወዲያና ወዲህ ያደርገኛል፡፡ ገልብጠው አስረው ሲዘቀዝቁኝ በአብዛኛው ራሴን እስታለሁ፡፡ እግርና እጄን ከወንበር ጋር ያስሩኛል፡፡

ከወንዶች በተጨማሪ ሴቶችም ይመረምሩኛል፡፡ ሴቶቹ የሚመረምሩኝ ራቁቴን አርገው ነው፡፡ እነሱም ራቁታቸውን ሆነው ነው የሚመረምሩኝ፡፡ አሁን ለመናገር የማልደፈርው አፀያፊ ነገርም ፈፅመውብኛል፡፡ ይህን አፀያፊ ነገር የሚፈፅሙት አደንዛዥ እፅ እየተጠቀሙ ነው፡፡ ይህን ሲያደርጉ በአይኔ አይቻቸዋለሁ፡፡ መርማሪዎቹ ሰውነቴን በኤሌክትሪክ አቃጥለውኛል፡፡ ኤሌክትሪኩን የሚሰኩት ደረቴና የውስጥ እግሬ ላይ ነው፡፡ በዚህም የውስጥ እግሬ ተገልብጦ ሌላ ሰውነት አምጥቶ ነበር፡፡ እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡ ይህን ያህል አሰቃይተው ከጥቅም ውጭ ስሆን ቂሊንጦ አምጥተው ጣሉኝ፡፡ 11 ወር ያህል አልጋ ላይ ነበርኩ፡፡ በኤሌክትሪክ ግርፊያው ምክንያት ግራ ሰውነቴ ሽብ ሆኖ ነበር፡፡ ግራ እግሬ መንቀሳቀስ አይችልም ነበር፡፡ በምርኩዝ ነበር የምሄደው፡፡ አሁን እያነከስኩ ነው የምሄደው፡፡

በተለይ ማዕከላዊ ውስጥ ይህን ያህል የሚሰቃዩኝ አንደኛ የሚያግዛችሁ አገር ማን ነው በሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አማራ ክልል ውስጥ እንድትንቀሳቀሱ የሚተባበሯችሁን የብአዴን ባለስልጣናት ስም ተናገር እያሉ ነው፡፡ በሶስተኛ ደረጃ የሚያሰቃዩኝ የት የት ቦታ ነው የሰለጠንከው እያሉ ነው፡፡

እዚህ ቂሊንጦ ከመጣሁ በኋላም ያሰቃዩኛል፡፡ ወጣቶች እንዳይቀርቡኝ ያስፈራሩዋቸዋል፡፡ ማንም ጠርቶ እንዳይጠይቀኝ እየተደረገ ነው፡፡ ጨለማ ክፍል ወስደውም አስረውኝ ያውቃሉ፡፡ እነሱ ደብድበው ከጥቅም ውጭ ካደረጉኝ በኋላ የምደገፍበትን ምርኩዝም ቀምተውኛል፡፡ ‹‹ይህኮ የጦር መሳሪያ አይደለም፡፡ እንጨት ነው፡፡ ለምን ትቀሙኛላችሁ? ደግሞም እናንተ ናችሁ እንዲህ ያደረጋችሁኝ፡፡›› ብያቸው ነበር፡፡ የሚሰሙ ሰዎች አይደሉም፡፡ የታሰርኩበት ክፍል ውስጥ እንድተኛበት የተሰጠኝ ቦታ ሽንት ቤቱ አጠገብ ነው፡፡ ሽንት እየሸተተኝ ነው የምተኝው፡፡ ‹‹ወደ ሌላ ቦታ ቀይሩኝ!›› ስላቸው ‹‹ደግሞ ለአንተ ይህ አንሶህ ነው?›› ይሉኛል፡፡ ያ ሁሉ ድብደባ ደርሶብኝ አልጋ ላይ በነበርኩበት ወቅት ወጣቶቹ ህክምና እንዳገኝ ወደ ሀኪም ቤቱ ወሰዱኝ፡፡ እነሱ ግን ‹‹ለአንተ ህክምና ሳይሆን ጥይት ነበር የሚገባህ›› ብለው መለሱኝ፡፡ እንዲህ እያሉ ለምን እንደማይገድሉኝ ይገርመኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ልጆችዋ ለእልቂት፣ ለስደት፣ ለግድያ እየተዳረጉ ነው፡፡ በአካልም ሆነ በስነ ልቦና ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ዓለም ለሰው ልጅ ምቹ በሆነችት ከዓለም ውጭ ሆነናል፡፡ የመገናር፣ የመሰብሰብ፣ የመደራጀት በአጠቃላይ ሰው የሚያደርጉንን መብቶች ተነጥቀናል፡፡ ከሰው የማንቆጠርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ገዥዎቻችን ህዝብን እየገደሉና ከሰው በታች አድርገው እየገዙም ቢሆን ግን ዓለምን እያታለሉ ነው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ሁሉ የሚደረገው የአንድን ቡድን የበላይነት ለማስፈን መሆኑ ነው፡፡ እንዲጠፋ ሆን ተብሎ ጥቃት የሚደርስበት ህዝብም እንዳለ እያየን ነው፡፡ ግን ኢትዮጵያ የ95 ሚሊዮን ህዝን ሀገር ናት፡፡

አሁን ያለው ስርዓት የአንድ ቡድን ስርዓት ነው፡፡ ለእሱ መኖር ደግሞ ሌሎቹን ገድሎ፣ አሰቃይቶ፣ አሳድዶ መኖር ይፈልጋል፡፡ ለስሙ የብሄር ብሄረሰብ መብት እናከብራለን ቢባልም እውነቱ ግን ኢትዮጵያውያን የመናገር፣ የመፃፍ፣ የመደራጀትና ሌሎች መብቶችን ተነፍጎ ከሰውነት ወጥተው ይገኛሉ፡፡ በዓለም ደረጃ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ቋንቋና ዘርን አይለይም፡፡ ይህ የሚደረገው በህወሓት ስርዓት ብቻ ነው፡፡ እኔ በርካታ ሰቆቃ የደረሰብኝ ሰው ስለሆንኩ ስርዓቱ የሚፈፅመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመመስከር እችላለሁ፡፡ እኔን ሰቆቃ ያደረሱብኝ ሰዎች ማንነታቸው መታወቅ ስላለባቸው እንደሚከተለው ስማቸውን እዘረዝራለሁ:-

1. አቶ አሸነፍ ተስፋሁን ላቀው
2. አቶ አብርሃም አይሸሽም
3. ሙሉጌታ ወርቁ
4. አቶ ደረሱ አያናው
5. የአማራ ክልል ደህንነት ኃላፊ የሆነው አቶ ተሾመ
6. የሰ/ጎ/መ/የታክቲክ ኃላፊ አቶ ሙላ እንየው
7. የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ተክላይ
8. የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ጌትነት
9. አቶ አሰፋ አትንኩት (ምርመራበ ኃላፊ)
10. መቶ አለቃ ተስፋዬ (መርማሪ)
11. ሳጅን ፍሬ ህይወት (መርማሪ)
12. ሳጅን ፅጌ (መርማሪ)

ከላይ የጠቀስኳቸውን በስምና በአካል የማውቃቸው ሲሆኑ ከእነዚህ በተጨማሪ ከደህንነት መስሪያ ቤቱ እየመጡ የሚያሰቃዩን ስማቸውን የማላስታውሳቸውና በመልክም የማውቃቸው የህወሓት ደህንነቶች አሉ፡፡

እዚህ እኛን እንደዚህ ሲያሰቃዩ ሀገሪቱን ገንዘብ መዝብረው የታሰሩ ሰዎች ምንም አይሆኑም፡፡ ተመችቷቸው ነው የሚኖሩት፡፡ ቂሊንጦ ውስጥ ሰው እንዳይቀርበኝም ቢፈልጉም ሰው ግን በጣም ይወደኛል፡፡ አሁን ጥፍሮቼ በቅለዋል፣ መራመድ ችያለሁ፡፡ አንድ ሽህ አመት አይኖርም፡፡ በጣም ብዙ ወገኖቻችን ሞተዋል፡፡ እኔ አለሁ፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ባለስልጣናት እኔ ላይ የደረሰውን ጨምሮ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ በፈፀሙት ወንጀል መጠየቃቸው የማይቀር ነው፡፡ nail

ይህ ሁሉ በደል ደረሰብኝ ስል ዝም ብዬ አይደለም፡፡ ማንኛውም ሰው መጥቶ የተሸማቀቀውን እግሬን፣ ቅጥ ባጣ ድብደባ የተጎዳው ሰውነቴን ማየት ይቻላል፡፡ ጥፍሮቼንም ለመስክርነት ይዤያቸዋለሁ፡፡ እነሱ ነቅለው ጥለው ሲሄዱ እኔ ስነቃ ሰብስቤ አስቀምጣቸዋለሁ፡፡ የተወሰኑትን ለመረጃነት አስቀምጫቸዋለሁ፡፡ ይህን ስል ግን እኔ ላይ የደረሰው ስቃይም የማይጠበቅ ሆኖ አይደለም፡፡ እነዚህ ሰዎች እንኳንስ ግለሰብ ሀገርም ገንጥለዋል፡፡ ከ40 አመት በፊት የነበረው የኢትዮጵያ ካርታ ተሸርፏል፡፡ እንኳን ሰው ሀገርም ለማጥፋት እየሰሩ ነው፡፡ ታሪካቸው፣ አመጣጣቸውም የሚያሳየው ይህን ነው፡፡ ይህን ሁሉ የምለውም መታወቅ ስላለበት ነው፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ)

ማሳሰቢያ:- አቶ አበበ ካሴ በስም የጠቀሳቸውን ከላይ የተጠቀሱትን ግለሰቦች ማንነት በተለይም ፎቶ ያላችሁ ሁሉ ለዝግጅት ክፍላችን በ (editor@goolgule.com) ወይም በፌስቡክ በኩል እንድትልኩልን ልናሳስብ እንወዳለን:: ቢያንስ ለዚህ ወገን የምናደርግለት ትንሹ ዕርዳታችን ይህ ይሁን::

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule