• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከእሁድ እስከ እሁድ

March 12, 2013 06:08 am by Editor Leave a Comment

ድርቅ ጦር እያማዘዘ ነው
የሟቾች ቁጥር ተደብቋል

በምስራቅና በምዕራብ ሃረርጌ ድርቅ በመግባቱ አርሶ አደሮች ከብቶቻቸውን በርካሽ ዋጋ ለመሸጥ መገደዳቸውን ዶይች ቬለ ሬዲዮ የአሜሪካን የርዳታ ድርጅት USAIDን ጠቅሶ ዘገበ። የድርጅቱ የምግብ አቅርቦት ተንታኝ ብሬክ ስታበረር እንዳሉት በአካባቢው የተከሰተው ድርቅ በሶማሊና በኦሮሞ አርብቶ አደሮች መካከል ግጭት አስከትሏል።

በተፈጠረው የውሃ ችግር ምክንያት ከብቶቻቸውን ውሃና ግጦሽ ፍለጋ ይዘው በሚሄዱ አርብቶ አደሮች መካከል የይገባኝልና ውሃና የግጦሹ ሳር ያልቃል በሚል ግጭት ተነስቷል። ተንታኙን የጠቀሰው ሬዲዮ በግጭቱ ስለደረሰው ቀውስ ያለው ነገር ባይኖርም ከተለያዩ ወገኖች የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሶማሊና ኦሮሞ አርብቶ አደሮች መካከል በተከሰተው ግጭት ከሰባ የማያንሱ ሰዎች ተገድለዋል።

የበልግ ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ ችግሩ መከሰቱን ተመልክቷል። በዚሁ ሳቢያ ምርቱ ከጠጠበቀው በታች ሃያ ከመቶ ሊሆን ችሏል። የዝናብ እጥረቱ በዚሁ ከቀጠለ ችግሩ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያው አስጠንቅቀዋል። ከብቶቻቸውን በመያዝ ምግብና ውሃ ፍለጋ የሚንከራተቱት አርብቶ አደሮች ከቤታቸው ርቀው ስለሚጓዙ ቤተሰቦች ወተት ማግኘት አልቻሉም። በአካባቢው ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኘው የጫት ምርትም በውሃ እጥረቱ ጉዳት ደርሶበት አርሶ አደሮቹን ገቢ እያሳጣቸው ነው። መንግስት ተከሰተ ስለተባለው ድርቅ ያለው ነገር የለም። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በዘንድሮው ዓመት የሚጠበቀው ምርት ከፍተኛ ስለሚሆን ግሽበቱን ያውረደዋል በማለት ለፓርላማ መናገራቸው ይታወሳል። መንግሥት የምግብ እጥረት እንጂ ድርቅ የለም በማለት እንደሚከራከር የሚዘነጋ አይደለም።

የ“አባባ”ታምራት ንብረት ለባንክ ተሰጠ
(ፎቶ: ዕንቁ መጽሔት)

በሰው ግድያና በማታለል ወንጀል ሞት ተፈርዶበት የነበረውና በይግባኝ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተቀይሮለት በማረሚያ ቤት የሚገኘው ታምራት ገለታ ወርቆች በየካራታቸው ተለይተውና ተጨፍልቀው ለብሔራዊ ባንክ ገቢ መሆናቸውን በፌዴራል መንግስት የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አቶ አወቀ አበራን ጠቅሶ ለአዲስ አድማስ ዘግቧል።

የግለሰቡ የንብረት ጉዳይ እስከ ሰበር ችሎት ድረስ በመድረስ የፍርድ አፈፃፀም ውሳኔ ካገኘ በኋላ የርክክብ ሂደቶቹ በኤጀንሲው በኩል ተፈጽሟል። ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ወርቆች በየካራታቸው ተለይተውና ተጨፍልቀው ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ተገርገዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማ ውስጥ የሚገኙት የግለሰቡ “አቢዶ” የተባለ ባለ ሶስት ኮከብ ሆቴልና መጠነኛ መኖሪያ ቤቱን ኤጀንሲው የተረከባቸው ሲሆን ለማስወገድ ጨረታ እንደወጣባቸውም አዲስ አድማስ አስታውቋል።

“ዳይኖሰር”

“… በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የምርጫ ሥርዓት “ዳይኖሰር” ነው የሚባለው፡፡ ምክንያቱም በብዙ አገሮች እየጠፋ ነው ያለው፡፡ የምርጫ ሥርዓቱ በሥልጣን ላይ ላለ ፓርቲ የሚያደላ ነው፡፡ ሥልጣን ላይ ያለው ፓርቲ ሥልጣን በቀጣይነትና በቋሚነት እንዲይዝ ዕድሎችንና ሁኔታዎችን የሚያመቻች ዓይነት የምርጫ ሥርዓት ነው፡፡ ከዚያ አኳያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲቀጭጩ ያደርጋል …”

ዶ/ር ያሬድ ለገሠ፣ የሕገ መንግሥት ተመራማሪ ታህሳስ21፤2005ዓም ለሪፖርተር ከተናገሩት የተወሰደ

ከየት አባቱ

እንባ እንባ ይለኛል

ይተናነቀኛል

እንባ ከየት አባቱ

ደርቋል ከረጢቱ:

ሳቅ ሳቅም ይለኛል

ስቆ ላይስቅ ጥርሴ

ስቃ እያለቀሰች መከረኛ ነብሴ::

(በአሉ ግርማ “ኦሮማይ”) ከበዓሉ ግርማ መድረክ የተወሰደ

ከሐረር የጭካኔ ወሬ ተሰማ

በአረብ አገር የተለመደው በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው አደጋ በኢትዮጵያ ወገኖቻችን መፈጸሙን ሸገር አዲስ ገለጸ። ሸገር በዘገባው እንዳስታወቀው በሐረር አንደኛ መንገድ ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ከቤቷ የወጣች የአስራ ሁለት ዓመት ታዳጊ ጨዋታ አታሏት መንገድ ትስታለች። የታዳጊዋን መደናገር የተመለከተች አንዲት ሴት ታዳጊዋን በወር 100 ብር ደሞዝ እንደምትከፍላትና ከእሷ ጋር ያለችግር እንደምታኖራት በማባበል አስረድታ ወደ ቤቷ ትወስዳታለች።

ከሃያ ቀን በኋላ ታዳጊዋ ስራ እንደበዛባት በመግለጽ ወደ ቤቷ እንድትመልሳት ትጠይቃለች። ሸገር ታዳጊዋ በኦሮሚኛ ስትናገር በማሰማት እንዳመለከተው ሴትየዋ ታዳጊዋ ወደ ቤት እሄዳለሁ በማለቷ ሳቢያ ተናዳ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ ከሁለተኛ ፎቅ ላይ ቁልቁል ወረወረቻት። በአካባቢው ሰዎች ርዳታ ድሬዳዋ ሆስፒታል የደረሰችውን ታዳጊ ህክምና የሚከታተሉት ዶክተር እንደተናገሩት አስራ ሁለት ጥርሶቿ የረገፉ ሲሆን፣ እግሯ ከጉልበቷ በታች ተሰባብሯል።

ታዳጊዋ በአስተርጓሚ እንዳለችው ሴትየዋ “ራሴን ከፎቅ የወረወርኩት እኔ ነኝ በይ፣ ይሀንን ካደረክሽና ከእስር ነጻ የምታደርጊኝ ከሆነ ወርቅ እገዛልሻለሁ። ገንዘብ እሰጥሻለሁ” ብላኛለች ብላለች። ከሀረር የተሰማው ዘግናኛ ዜና በአረብ አገራት ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍ ወደ አገር ቤት መዛመቱን ያመለከተ ነው። ሸገር ድርጊቱን የፈጸመችውን ሴት እምነትና ማንነት አልገለጸም።

ሜኔጃይተስ እንደ ሰደድ ተራባ
መንግሥት አልተነፈሰም

በያዝነው ሳምንት መገባደጃ ቪኦኤ እንዳስታወቀው ሜኔጃይተስ የሚባለው አደገኛ ወረርሽኝ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው። የዓለም የጤና ድርጅትን እንዳስታወቀው ወረርሽኙ በኦሮሚያና በደቡብ ክልል አስራ አራት ዞኖችን፣ ስልሳ ወረዳዎችን አዳርሷል። በተለይም በአስራ ስድስት ወረዳዎች ወረርሽኙ የከፋ ነው።

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለዜጎቹ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል። እንደ ቪኦኤ ዘገባ አሜሪካውያን የቅድመ መከላከያ ክትባት እንዲወስዱና፣ ክትባቱን ከወሰዱ ከአስራ አራት ቀን በፊት ወደ ስፍራዎቹ እንዳያቀኑ መመሪያ ተላልፎላቸዋል። ቪኦኤ ጉዳቱን መጠን አልዘረዘረም። ከመንግሥት ወገን ያገኘውና ያስተላለፈውም መረጃ የለም። አገር ቤት የሚታተሙ የግል ጋዜጦችም በሳምንቱ መጨረሻ ያሉት ነገር የለም። ወረርሽኙ ተስፋፍቷል የተባለባቸው ቦታዎች ሃዋሳን ጨምሮ የቱሪስት ገበያ ያለባቸው ከተሞችን ያዳረሰ በመሆኑ በሆቴሎችና በቱሪዝም ገበያ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት አለ። ከሁሉም በላይ ግን ወረርሽኙ ያስከተለው ጉዳት ይፋ አለመሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል።

ተመስገን ደሳለኝ “ልዕልና” ይዞ ወደ ህትመት ተመለሰ
“ይህ ለአፈና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምጽ ነው”

“ለዜጎች ክብር የማይሰጠው ኢህአዴግ፣ ህዝብ በሚከፍለው ግብር መልሶ የሚያፍነው ኢህአዴግ፣ የሀይማኖት ተቋማትን ወደ “አጋር ፓርቲነት” እየቀየረ ያለው ኢህአዴግ፤ ፍትህ ጋዜጣን እና አዲስ ታይምስ መፅሄትን በጉልበት ከነጠቀን በኋላ፣ ለሶስተኛ ጊዜ በሌላ ጋዜጣ ተመልሰናል” ሲል ተመስገን ደሳለኝ “ይህ ለአፈና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምጽ ነው” በሚል ስም በሚታወቀው የፌስ ቡክ ገጹ አስታወቀ።

“ልዕልና” ተመስርታ እንዴ ከታተመች በኋላ መቋረጧን ያመለከተው ጋዜጠኛ ተመስገን የመንግስት ዕዳ ተከፍሎ፣ አሳታሚ ድርጅቱ የአገሪቱ የአክሲዮን ሽያጭ ህግ በሚያዘው መሰረት ወደ “እኛ” ተላልፋለች ብሏል። ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ “አርብ አርብ ይሸበራል” እንዲል ንጉሥ ቴዎድሮስ፣ ልዕልና ጋዜጣም የዕለት አርብ ድምፅ ሆና እንደምትቀጥል ተመስገን አመልክቷል።

በኢሚግሬሽን ጉቦ ነግሷል

የጉዞ ሰነድ የሚያዘጋጀው የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት በመንግሥት ታማኝ የደህንነት ሰዎች የሚተዳደር ቢሆንም በጉቦ መነከሩን ኢሳት የካቲት 28 ቀን 2005 ዓ ም ምንጮቹን ጠቅሶ ዘገበ። ኢሳት እንዳስታወቀው አገልግቱን ፍለጋ ወደ ኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት የሚሄዱ ዜጎች አስከ አምስት ሺህ ብር በነፍስ ወከፍ ይጠየቃሉ።

አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት፣ ለማሳደስ፣ የስም ስህተት ለማረም እና የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከክልሎች ጭምር በየቀኑ በሺ የሚቆጠሩ አግልግሎት ጠያቂዎች ወደ አዲስ አበባው ኢምግሬሽን መ/ቤት ይጎርፋሉ። ጉዳያቸው ባስቸኳይ ስለማይፈጸም በገንዘብ እጥረት ጎዳና ላይ ለማደር ጭምር የሚገደዱ እንዳሉ ኢሳት አስታውቋል። በዚህ ምክንያት በርካታ ሴቶች ለመደፈርና ለዝርፊያ እየተዳረጉ ቢሆንም መ/ቤቱ አገልግሎት አሰጣጡን አሻሽሎ ቀልጣፋ ከማድረግ ይልቅ አንዳንድ ሰራተኞቹ በአካባቢው ካሉ ደላሎች ጋር በመሻረክ ቅድሚያ አግልግሎት ለማግኘት ከሚፈልጉ ግለሰቦች እስከ አምስት ሺ ብር የሚገመት ጉቦ በነፍስ ወከፍ እየተቀበሉ በማስተናገድ ላይ ናቸው ሲል ኢሳት ማህበራዊ አደጋውን በማካተት ዘግቧል።

በቦረና ባለስልጣናት በግና ገንዘብ ወሰዱ

በቦረና ዞን የኦህዴድ ባለስልጣናት ከ400 ሺህ በላይና በስጦታ የቀረቡ የበግ ጠቦቶችን መውሰዳቸው ተሰማ። ፍኖተ ነጻነት የካቲት 23 ቀን 2005 ዓ ም ባሰራጨው ዜና እንዳስታወቀው የተጠቀሰው የገንዘብና የጠቦት ስጦታ ሊወሰድ የቻለው በየስድስት ዓመቱ ለአባገዳው የሚቀርበው ስጦታ  ከህዝብ “እኛ እንሰበስባለን” በማለት ነው።

ድርጊቱ በዞኑ አመራሮችና በአባገዳው መካከል ልዩነት ያስነሳ መሆኑን የጠቆመው ጋዜጣው ጉዳዩን ለማጣራት ለቦረና ዞን አስተዳደር ማግኘት እንዳልቻለ፣ ለክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ጥያቄ አቅርቦ መልስ አለማግኘቱን አስታውቋል። አባገዳ በየትኛውም ጉዳይ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ከመሆናቸው በላይ ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው የማይቀለበስ የክልሉ ባህል መሰረት በህዝብ ፍጹም ተቀባይነት ስላላቸው ጉዳዩ ሌላ ችግር ሊያስከትል እንዳይችል ፍርሃት እንዳለ ታውቃል።

የሳምንቱ ፎቶዎች

በአዲስ አበባ የሚገኙ የሕዝብ ስልኮች ያሉበትን ሁኔታ የሚያመለክተውን ፎቶ ያገኘነው ከፎርቹን ጋዜጣ ነው፡፡ በኔትወርክ ችግር መከራውን የሚበላው የሞባይል ስልክ መበራከት ነው ወይስ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ውጤት?

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule