• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሽ – ሽ – ት …!

November 21, 2012 12:53 am by Editor 10 Comments

ሽ – ሽ – ት …!

እንደዋዛ ሲከንፍ ዕድሜዬ እኔን ጥሎ

ስም ያልዘራሁበትን ወኔዬን ጠቅልሎ

እንደ ቀልድ ፤ እንደ ህልም ፤ ሲከስም ወዘናዬ

ብ … ን … ! ሲል የኋሊት ጠጉሬ ከላዬ

እንደው እንደ ዘበት ልጆች ሲሉኝ ጋሼ

መናገር ያምረኛል ዕድሜዬን ቀንሼ፡፡

ይህንንም ግጥም ያገኘነው ከፌስቡክ ላይ ሲሆን ታዋቂው ገጣሚ አብዲ ሰኢድ ነው የገጠመው፡፡ ምስጋናችንን እንቸረዋለን፡፡

በሥራ መደራረብ እንደታሰበው በወቅቱ የግጥም ጨዋታችንን በማዘግየታችን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ ባለፈው “ህልመኛው” በሚል ርዕስ ላወጣነው ግጥም አጸፋ መልስ የሰጣችሁ የዘወትር ገጣሚዎቻችንን yeKanadaw kebede፣ inkopa፣ Tsinat፣ እና አሥራደው ከፈረንሳይ ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ስለ “ሽሽት” ምን ትላላችሁ? ሽሹ! ሽሹ! ወይስ …? እስቲ ጨዋታውን አምጡት?

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Literature Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. dawit says

    November 21, 2012 01:52 am at 1:52 am

    በጋ – ከክረምት፣
    ቀን – ተምሸት.
    ደባል መሆናቸው
    በወል መንጎዳቸው
    አብስሎ አሸብቶ
    አጉብጦ አስረጅቶ
    “ጋሼ” አባባ ካላስባሉ
    ታዲያ ምኑ ላይ ነው እድሜን መከጀሉ?
    በዘበትም ቢሆንልኝ
    እድሜ ባጠገበኝ፣
    ሁሉም ጋሼ ባለኝ፤

    Reply
  2. ሽማግሌው says

    November 21, 2012 09:25 am at 9:25 am

    ጸጉሬም ብን ይበል ብንን ያርገውና
    ይደባለቅ መልኩ ማን ይፈራውና
    አርባው ላይ ነበረ ትልቁ ሙግቴ
    እምቢ አላርጅም ገና ነኝ ማለቴ

    መቆየትም ደጉ:- ዕድሜም ሃብት ጸጋ
    “ጋሼ”ንም አልጠላ:- አንቱታም አልሰጋ

    Reply
    • Dubale says

      November 22, 2012 01:17 am at 1:17 am

      Can you help me out how I can type in Amharic font on your message board? I just couldn’t figure it out.

      Thanks

      Reply
      • Editor says

        November 22, 2012 02:12 am at 2:12 am

        Dubale
        If you are using Firefox browser you can follow the instructions here (http://www.youtube.com/watch?v=FtFplPQfXj0) and have Amharic as add-on on your Firefox browser and write it without any problem. Or you can download one of the Amharic softwares from here (http://www.selamta.net/downloads.htm) and using your word processor you can do copy/paste to our forum. Or you can just use this (http://freetyping.geezedit.com/) type the Amharic online and copy/paste it the comments field here. Or you can download (http://www.tavultesoft.com/keyman/downloads/keyboards/details.php?KeyboardID=300) Amharic keyboard and do the typing by switching from Latin to Phonetics …

        Hope we have been of some help here. We are pretty sure some of our esteemed readers would add more to it.

        Reply
  3. በለው ! says

    November 22, 2012 02:46 am at 2:46 am

    እንዴት ዕድሜህ አይሮጥ ከቶ አንተን ጥሎ
    ያልሰራኸው ወኔ አንተኑ ጠቅልሎ
    ብን ቢል ከኋላ ፀጉር ከላይህ
    ጨጓራህ መላጡን ማን ነው ያየልህ ?
    ወኔህ ተቀፍዶ እጅ እግርህን ይዞህ
    በቁምህ ተቀምጠህ – ተቀምጠህ ተኝተህ
    ባልጋ ቦታ ይዘህ – ሞተህ ቦታ አጣበህ !
    መች ነበር በዕድሜህ ማፈር በሥራህ
    ል-ሽ-ሽ ! ብትለውስ የት ትሔደዋለህ ? ?
    በለው!ከሀገረ ካናዳ

    Reply
  4. yeKanadaw kebede says

    November 23, 2012 10:46 pm at 10:46 pm

    ካንተ ጋር ለመኖር አልቻለው ብሎ
    ስምህን – ወዝህን – ወኔህን ጠቅልሎ
    መሄዱን ስሰማ ዕድሜህ አንተን ጥሎ
    የሰው-ቀፎ ስትሆን – ሕመምህ አሞኛል
    ራስህ ራሱም መቅረቱ ገርሞኛል
    ሸሸና ሸፈተም በመኖር ይፈታል
    ዕድሜ ግን ውሐ ነው ካልሄደ ይሸታል

    Reply
  5. ዱባለ says

    November 23, 2012 10:48 pm at 10:48 pm

    የጎልጉል አስተዳዳሪ
    ስላደረጋችሁልኝ እርዳታ በጣም አመሰግናለሁ!!!

    Reply
    • Editor says

      November 23, 2012 11:02 pm at 11:02 pm

      ዱባለ

      በአማርኛ ጽፈው ለማየት በመቻላችን እኛም እጅግ ደስተኞች ነን:: ታዲያ ለግጥሙ እንዴት ነው አንድ ሁለት ስንኝ ጀባ አይሉንም እንዴ?
      በተስፋ እንጠብቃለን::
      አክባሪዎ

      ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ

      Reply
  6. ዱባለ says

    November 24, 2012 04:51 am at 4:51 am

    ሽ-ሽ-ት ከአድሜ አይሁን ይሁን ከህሊና
    ሸምግሎ ለጋ መምሰል ተዘፍቆ በሙስና
    ወገንን በድሎ ከመኖር በዝና
    በቶሎ ተመልጦ ሸምግሎ ከብሮ በምስጋና
    ማለፉ ይሻላል ህዝብ መርቆት በቁና
    ከመረገም ይልቅ ባልተወለደና
    ሟምቶ በቀረ ጭንጋፍ በሆነና

    ምንም በመጀመሪያ አንድመጣልኝ ባይሆንም ለጊዜው ማደርያ ይሁንልኝ!!!!

    Reply
  7. Addis says

    December 13, 2012 02:33 pm at 2:33 pm

    ይቺ ግጥም ለ aboy sibehat nega
    “ሽበት”
    ሰው እድሜ ታድሎ ሲኖር ጊዜ አግኝቶ:
    ይሸብታል ፀጉር መቼም አያውቅ ዋሽቶ:
    በዘልዛላው እድሜ ያልተማረው ሽበት
    በዛገ አስተሳሰብ የሁዋሊት ሲጎተት:
    ‘በእኔ አውቅልሀለሁ’ ሲዳክር ካየነው:
    የሰው ሽበት ሳይሆን ሽበቱ የድንጋይነው::

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule