• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

‘አጃኢብ’ ያሰኘው የአዜብ መስፍን ወሬ

September 22, 2017 10:29 am by Editor 2 Comments

“አከ’ሲ” አለ ያገሬ ሰው፣ ከሰሞኑ ‘አጃኢብ’ ያሰኘውን የአዜብ መስፍን ወሬ ሲሰማ። አዜብ ልምድ ያላት ውሸታም እንጂ  ልምድ ያላት ኮሜዲያን አትመስልም ነበር። ከሚሚ ስብሃቱ ጋር በያዝነው ሳምንት የተወኑት ድራማ ግን ጦሽ አርጎ ያስቃል። መቼም ጥርስ እንጂ ልብ አይስቅ። ፈንድሻም’ኮ ልቧ እየተቃጠለ ነው ፊትዋ ሚፈካው።

ሴትየዋ አይኗን ሳይሆን ቅንድቧን በጨው አጥባ “ምንም የለኝም ግን ይወረስ” ነው የምትለው። መለስ የባንክ ደብተር ይቅርና መንጃ ፈቃድ እንኳ የለውም ስትል የቀለደችበት ወቅት ሩቅ አይደለም። እርግጥ ነው አዜብ በራስዋ ስም እንኳን ሕንጻ፣ ሲም ካርድም ሊኖራት አይችልም። ጥሩ ጋዜጠኛ አልገጠማትም እንጂ፣ ቢገጥማት፣ “እመኑኝ ልጃገረድ ነኝ!” ብላ እያለቀሰችም ቢሆን ለማሳመን ትሞክር ነበር። ልጆቼን እየተበደርኩ ነው የማስተምረው ብላ በተናገረች ሰሞን ኤ.ቢ.ሲ ኢንተርናሽናል የተባለው የማድሪድ ጋዜጣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአንድ ቀን የግል ግብይት ብቻ 1.5 ሚሊዮን ዶላር እንዳወጣች ዘግቦ ነበር።

የወዲ ስብሃቱ ልጅ አላማ ‘የሙስናዋን ንግስት’ ነጻ ለማውጣት መሞከር ባይሆን ኖሮ፣ በነካ እጅዋ ሰሞኑን በወደቀ ሂሳብ እየተቸበቸቡ ስላሉ የአዲስ አበባ ሕንጻዎች ጉዳይ ታነሳ ነበር።

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ጠቅልሎ  የያዘው ኤፈርት አናት ላይ ቁጭ ብላ “ምንም የለኝም” የሚል ነጠላ ቀልድ የለቀቀችው አዜብ 30 ሚሊዮን ብር  ከኪስዋ መዝዛ  ለመቀሌ ስፖርት ክለብ መለገስዋን እንኳ ረስታዋለች። ግብር የማይከፍልና የኦዲት ቁጥጥር የማይነካው ደጀና የተባለው የማፍያ ኩባንያ ከኤፈርት ጋር ተጣምሮ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ እኩሌታ ይዟል። ካፒታሉ አፍሪካ አንደኛ  የሆነው የዚህ ጥምር ዋና ሥራ አስፈጻሚ (CEO) ነኝ ብላናለች አዜብ። ሰማይ አይታረስ፣ ንጉስ አይከሰስ፣ ደሞዝ አይነገር … ደሞዝ አይጠየቅ! በዛሚ!

“ዛሚ ኤፍ.ኤም” ተብሎ በሚጠራው የነሚሚ ስብሀቱ ራዲዮ ጣቢያ ከዚህ ቀደም የሞራል ቀውስ ውስጥ ገብተው የሚዋኙ ትናንሾችን እያቀረበ፣ በደረቀ ፕሮፓጋንዳ  ብቻ ብዙ መጓዝ ባለመቻሉ፣ የፕሮግራም ለውጥ ያደረገ ይመስላል። እንደ አዜብ መስፍን አይነቱን ጥያቄና መልስ እያስጠና ተከታታይ ድራማ ማቅረብ ጀምረዋል። የመጀመርያው ሾው  በቴዲ አፍሮ  ተጀመረ ። ገድለው ሃውልት መስራት ለነሱ አዲስ ነገር አይደለምና ጸሃይ የሞቀውን “እርምጃው ፍትሃዊ አይደለም” እንቶፈንቶ ደጋገመችው። የቴዲ አፍሮን የአልበም ምረቃ ያገደውን ስውር እጅ  አደባብሳ አለፈችው። ስለማታውቀው  ፍትህ እና መብት መለፈፍዋ ግን ብዙዎችን ሳያስደምም አልቀረም።

አዜብ በተከታዩ ክፍል ብቅ ብላ፣ “የምተዳደረው በዶሞዝ ነው። መለስም፣ እኔም፣ ልጆቼም ሃፍት የላቸውም” አለችን።

“ውልና ማስረጃ የሌለው ሃፍት ካላኝ ቦታውን ያሳዩኝ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ልመልሰው” የሚለው ሕጻን ልጅን እንኳ የማያሳምን አባባልዋ ትንሽ ያስቃል። ሕዝብ በደቦ ወጥቶ የአዜብና ዘመዶችዋን ያልተመዘገበ ንብረት እንዲያፈላልግላት መጠየቅዋ ነው ወይንስ የእሷም ህንጻዎች እንደ ኮንዶሚኒየሙ “ጠፍተዋል” ብለው ነገሯት? ከሠበታ የወሰደችው 1200 ሄክታር መሬት የቀብርዋ ስፍራ መሆኑ ነው። ይህ ደግሞ በነሱ ቋንቋ ሙስና አይባልም። ሙስናም ቢሆን ለከባባድ ሚዛን የህወሃት አባላት የአገልግሎት ስጦታ ነው። አቶ አያሌው መንገሻ፣ የቀድሞው የደህንነት መ/ቤት ሹም ህብር ሬዲዮ ላይ ቀርበው በሰጡት ቃለ ምልልስ “በሕወሃት ሙስና ወንጀል አይደለም” ብለውናል።

ኮሜዲያን ወደ ውጭ ሲሰደዱ፣ ፖለቲከኞቹ  ቦታቸውን ይዘዋል ልበል? ከሰሞኑ የህወሃት ካድሬዎች እንደጉድ መቀለድ ጀምረዋል። አዜብ እና ከሚሚ ተደራጅተው የሰሩት ይህ  እየሳቁ-ማንባት ተውኔት ግን ከኮሜዲ መስመር ወጣ ይላል።

ቃለ-ምልልሱ የተጠና ላለማስመሰል እንኳ አለመሞከራቸው፣ ለአድማጭ ያላቸውን ንቀት ያሳያል። “መኖርያ ቤት ሰርተሻል?” የሚለው የመጀመርያ ጥያቄ ሲቀርብላት ነበር፣ አዜብ “ከሌላው ጋር አብሬ ልመልሰው” ስትል ተከታዩን ጥያቄም እንደምታውቀው ያስፎገረችው። መዋሸት አንድ ነገር ነው። ውሸት ለማስመሰል መቻል ደግሞ ማወቅን ይጠይቃል። ይህንን እንኳን ማድረግ አልቻሉም። የዛሚዋ ካድሬ ሚሚ ስብሃቱ አዜብን ለማንጻት ብዙ የታከከች ይመስላል – ለዛሬ ባይሳካም።

አዜብ እውቀት ነጻ ትሁን እንጂ፣ በጣም ደፋር ናት። የእንግሊዝን መንግስትንም ሆነ የአውሮፓ ህብረትን ብትጠይቁ ምንም የሌለኝ  ድሃ መሆኔን ይነግሯችኋል ትለናለች። አዜብ ሃብታም ግን የምትሆነው ህወሃት ወይንም ኤፈርት ሲለቅቃት ብቻ ነው። “ድርጅቴ ሲለቅቀኝ በግሌ ከጉልት ንግድ በመጀመር ሃብታም ሆናለሁ” ስትል አስቃናለች።

ይህንን ያድርግልሽ ብለናል!

ክንፉ አሰፋ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    September 26, 2017 09:46 pm at 9:46 pm

    ——– ታጋይቷ አልሰሙም ? “ኀይለመለስ ከአማራ ክልል በስተቀር ሁሉም ክልሎች ወርቅ በሰፌድ ይነጠራል ” በወይልቃይት አማራነትዎ አንድ ሰፌድ አልሰፉም ? ወይስ ሰፌድ መግዣ የለዎትም? አለዚያም ጥሩ ጎረቤት የለዎትም ? ምን አልባት የመለስ ወንድም ጢቢኛ ሲሸጥ፡ እህቱ ጠላ ስትሸጥ ፡እርስዎ ጉልት ቸርቻሪ መሆን ያማረዎት ፓርቲዬ አለቅም አለኝ ትወና ህወሃት ሥራ አይንቅም ድልድይ ማፍረስ፡ ባንክ መዝረፍም፡ የዕርዳታየለዎትም፡፡፡፡ሙስናም የተካነበት ፍጥረቱ አደለም እንዴ? ዋሸሁ?
    ______ “የምተዳደረው በዶሞዝ ነው። መለስም፣ እኔም፣ ልጆቼም (ሃፍት )የላቸውም አለችን። ኤ.ቢ.ሲ ኢንተርናሽናል የተባለው የማድሪድ ጋዜጣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአንድ ቀን የግል ግብይት ብቻ 1.5 ሚሊዮን ዶላር እንዳወጣች ዘግቦ ነበር።”

    ” አዜብ እውቀት ነጻ ትሁን እንጂ፣ በጣም ደፋር ናት። የእንግሊዝን መንግስትንም ሆነ የአውሮፓ ህብረትን ብትጠይቁ ምንም የሌለኝ ድሃ መሆኔን ይነግሯችኋል ትለናለች። አዜብ ሃብታም ግን የምትሆነው ህወሃት ወይንም ኤፈርት ሲለቅቃት ብቻ ነው። “ድርጅቴ ሲለቅቀኝ በግሌ ከጉልት ንግድ በመጀመር ሃብታም ሆናለሁ”… ይህንን ያድርግልሽ ብለናል!

    _____ “የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ጠቅልሎ የያዘው ኤፈርት አናት ላይ ቁጭ ብላ “ምንም የለኝም” የሚል ነጠላ ቀልድ የለቀቀችው አዜብ 30 ሚሊዮን ብር ከኪስዋ መዝዛ ለመቀሌ ስፖርት ክለብ መለገስዋን እንኳ ረስታዋለች። ግብር የማይከፍልና የኦዲት ቁጥጥር የማይነካው ደጀና የተባለው የማፍያ ኩባንያ ከኤፈርት ጋር ተጣምሮ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ እኩሌታ ይዟል። ካፒታሉ አፍሪካ አንደኛ የሆነው የዚህ ጥምር CEO ነኝ ብላናለች አዜብ። ውልና ማስረጃ የሌለው ሃፍት ካላኝ ቦታውን ያሳዩኝ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ልመልሰው” ስትል አስቃናለች።” ሕዝብ የወርቆቹ ሲሆን ቦርቃቃው ብሔር ብሔረሰብ ግን ለጭፈራ እንጂ ለሀፍት ውርስ እንኳ ቦታ የለውም ማንነቱን የጣለ ሀፍት ይጠይቃልን? ወ /ሮ አዜብ ቤት አለዎት?ከአስረኛ እና ጎላ ከጥሊያን ወረራ ግዜ በሹምባሽነት የተሸለሙት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ሀፍት በገዢውና አውራው ፓርቲ ተራራውን ላንቀጠቀጡ በውልና ማስረጃ አፀደቀላቸው!?
    *************!
    “ቀዳማዊት እመቤት አትበሉኝ ” ! ያ …ማለት የአቶ እከሌ ሚስት ለማለት ነው ። ታጋይ አዜብ መስፍን( ጎላ ) በሉኝ ሲሉ ለዚህ ኮራጅ ትውልድ ማረሚያ ሰጡ ምንስ ቢሆን ወልቃይት ተከዜን ሳይሻገሩ ለአማርኛ አይቀርብምን!?
    “ተመዝግቦ በነፃ የታደላችሁ ሀብትና መሬት ስንት ነው ? ብሎ የሚጠይቅ የለም፡ ይህ ሕዝባቸው ማንነቱን ያወቀው እና የተፈጠረው በሕወሓት መልካም ፈቃድ ነው ። ” ከውጭ ይዘነው የመጣነውን ገንዘብ ሌላ ሀገር ኢንቨስት ከማድረግ ለአማራና ኦሮሞ ትንሽ ትንሽ በጭቀንላቸዋል ። ለመሆኑ የኢፈርትን ገንዘብ የሚጠይቀው ምን ሰው ? ማለቴ ሰው ስል የተማረ ማለቴ ነው”ዶክተር ስብሃት ነጋ
    ** የሚደግፋቸው ፹ከመቶ ገበሬ ስላልተማረ ሰው አደለም !። ማንነትህን በፍቃደኝነት ለቀህ ሀገርህን በክልል ለውጠው የበይ ተመልካች ፡ቤተ ሙከራ፡ ሆነህ ለጭፈራ ተጠራርቶ ተገፋትሮ የሚመጣ፡ የልዩ ጥቅማጥቅም ምርኮኛ ሕዝብ፡ የእርዳታ ንፍሮ እየነፋ በተውሶ ልብስና የፀሐይ መነፅር ተወጥሮ የአዞ ዕንባ :ልሃጭና ንፍጡን ባዶ ሳጥን ላይ ሲያዝረከርክ ቤተመንግሥት ቁጭ ብለው አድርባይ ! እያሉ ተሳልቀዋል አሁን ቢኮምኩ ብርቅ ነው ? ጠቅላዩ ባለቤታቸው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦችን ቀልድና ተረት ጨርሰው የቻይና ተረትና አባባል ፓርላማ መኮመክ ሲጀምሩ ጠቀለሏቸው።ህወሓት ኢህአዴግና ኢፈርት በመለስ ዜናዊ ቤተሰብ ጭንቅላት ብቻ እየተመራ ሌላው ሎሌ መሃይም ነው ማለት አደለምን ?ለመሆኑ የመንገድ ላይ ነዋሪ ልጆች እና ባለቤታቸውን ተማምነው ሀፍት ንብረታቸውን ገጠር ተነጥቀው ቤተመንግሥት መንገድ ዳር የወደቁትን ብሔር ብሔረሰቦች እንደምን አደረጓቸው ? እነሱ ሀፍት አካብተው መለስ ቤተሰብ ላይ የተነሱትን ሥም አጥፊ፡ የሙሰኞች ቡድን እንዳለ አያወቁ እስከ ዛሬ ለኢትዮጵያ ሕዝባቸው ለምን አላጋለጡም ? አስገደ እና ገብረመድህን የተባሉትን ዛር ቀስቃሽ አስጓሪ ይላክባቸው !!።
    ዘይገርም…

    Reply
  2. balcha says

    October 2, 2017 03:58 pm at 3:58 pm

    Azeb and aba sebhat nega are clue less but clue givers. Lie is there moto and arrogance is there identity. They are all lucky because they are in Ethiopia, if they were some where else, it could have been a different story.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule