ባለፈው እሁድ በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራውንና በሰላም የተጠናቀቀውን ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ግልጽ ደብዳቤ ላኩ፡፡ በደብዳቤው ላይ ኢህአዴግ ሰልፈኞቹንም ሆነ የፓርቲውን አመራሮች ለማሠር የሚያደርገውን ሃሳብ ከመፈጸም እንዲቆጠብ ማስጠንቀቂያ ልከዋል፡፡ አቶ ኦባንግ በደብዳቤያቸው ላይ በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሱ ሲሆን በቅድሚያ ግን ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ሠልፉን በመፍቀዳቸው ሊመሰገኑ እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡ ይህንንም በማድረግ ከቀድሞው መሪ መለስ እንደሚለዩና ምናልባትም ህዝብን ለማዳመጥ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቋሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምክንያቱንም ሲያስረዱ መለስ በእንደዚህ ዓይነቱ ሠልፈኞች ላይ የህወሓት አልሞ ተኳሾች ተኩስ በመክፈት እንዲገደሉ ማድረገቸውና የፓርቲ አመራሮችን … [Read more...] about ኦባንግ ለኃይለማርያም ግልጽ ደብዳቤ ላኩ
“ይህ መንግሥት አይመጥነንም”
ሰሞኑን ኢትዮጵያ የዓለም መገናኛ አጀንዳ ሆናለች። ለዘመናት እጇን ኢትዮጵያ ላይ ተክላ የኖረችው ግብጽ የምትዝተው ዛቻና፣ በቅርቡ ተቋቁሞ ታላቅ ታሪክ በማስመዝገቡ የተረጋገጠለት ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ አጀንዳዎቹ ናቸው። በወጣት አመራሮች የተገነባውና በርካታ ሴት አባላት እንዳሉት የሚነገርለት ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በዋናነት የተገኘው ድል የፍርሃት ደመና መገፈፉ ነው። አቶ መለስ ባስተላለፉት ትዕዛዝ በ1997 ዓ.ም ዜጎች አልመው በሚተኩሱ የአጋዚና ታማኝ የህወሃት አባሎች ደረትና አናታቸው እየተወጋ እንዲገደሉ ከተደረገ በኋላ የተቃውሞ ሰልፍ የማይታሰብ ሆኖ ላላፉት ስምንት ዓመታት ቆይቶ ነበር። ከዳር እስከዳር ድምጽ አልባ ሆኖ የተሸነፈው ኢህአዴግ በጠመንጃ ፣ በወቅቱ የነበሩት የቅንጅት አመራሮች ታሪካዊና ሊረሳ የማይችል ስህተት ተዳምረው የህዝቡን … [Read more...] about “ይህ መንግሥት አይመጥነንም”
በሰላማዊ ሠልፉ ሰማያዊ ፓርቲና መንግሥት እየተወዛገቡ ነው
ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድ ወር በፊት በጠራውና ባለፈው እሑድ የተደረገውን ሰላማዊ ሠልፍ መንግሥት ሲያወግዝ፣ ሰላማዊ ፓርቲ ደግሞ የመንግሥት ውግዘት በተቃውሞ የተነሳውን ሕዝብ ከማሸማቀቅ ባለፈ የሕግ ድጋፍ እንደሌለው እየገለጸ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዝያ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ባስተላለፈው የሰላማዊ ሠልፍ ጥሪ፣ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጐች ወጥተው ተሰተውለዋል፡፡ አራት ኪሎ ቀበና አካባቢ ከሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት መነሻውን ያደረገው ሰላማዊ ሠልፉ በአራት ኪሎ፣ በፒያሳና በቸርችል ጐዳና አድርጐ ኢትዮ ኩባ የወዳጅነት መናፈሻ ደርሶ፣ እስከ ቀኑ ስምንት ሰዓት ድረስ የተለያዩ መፈክሮችንና ተቃውሞዎችን በመንግሥት፣ በመንግሥት መገናኛ ብዙኅንና በአንዳንድ የግል መገናኛ ብዙኅን ላይ አሰምተዋል፡፡ ሠልፈኞቹ ለመንግሥት ካቀረቧቸው ጥያቄዎችና መፈክሮች … [Read more...] about በሰላማዊ ሠልፉ ሰማያዊ ፓርቲና መንግሥት እየተወዛገቡ ነው
ዶ/ር አበራ ጀምበሬ ትዝታዬና መጽሐፉ
ዛሬ ብቻ ኖረው - በዛሬ ያልቀሩ ነገንም አስበው - ለነገ የሠሩ ለራሳቸው ሳይሆን - ለህዝብ የኖሩ ግዴታ ሆነና ሞት - ቢሆን ዕጣቸው ሲበራ ይኖራል - አይጠፋም ሐቃቸው ግጥም - አስራት ዳምጠው በስድስተኛ ዓመቴ መጨረሻ ግድም አንድ ቀይ እንግዳ እቤታችን መጣ። ከናትና አባቴ ጋር ሆኜ ከሰውየው ጋር የመቀመጥ እድል አገኘሁ። ቀዩ ሰውዬ ሳቂታ ፊት፣ የሚቁለጨለጩ አይኖች፣ ሰልካካ አፍንጫና፣ የሞሉ ጉንጮች አሉት።ያም ሆኖ ሙሉ ፊቱ ስትታይ አነስተኛ ነች። ይህን ሰው ከዛን ቀን በፊት ስለማወቄ እርግጠኛ አይደለሁም። እንኳን እሱን ሌሎች አብረውኝ ያሉትንም ዝምድናቸውን ለይቼ ለመናገር እቸገራለሁ። ያን ቀን ያንን ሰው አይነ ህሊናዬን ምን እንዳበራው አላውቅም ቀረብኩት። አንድ አይነት የሚያስተሳስረን ነገር እንዳለን ገባኝ። ነፍስ ማወቅ ይሄ ይሆን? ይሄ ካልሆነ ሌላ ምንም … [Read more...] about ዶ/ር አበራ ጀምበሬ ትዝታዬና መጽሐፉ
ምርመራው ወደ አቃብያነህጉ ተዛወረ!
* “አዲስ ነገር የለም” ጸረ ሙስና ኮሚሽን በተለያዩ ከፍተኛ ወንጀሎች በተጠረጠሩ ሰዎች ላይ የተከፈቱ ክሶችን በማፈንና በመመሪያ ፍትህ በማዛባትና በማቋረጥ ወንጀል የተጠረጠሩ አቃቤያነህግ ላይ ምርመራ መጀመሩ ከፍተኛ ድንጋጤ መፍጠሩ ተሰማ። በተለይም ከወንጀል ጋር ቁርኝት እንዳላቸው በህዝብ የሚታወቁ ክፍሎች ክፉኛ መደናገጣቸው ተሰምቷል። በሙስና የተጠረጠሩት የጉምሩክ ባለስልጣናት፣ ተባባሪ ነጋዴዎችና ደላሎች መታሰራቸውን ተከትሎ ከተፈጠረው ስሜት በላይ ከፍተኛ መደናገጥ የፈጠረው ዜና አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅዳሜ እለት ለንባብ ያበቃው ዜና ነው። በቅርቡ ከሃላፊነታቸው የተነሱት የፍትህ ሚኒስትር አቶ ብርሀነ ሃይሉና ከአስር በላይ አቃብያነህግ በተለያዩ ጉዳዮች የተመሰረቱ ክሶች እንዲቋረጡ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው መመርመራቸው በትክክል ከተሰራበት ዋንኛ የሚባሉትን የሙስና ወንጀል … [Read more...] about ምርመራው ወደ አቃብያነህጉ ተዛወረ!
በህዝብ አቆጣጠር አሁን ጨዋታው ተጀመረ!
ሙስናው ላይ የተጀመረው ዘመቻ ሙስናን በስንጥር የሚያሰኝ ቢሆንም አቶ መለስ ያልደፈሩትን ሰፈር አቶ ሃይለማርያም ነክተውታልና በኢህአዴግ ታሪክ የሙስናን ሰፈር በማንኳኳት ግንባር ቀደሙ ሰው ያደርጋቸዋል። እኛም ጅምሩ መልካም ነው እንላለን። ግን ጥያቄም ማሳሰቢያም አለን። ለማንኛውም በህዝብ አቆጣጠር አሁን ጨዋታው የተጀመረ ይመስለናል። በሙስና የተጠረጠሩ ነጋዴዎች፣ ደላሎች፣ አቀባባይ የተባሉና የመንግስት ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ከተሰማ ጀምሮ ህዝብ በስፋት እየተቸ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የተደላደለውን ሙስና ህዝብ ጠንቅቆ ከነባለቤቶቹ ያውቃል። ይረዳል። ያሸታል። ባለፈ ባገደመ ቁጥር ለድህነቱ ማስታገሻ ያላምጣቸዋል። ሙስና ሲባል ሙስና ነው። ወንጀል ሲባል ወንጀል ነው። ህግ መተላለፍ ያስጠይቃል። አሁን እንደሚታየው ግን የጸረ ሙስናው ዘመቻ ሰፈር የለየ ይመስላል። ዋናዎቹ … [Read more...] about በህዝብ አቆጣጠር አሁን ጨዋታው ተጀመረ!
ከእሁድ እስከ እሁድ
ከእስረኞች ጠበቆች ጋር የተደረገው ውይይት ታፈነ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ከአሜሪካ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመሆን በኢትዮጵያ እስር ቤት ለሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ አስረኞች ጥብቅና ከቆሙ የህግ ባለሙያዎች ጋር ለመነጋገር ያደረገው ሙከራ ታፈነ። የጋራ ንቅናቄው ለጎልጉል እንዳስታወቀው ዓርብ ሰባት ከሚሆኑ ጠበቆች ጋር ለመያየትና መረጃ ለመለዋወጥ መስመር ተዘርግቶ ነበር። አቶ ኦባንግ ሜቶና የጋራ ንቅናቄው የሚዲያ ዴስክ፣ ከአሜሪካ የጠበቆች ማህበር አራት፣ ከአዲስ አበባ ሰባት ጠበቆች በመሆን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 11 ሰዓት ላይ የስካይፕ ውይይት ለመጀመር ተዘጋጅተው ነበር። የጋራ ንቅናቄው እንዳስታወቀው ውይይቱ ሲጀመር ድምጽ መስማት አልተቻለም። በዚሁ ሳቢያ ውይይቱ መቋረጡን ያስታወቀው አኢጋን ከአሜሪካ የጠበቆች ማህበር ጋር በመነጋገር ሰኞ ቀን … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ ትግል – ቁጥር 01
ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ካለምንም እንከን ተጠናቀቀ። አምባገነን መለስ ዜናዊ ከግንቦት 8 ቀን 1997 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በሽብርተኛ ህጎቹ እና ተግባሮቹ የገነባው የፍርሃት ፖለቲካ ህንጻ ፈረሰ። በዚኹ እለት የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች ማዕከል በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ መስኮች መፈጸም አለባቸው የሚላቸውን እርማቶች በንግግሮች እና በመፈክሮች በአደባባይ አስታወቀ። እነሱም ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው ሊቀርቡ ይችላሉ፥ “መብት መጠየቅ ወንጀል አይደለም፣ ነፃነት እንሻለን፤ ፍትህ እንሻለን፤ አንለያይም፤ የህሊና፣ የሃይማኖት እና ሌሎች ፖለቲከኛ እስረኞች ይፈቱ፤ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች ይመለሱ፤ በአገራችን ሰላም አጣን፤ ልማት እያሉ ሙስና ሰሩ፤ በኑሮ ውድነት የጎበጠው ትከሻችን እረፍት ይሻል፤ ህዝብ ማፈናቀል የዘር ማጥራት ወንጀል … [Read more...] about የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ ትግል – ቁጥር 01
ኃያሉ አሜሪካ፤ የሞትህ ትዝታ በኢማኑዔል ቶድ
በፈረንሣዩ የታሪክና የህዝብ ቁጥር ዕድገት (Demography) ተመራማሪ በኢማኑዔል ቶድ (Emmanuele Todd) የተደረሰው መጽሀፍ ከሶቪየት ህብረት አገዛዝ መገርሰስ ወዲህ የቀረውና ብቸኛው ኃያል መንግሥት የሚባለውን የአሜሪካንን የበላይነት መቦርቦርና ውድቀት የሚያሳይ የ252 ገጽ መጽሀፍ ነው፡፡ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ኃያሉ አሜሪካ፤ የሞትህ ትዝታ በኢማኑዔል ቶድ
እኛ ያልነው ለፉገራ…
በሰሞኑ ቀልድ ልጀምር። የአፈሪካ ህብረት ድርጅት 50ኛ አመቱን በያዝነው ሳምንት በአዲስ አበባ ሲያከብር በነበረው የሻምፓኝ ስነ-ስርዓት ላይ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ብቻ ከመሪዎቹ ተነጥለው ያለ ብርጭቆ ቆመዋል። ለፕሮቶኮል እንዲመሳሰሉ ቢጠየቁ አሻፈረኝ አሉ። የህብረቱ የወቅቱ ሊቀመንበር ስለነበሩ ለይሰሙላ እንኳን ብርጭቆዋን ጨብጡ ቢባሉ አይሆንም፣ ሃይማኖቴ አይፈቅድም አሉ። በመጨረሻ ግን በረከት ስምዖን በጆሯቸው አንዳች ነገር ነገራቸውና የያዘውን ብርጭቆ ሲሰጣቸው ተቀብለው በደስታ ጨለጡት። በረከት ለጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ በጆሯቸው እንዲህ ነበር ያላቸው። "ብርጭቆ ውስጥ ያለው መለስ የጀመረው ወይን ነው።" አሁን አሁን መቀለጃ እየሆኑ የመጡት ሃይለማርያም ደሳለኝ፤ መለስ የጀመረውን ሁሉ፤ ፉገራም ቢሆን - ያንን ለመጨረስ ነው የተቀመጥኩት ይሉናል። እየደጋገሙ! ብርኖ … [Read more...] about እኛ ያልነው ለፉገራ…










