• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የታሪክ እርማት በየገፁ

October 16, 2017 06:38 am by Editor Leave a Comment

በቅርቡ “የትምህርት ሚኒስቴር” 400 ተማሪዎች በፈተና ቅጾች ላይ ኢትዮጵያውያን አይደለንም ብለው ሞሉ የሚል መረጃ አወጣ ሲባል ሰምቼ ቆሽቴ አርሮ ነበር። የተናደድኩበት ምክንያት የመንግስት የ26 አመት የጸረ-ኢትዮጵያዊነት ፖሊሲ አፈጻጸም ይህን የመሰለ ውጤት እንዴት ሊያመጣ ቻለ በሚል ሳይሆን እንዴት ዛሬ ስርአቱ በሞት አፋፍ ላይ ቆሞ እንኳን የሩብ አመት ድካሙ ከንቱ መሆኑን አይገባውም ብዬ ነበር። እንጂ ኢትዮጵያን የማትመስል ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሌት ተቀን ያለመታከት ሲዘራ የኖረው የጎሳ መርዝ 400 የተበላሹ እጽዋትን አበቀለ ቢሉኝ እንኳን ጉዳታችን ከዚህ በላይ አልሆነ ብዬ በእፎይታ እተነፍስ ይሆናል እንጂ ብዙም አላዝንም። መንግስት ግን ላመታት ስራው ከንቱነት ዋቢ የሆነውን መረጃ ዛሬም ሳያፍር  እንደመልካም ዜና ማወጁ ያስገረመኝ መሆኑን ግን መሸሸግ አልችልም።

የዛሬ ርእሴ ግን ይህ አይደለም። የጎሳ ፖለቲካ ቀባሪ አጥቶ እንጂ በህዝብ ህሊና ውስጥ ከሞተ ቆይቷል። አሁን የኢሀዲግ ኢትዮጵያ ቅዠት ሆና የህዝቡ ኢትዮጵያ እውን ልትሆን የተስፋ ቾራ ብቅ ማለት ጀምሯል። ህዝብ ላመታት በጎሰኝነት ፖለቲካ ስትጎሳቆል የኖረቺውን አንዲት ኢትዮጵያ ሊያድስ ሲታጠቅ እየታየ ነው። የሰሞኑ የባለራእይ የዖሮሞ ወጣቶች አስገራሚና አስደማሚ የሰሜንኢትዮጵያ ጉብኝት የዚህ የሀገር መልሶ ግንባታ ጥረት ግሩም ጥንስስ ነው። ኢትዮጵያን ለማፍረስ የታቹት የኢትዮጵያ ዖሮሞ ወጣቶች ኢትዮጵያን ዳግም ለመገንባት አስደናቂ ታሪክ ሰሩ። በጣና አረም ተምሳሌነት የኢትዮጵያን የተበላሸ ታሪክ አረሙት። የደበዘዘውን የህዝብ አንድነት እንደገና በፍቅር አደመቁት። “ኢትዮጵያ ኬኛ” ሲሉ።  የአንድነት ታሪክን ስርዝ ድልዝ በብሩህ የወጣት አእምሯቸው በቀረጹት አዲስ የፍቅር ብእር አድምቀው ጻፉና በሁላችንም ልብ ነገሱ።

ይህ ያልተጠበቀና ኢምንት የሚመስል ግን ደግሞ የኢትዮጵያን የታሪክ አቅጣጫ ከመሰረቱ የሚለውጥ ድንቅ እርምጃ አድማሱ መስፋት ይኖርበታል። በዚህ የፍቅር መርከብ ሁሉም መሳፈር ይኖርበታል። የአማራና ዖሮሞ ህዝብ አንድነት ለኢትዮጵያ አንድነት ያለው ፋይዳ ግዙፍ ነው። ሆኖም ኢትዮጵያ ከዚህም በላይ ናት። የትግራይ፣ የደቡብ፣ የቤኒሻንጉል፣  የጋምቤላና የሶማሌ ህዝብ ከኢትዮጵያ ሌላ እናት የለውም። እናም የዖሮሞ ወጣቶች ያሳዩን የፍቅር አበባ በሁሉም አቅጣጫ ሲበተን ማየት እንሻለን። በተለይ የትግራይ ህዝብ የሚነቃበት ጊዜ አሁን መሆን አለበት። በእኔ እምነት የትግራይ ህዝብ ወንድምና እህቶቹን የሚጠላ ህዝብ አይደለም። እንዲያውም የፍቅር ህዝብ ነው። ባልጠበቀው መንገድ የቅሬታ አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገባ ተደረገ እንጂ ህዝቡ በባህሪው ፀረአንድነት አይደለም። ስለዚህ ያለፍላጎቱ የተፈጠረበትን የአንድነት ክፍተት የሚሞላበትን ስልት ለመፈለግ ከዚህ በላይ አጋጣሚ ሊኖር አይችልም። የኢትዮጵያ የፍቅር ልብ ለሁሉም ክፍት ነው። አማራና ዖሮሞ ዜጎች የከፈቱት የፍቅር አዳራሽ ለማንም አይጠብም። ኢትዮጵያውያን አስተዋይ የዖሮሞ ወጣቶች ባቀጣጠሉት የፍቅር ሻማ መብራት እየተመሩ የደበዘዘ ያንድነት ታሪካቸውን ዳግመኛ ሊያደምቁት ይገባል። የዖሮሞ ወጣቶች የጀመሩት የታሪክ እርማት ስርዝ ድልዝ ባለበት ገፅ ሁሉ ሊቀጥል ይገባል። እናንት አስተዋይ የኢትዮጵያ ወጣቶች፣ ባስተዋይ ምግባራችሁ ሁላችንም ኮርተናል፤ ኢትዮጵያም ለዘላለም ትኮራባችhኋለች።

ህሩይ ደምሴ (zobar2006@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule