ፍቅር ታሞ ከርሞ አልጋ ላይ እንደሰው ብዙ ዘመን ሆነ ሞቶ ከቀበርነው ይሄ ሆኖ እያለ ሞቱን እያወቅን ለአያሌ ዓመታት ዘፋኞች በዘፈን አሁንም እንዳለ ህይወት እስትንፋሱ ጨርሶ እንዳልሞተ እንዳልወጣች ነፍሱ አድርገው ሲዘፍኑ ሲያቀብሉን ውሸት ነገሩን ዋጥ አድርገን አብረን ጨፈርንበት ከሁሉ ‘ሚገርመው የሚደንቀው ነገር አለ የሚባለው የአሁን ዘመን ፍቅር ገንዘብን ውሃልክ አ’ርጎ ተመስርቶ በዓይናችን እያየን መካካዱ ከፍቶ ዘፋኙ ተነስቶ ሲለን ፍቅር ፍቅር በሆታ በስክስታ የኛ አብሮ ማጫፈር ከ «እማትበላ ወፍ»«እዘበናኝ» ድረስ ሆዴ አንጀቴ እያለ ተሸክሞ እንደ ውርስ ወጣቱም ያንኑ ሲያማስል ሲያቁላላ ስለከረመበት ሳይቀይር በሌላ ያወጣው ሙዚቃ ሳይሰማ ጣፍጦ ዘፈኑ ይሞታል ዘፋኙ ተቀምጦ ይህ ሁሉ ሲሰራ ይህ ሁሉ ሲፈጠር እስከዛሬ ቆየን ምንም … [Read more...] about ልዩ ጥበብ ገንባ
የኢትዮጵያዊያን ማሕበር በሆላንድ
መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብሎ ሞተ
መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ፣ ይቅናችሁ ማለት ነው፤ ለልማት ለሚሰማሩ ሰዎች ምርቃት ይሆናል፤ ለጥፋት ለሚሰማሩ ሰዎች እርግማን ነው፤ እርግማን ብቻም አይደለም፤ የጥፋት ምኞትም ነው፤ ሰዎች ለጦርነት ሲዘጋጁ፣ ሰዎች ሌሎች ሰዎችን ለመግደል ሲሰናዱ፣ ሰዎች እርስበርሳቸው ለመገዳደል ጦራቸውን ሲስሉ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ማለት ከጀግና አንደበት የሚወጣ አይደለም፤ ብዙ ሰዎች ለእንጀራ ብለው ሕይወታቸውን ወደአጥርነት ለውጠው ሕይወቱን የሚጠብቁለት ሰው ጦር ቢወረወር አይደርስብኝም ብሎ ሌሎችን ለሞት ቢዳርግ አይደንቅም ይሆናል፤ አጥሩን ጥሶ ወደሱ የሚገሰግስ ሞት ሲያይ ቢፈረጥጥም አያስደንቅም፤ ሆኖም የሞት መንገድ ከጎን ብቻ ሳይሆን ከላይም ሊሆን እንደሚችል አለማወቁ ቀላል አለማወቅ አይባልም፡፡ ባህላችን ገዳይን የምናከብር፣ ለገዳይ የምንዘፍን ሕዝብ ቢያደርገንም፣ በድንቁርና ዘመን … [Read more...] about መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብሎ ሞተ
ሃራም ቦኮ ሃራም – ሃራም አልሸባብ
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአፍሪካውያንን ህልውና እየተፈታተኑ ካሉ ጉልህ ችግሮች መካከል ኣሸባሪነት ዋና ጉዳይ ሆኗል። ISIL በሊቢያ፣ ኣልሸባብ በምስራቅ ኣፍሪካ፣ ቦኮሃራም በምእራብ ኣፍሪካ በከባድ ፍጥነት እያደጉ ነው። አፍሪካውያን ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ በሽብር ስራዎች ላይ የተባበረ ክንዳቸውን ሊያነሱ የሚገባበት፣ ህዝቦች ግንዛቤያቸውን በማስፋትና የዚህን ኣሸባሪ መንፈስ ሊዋጉ የሚገባበት ሰዓት ላይ ነንና እኛ ኢትዮጵያውያን በዚህ ጉዳይ ላይ በጽኑ መወያየት ያሻናል። በተለይ ወጣቱ በኣህጉራችን ስላለው የሽብር እንቅስቃሴ በሚገባ ሊረዳ ይገባዋል:: መምህራን አፍሪካ ውስጥ ስላጠላው የሽብር ጥላ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ኖሯቸው ተማሪዎቻቸውን ሊያስተምሩ ይገባል። ወደ ዋናው ውይይታችን እናምራ። ስለ ሽብርተኞች ሲነሳ የሚነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎች ይኖራሉ። ለመሆኑ እነዚህ ኣሸባሪ ቡድኖች ምንድነው … [Read more...] about ሃራም ቦኮ ሃራም – ሃራም አልሸባብ
“ሙዚቃ መምራትን ለዓለም ያስተዋወቀችው ኢትዮጵያ ናት”
ሙዚቃን በተለየ መንገድ በማዋሐድ ሙላቱ አስታጥቄ የሙዚቃ ሳይንቲስት መሆኑን በአምስት አሠርታት የሙዚቃ ጉዞው ውስጥ አስመስክሯል፡፡ የተለያዩ ቅላፄዎችንና ምቶችን ከተለያዩ አፍሪካ አገሮች፣ አሜሪካና አውሮፓ ሙዚቃ በመውሰድና በማጣመር አዲስ የሆነ ሙዚቃንም ለዓለም አበርክቷል፡፡ የኢትዮ ጃዝ ፈጣሪው ሙላቱ አስታጥቄ የሙዚቃ ትምህርቱን ያጠናው በለንደን፣ ኒውዮርክና ቦስተን ከተሞች ሲሆን፣ የራሱን የሆነ የሙዚቃ ስልት ከኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅኝቶች ጋር አጣምሮ ኢትዮ ጃዝን ፈጥሯል፡፡ በቀላሉ በዓለም አቀፍ ሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ ጆሮ ማግኘት የቻለው ሙላቱ ከመቶ ሺሕ በላይ የሚሆኑ ታዳሚዎችም ኮንሠርቱን ለማየት መሽቀዳደም የተለመደ ሆኗል፡፡ ከሙዚቃ ክህሎቱም በተጨማሪ በጥንታዊ ሙዚቃዎች ላይ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ምርምሮችንም በማካሄድ ነው፡፡ የአምስት አሠርታት የሙዚቃ ጉዞውንም በተመለከተ ከሪፖርተሩ … [Read more...] about “ሙዚቃ መምራትን ለዓለም ያስተዋወቀችው ኢትዮጵያ ናት”
እግርና ጫማ
እግርና ጫማ ተጣብቀው አንድ ላይ በክር ተሳስረው አብረው ውለው ስታይ እውነት አይምሰልህ ያ ሁሉ ፍቅራቸው ሲመሽ ወደማታ ሄደህ ብታያቸው በአንሶላ መካከል እግር ተዘርግቶ ጫማ በራፉ ላይ ወድቋል አፉን ከፍቶ! … [Read more...] about እግርና ጫማ
“እንተያያለን አስክሬንህ ነው የሚወጣው” የህወሃት አሸባሪዎች
* "በክፉ ጊዜ የከዱን አሉ፤ ለእነሱም ፈጣሪ ልቦና ይስጣቸው" "የመጣሁት ከትግል እንጂ ከሽርሽር አይደለም" ይላሉ ዳንኤል ሺበሺ! የቀድሞው አንድት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ኃላፊና የደቡብ ቀጠና ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበረ ሲሆን ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ ላለፉት 22 ወራት በእስር ላይ ቆይተው ባለፈው ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ከእሥር ተፈትተዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ አየር ጤና አካባ በተለምዶ ቻይና ካምፕ በተሰኘው የአቶ ዳንኤል መኖሪያ ቤት ተገኝታ በእስር ቆይታቸው ስላሳለፏቸው ነገሮች፣ ስለወደፊት ሀሳባቸውና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ተከታዩን ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ እንዴትና በምን ሁኔታ ነበር የተያዙት? የተያዝኩት ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በተለምዶ ጀርመን አደባባይ … [Read more...] about “እንተያያለን አስክሬንህ ነው የሚወጣው” የህወሃት አሸባሪዎች
የጀርመን ኤምባሲ ትግርኛን ቅድመ መስፈርት ያደረገ የስራ ማስታወቂያ አወጣ
ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው የጀርመን ኤምባሲ የትግርኛ ቋንቋን ቁልፍ ቅድመ መስፍርት የሚያደርግ ክፍት የስራ ማስታወቂያ አዲስ አበባ ለሚገኘው ጽህፈት ቤቱ አወጣ። ትግርኛ ዋና መስፈርት የሆነበት ምክንያት ይፋ አለመደረጉ ጥያቄ አስነስቷል። ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች የኤምባሲው ተግባር የኢትዮጵያውያንን እኩልነትን ከህወሃት በላይ ያንቋሸሸ ነው ብለውታል፡፡ ኤምባሲው ማብራሪያ እንዲሰጥ ይጠበቃል። ኢምባሲው በድረገጹ ሜይ 4 ቀን 2016 ያወጣው ማስታወቂያ የሚፈልገው ባለሙያ የቪዛ ማመልከቻ ስራን የሚያመቻች፣ የሚያረጋግጥ፣ ቪዛ ነክ ጉዳዮችን አስመልክቶ የቃልና የጸሁፍ መረጃዎችን የሚሰጥ፣ የቪዛ ክፍያን የሚፈጽምና የመዝግብ አያያዝ ስራን የሚያከናውን እንደሆነ ያረጋግጣል። የስራው ቦታ ከአዲስ አበባ ውጪ ስለመሆኑ የሚለው ነገር የለም። ማስታወቂያውን የተመለከቱ ወገኖችን ያነጋገረውም … [Read more...] about የጀርመን ኤምባሲ ትግርኛን ቅድመ መስፈርት ያደረገ የስራ ማስታወቂያ አወጣ
“አፋልጉን ማስታወቂያ! 88 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ብሎኮች ጠፍተዋል” ህወሃት
ዜጎች “አሸባሪ” እየተባሉ በሚታፈኑባት፣ በሚገደሉባት፣ የደረሱበት በሚጠፉባት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በሚገዛት ኢትዮጵያ ሰሞኑን “88 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ብሎኮች” “ጠፍተዋል” እየተባለ በሰፊው እየተናፈሰ ከመሆኑ አልፎ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የህወሃት ሹመኛ መኩሪያ ኃይሌ በህወሃት ለተሰየመው የኢህአዴግ ምክርቤት (ወግ እንዳይቀር “ፓርላማ” በሚባለው) ቀርበው ስለነዚህ “ጠፉ” ስለተባሉ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ምንም አስተያየትም ሆነ ዘገባ ሳያቀርቡ እንደ ካኔተራ ውልቅ ብለው ሊወጡ ሲሉ፤ ምናልባትም ቤቶቹ የጠፉባቸው “የፓርላማው” አባላት ሊሆኑ ይችላሉ፤ “የገባህበት ገብተህ ታመጣታለህ” የሚል እንደምታ ያለው ቀጭን ትዕዛዝ ለመኩሪያ ሰጥተው ሸኝተዋቸዋል፡፡ ከዜጋ እስከ ወርቅ የሚጠፉበት ህወሃት አሁን ደግሞ ብዙ ኮንዶሚኒየሞች ጠፍተውበታል፡፡ ወሮታው ምን እንደሆነ … [Read more...] about “አፋልጉን ማስታወቂያ! 88 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ብሎኮች ጠፍተዋል” ህወሃት
ዘ-ፀዓት! . . . . ውጣ!
ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1500 ዓመተ ዓለም አንድ የነጻነት መሪ ነበር። በዘመናዊ የማኔጅመንት ትምህርት ውስጥ የስራ ክፍፍልን የፈጠረና መሰረት የጣለ ትልቅ ሰው ነው። ይህ ሰው የተወለደው በጭንቅ ሰዓት ነበር። እስራዔላውያን በግብጽ ምድር በባርነት ቀንበር ስር ባሉበት ሰዓት። ንጉስ ፈርዖን የእስራዔላውያንን የጥበብ ስራዎች፣ የሚሰሯቸውን ጡቦች ቢወድም ነገር ግን በቁጥር እየበዙ ከመጡ መንግስቴን ይነጥቁኛል ብሎ ስለፈራ ህጻናትን ሁሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ የተላለፈበት የጨለማ ዘመን ነበር። በዚህ ወቅት የተወለደው ይህ ሰው ወላጅ እናቱ በዓባይ ወንዝ ላይ በእንዲት ቅርጫት ኣሳፈረችው። መደበቋ ነው። በርግጥም ከወታደሮች ሰይፍ መትረፍ ችሏል። ለሶስት ወራት በዚህ ሁኔታ ወላጅ እናቱ ደበቀችው። ታዲያ ከእለታት ኣንድ ቀን ልእልት እየችው። ልእልት ይህን ህጻን ስታየው ያማረ ነበርና ቤተመንግስት … [Read more...] about ዘ-ፀዓት! . . . . ውጣ!










