• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከመቀሌው ዱለታ በስተጀርባ ያሉ እውነታዎች

June 15, 2018 12:25 am by Editor 3 Comments

የህወሃት መግለጫ በመስመሮች መካከል ሲነበብ በተቀማ ጩኸት ሊመሰል ይችላል።

ከመቀሌው ዱለታ በስተጀርባ የነበሩ እውነታዎችን ለመዳሰስ የፖለቲካ ሊቅ መሆንን አይጠይቅም።ህወሃቶች አብረው ወስነው ያስተላለፉትን ጉዳይ እንደመጋዣ አኝከው ሲያበቁ፤ ከብዙ ገጽ የክስ ቻርጅ ጋር ብቅ ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩን ለማስጠቆር የሄዱበት ርቀት ግልጽ እና መሳጭ ነው። ሰማይ ወጥተው ቁልቁል ቢወርዱም ግን ከቶውንም የህዝብ ቀልብ ሊስቡ አይችሉም። እኛ ከሌለን ሃገር ትጠፋለች ይሉት የነበረው ቁንጽል እሳቤ፤ እነሆ ፉርሽ ሲሆንባቸው፤ አዲስ ካርታ መዘዙ። የአዲሱ ትውልድ መሪዎች፤ ሕዝብን በሃይል ሳይሆን በፍቅር መምራት እንደሚቻል ሲያሳዩዋቸው፣ ወደ ኦሪት ዞር ብለው ከዘፍጥረት መጀመራቸው ይሆን? በአዲሱ ዜማቸው፤ ኢትዮጵያን ትተው ስለ ትግራይ መጮህ የያዙ ይመስላል።

“ለነባር አመራሮቻችን እውቅና ይሰጥ” የምትለዋ ሃረግ ግን ብዙዎችን አስደምማለች። እውቅናውስ ይሰጥ። ግን ማን ነው ሰጭው? ዶ/ር አብይ አህመድ ወይንስ የአሜሪካ መንግስት?

እውቅና ሲሉስ ምን ማለታቸው ይሆን? ሰዎቹ ያካበቱት እና የተካኑበት ነገር ቢኖር ሱስ እና ዝርፊያ ነው። ለሌብነት የሚሰጥ የስራ ፍቃድ ማለታቸው ይሆን? የቃሉ ሰምና ወርቅ ፍቺ ይህ ከሆነ፤ ጥያቄው በአግባቡ መታየት አለበት። በአብዮታዊ ዲሞክራሲ አግባብ።

ሰጭው እና ከልካዩ ዶ/ር አብይ ከሆኑ ግን ለ27 ዓመታት ሳይታክቱ ሃገር በመዝረፍ እና ዜጋን በመግደል፤ ላደረጉት አስተዋጽዖ ከዝምታ ይልቅ እውቅናውን ቢሰጡ ይመረጣል። ጥያቄውን ተቀብለው በአቃቤ ህግ በኩል ቢያሳውቁ፤ ከእንደዚህ ዓይነት ክስ ይድኑ ይሆናል።

እጃቸው ላይ በከንቱ የፈሰሰ የንጹሃን ደም እና የሕዝብ ሃብት መያዛቸውን ለአፍታ እንኳ ዘንግተው፤ ለወንጀላቸው እውቅና ሲጠይቁ እፍረት እንኳ አይታይባቸውም። ክብር ለሚገባው ክብር ይሰጠዋል። የዘረፈ እና የገደለ ደግሞ ለፍርድ ይቀርባል። “ዘመኑ የይቅርታ እና የፍቅር ነው” በሚል እሳቤ ቅሊንጦ እና ዝዋይ የሚገባቸውን ሌቦች፤ በማክበር በጡረታ ስለሸኙዋቸው ብቻ መቀለድ ጀመሩ። ግዜውን ሳይዋጁ መቀለድ ደግሞ መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ህጻን ልጅም መገመት አያቅተውም።

መንጌ በአንድ ወቅት ካቢኔውን ሰብስቦ፡ “ወደዳችሁም ጠላችሁም፣ ይህ ሕዝብ የምትነዱትን መኪና፣ የምትኖሩትን ሕይወት፣ የምትኖሩበትን ቤት… ጠንቅቆ ያውቃል” ብሏቸው ነበር።አንዳንዶችዝቅ ብለው ሌሎች ደግሞ ከፍ ብለው ይብረሩ እንጂ፤ከሕዝብ ራዳር ውጭ ያለመሆናቸውን ገና የባነኑ አይመስልም።

ዛሬ ደርሰው ይህን ሲሉ፤ ይህ ግዜ የሚሉት ተረኛ በማማው ላይ ከፍ አርጎ ስላስቀመጣቸው ብቻ ሕዝብን በጅምላ ናቁት። ወገንም እያየ እንዳላየ፤ እየሰማ እንዳላዳመጠ እንጂ የጠጡትን ውስኪ፣ የዘረፉትን ዶላር፤ ምን ያህል እንደዘረፉ፣ ዶላሩን ያስቀመመጡበት ሃገር ጭምር ያውቃል። ይህ ሕዝብ ግዜ ይሰጠው ቅል አይነት እንዲያው ዝም ይበል እንጂ በነሱ የተገደለን ዜጋ ሁሉ፤ የተሰቃየ እና በግፍ የታሰረውን ሁሉ በቁጥርም ያውቀዋል።

እንደ ሞዴል አርሶ አደር “እውቅና ይሰጠን” አሉ። ጥሩ ጥያቄ ነው። ግን ምን አስቸኮላቸው። ግዜው ሲደርስ፤ ሪከርዳቸሁ ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ከፍሪደም ሃውስ ዳታቤዝ ውስጥ እየወጣ እውቅናውን ያከናንባቸው የለ?

ጥቂቶች ብቻ ይዘውሩት የነበረ መልህቅ አልባ መርከብ፤ በባሕር ሞገዶችና ከጎን በሚነፍሱ ወጀቦች ክፉኛ ሲወዘወዝ በግልጽ ይታያል።መርህ አልባ ያሉት ጉድኝት፤ ራሳቸውን ቆላልፎ ፍጹም ከማይወጡበት ማጥ ቢዶላቸውም፤ ካሁን በኋላ የኋሊዮሽ ሊመለስ ከቶም እንደማይሻ ግን ገና የተረዱት አይመስልም።

እርግጥ ነው። ህወሃቶች ተከፋፍለዋል። ስለዚህም ከሕዝብ ጋር በጀመሩት ሌባና ፖሊስ ጫዋታ ብዙ ሊገፉበት አልቻሉም።

“አውሬውን አቁስለነዋል!” ብለው ነበር ኦቦ ለማ መገርሳ። አውሬው ቲም ለማን መልሶ ለማጥቃት ቁስሉ እስኪሽርለት እንኳን አልጠበቀም።

የዘረፋ ቡድን መቀሌ ላይ መሽጎ ሲዶልት የነበረውን ሁሉ አደባባይ አውጥቶታል። በመቀሌው የግንቦት 20 የፓናል ውይይት ላይ ህላዌ ዮሴፍ፣ ጌታቸው ረዳና ስዩም መስፍን የተናገሩት አስደምሞን ሳያበቃ፤ እነሆ “ያሁኑ ይባስ” የሚያስብል መግለጫ ጀባ ብለውናል። አስቀድሞ በነ ህላዌ ዮሴፍ፤ በነ ስዩም መስፍን ማማሟቂያ ተለቀቀ። ህላዌ ዮሴፍ ቋንቋችንን ተቀማን፤ “ጽንፈኛ፣ ሽብርተኛ፣ አክራሪ፤ ወዘተ” ብለን ለመሳደብ የምንሳቀቅበት ዘመን ደረስን ሲል ነበር ያማረረው። ኢትዮጵያ ብለው ለመጥራት የሚጸየፏትን ሀገር ለሃያ ሰባት ዓመታት መግዛታቸው ሳያንስ፤ ሕዝቧ ላይ ለምን አልተሳለቅንም ሲሉ ቀለዱብን።

የህወሃቱ መግለጫ፤ በአንድ እጁ ጎራዴ በሌላ እጁ የመላእክትን ሰእል ይዞ እንደሚለምን ተመጽዋች አይነት ነው። በልመና ሃረጎች ታጭቋል። ኢህአዴግ ተሰብስቦ ይምከርም ይላል። አብዮታዊ ዲሞክራሲ ሳይሸራረፍ እንዲቀጥል በተማጽኖ ይጠይቅና እዚያው ላይ የጦርነት ጥሪ ሊያስተላልፍ ይሞክራል። “የትግራይ ህዝብን ሰላም ለመረበሽ እየተደረጉ ያሉት ፀረ ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሶች ህወሓት ከህዝቡ ጋር በመሆን በፅናት ለመታገል ወስኗል” ይለናል። በእርግጥ ደጀን ያሉት ትግራይ ሕዝብ ለነዚህ ቡድኖች የስልጣን ሱስ ብሎ ዳግም ልጆቹን ይገብራል ብለው ማሰባቸው ሕዝቡን መናቅ አይሆንም? ይህንን ሕዝብ ከስንቱ ጋር ሊያጋጩት አቅደው ይሆን?

በብሄራዊ ቴሌቭዥን ላይ የለቀቁትን ሰበር መግለጫ፤ “አንቺው ታመጭው አንቺው ታሮጪው” ሆነና ግራ አጋባን። ለመሆኑ ህወሃት ስንት ነው? የኢህአዴግ አባል ድርጅት ሆኖ የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ያስተላለፈው ህወሃት መቸም ከማርስ አልመጣም።

ጫወታው ወዲህ ነው። እነሱ ለመግደል የሞከሩትን ኢትዮጵያዊነት፤ እነሱ ያንቋሸሹትን የኢትዮጵያን ታሪክ፤ ቲም ለማ ከፍ አድርጎ ሲያነሳ እና ታሪኩን በደማቅ ቀለም ሲጽፍ፤ ፊታቸው ጠቆረ። አይናቸውም ደም ለበሰ። ሙስና እና ኪራይ ሰብሳቢ እያሉ ያሞካሹት የነበረ ስራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የተደራጀ ሌብነት” በሚል አደባባይ ላይ ሲሰጣ አላስደሰታቸውም። “ልማታዊ መስመራችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አደጋ ውስጥ የወደቀበት ሁኔታ ተፈጥሯል” ማለታቸው ይንን ያመላክታል። በሃገሪቱ ብሩህ ነገር መታየቱም አስጨንቋቸዋል፤ አመራሩ ከገዢነው ወደ መሪነት መቀየሩ አስደንግጧቸዋል።

የህወሃት መግለጫ በዶ/ር አብይ ላይ ብቻ ሳይሆን በሃገር ላይ የታወጀ ጦርነት ነው። ከአስር የማይበልጡ ሌቦች ያወጁት ጦርነት። የፍጻሜ ጦርነት።

መግለጫው ሲደመድም፤ “ወቅታዊ ሁኔታዉን በፍጥነት ለማየት እና ለመገምገም የኢህኣዴግ ስራ አስፈፃሚ እና ምክር ቤት አስቸኳይ ሰብሰባ እንዲጠራ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ይጠይቃል” ይላል።

ለዚህ ቀደም እንዲህ አይነት መግለጫ እንሰማ የነበረው ከተቃዋሚዎች ነበር። እነሆ ዘመን አልፎ ይህን ለቅሶ ከህወሃት ያስማን ጀመር። ተመስገን ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን አንድ መልካም እድል ገጥሞታል። ህወሃቶች ቢያውቁበት ይህ መልካም እድል እነሱንም ነጻ ያወጣቸው ነበር። ይህንን እድል በሁለት እጃቸው ከመቀበል ይልቅ ሲያጣጥሉት እና ሊያኮላሹ ሲሞክሩ ማየቱ የበለጠ ያሳምማል። አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል እንዲሉ፤ ይህንን ሕዝብ ባይፈታተኑት የሚበጃቸው ይሆናል።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Abduman says

    June 15, 2018 02:56 pm at 2:56 pm

    Perfect

    Reply
  2. Tadesse says

    June 15, 2018 08:37 pm at 8:37 pm

    I am worried about the people of Tigray kehezb gar atalut

    Reply
  3. jackal jackal says

    July 9, 2018 12:08 pm at 12:08 pm

    people and reality will win!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule