• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሀገሬ ዲሞክራሲያዊ የበቀል ፖለቲካ!

July 9, 2016 10:04 am by Editor Leave a Comment

* የሰሜኑ ኮከብ አብርሃ ደስታ እንኳንም ተፈታህ!

የሰሜኑ ኮከብ ወንድም አብርሃም ደስታ ከእስር እንደሚፈታ ቢገመትም ዘንድሮ ሲሆን እንጅ ሲባል ለማመን ተቸግሬያለሁና ዛሬን መቆየት ነበረብኝ ። እናማ የሰሜኑ ኮከብ ደፋሩና ለእውነት ግንባሩን የማያጥፈው የመቀሌው አብርሃም ደስታ ” እውነት ተፈታ ”  ሲባል ሰማሁ ፣ ደስ አለኝ !  አብርሽ
እንኳንም ከቤተሰብ ፣ ከዘመድ አዝማድና ወዳጅ አፍቃሪ ወገንህ ጋር ተቀላቀልክ እልሃለሁ ፣  አብርሽ!

ከሁሉ አስቀድሞ አብርሃም ሃብታሙ ከተኛበት ሲጎበኘው የሚያሳየውን ምስል ስመለከት በደስታ ኩራት ስሜቴን መቆጣጠር አቅቶኝ ማንባቴ አልቀረም … ሁለቱ ወንድሞች ገርድሰው የጣሉት ልዩነትና ህብረታቸው ሳውቀው ዛሬ እንደ ብርቅ ነገር አስደሰተኝ  ! በዚህ ዛቢያ ስማስን የዘር ፖለቲካው ክፋት አንደርድሮ ወደ ሌላ አቅጣጫ ወረወረኝ … ከምንም በላይ በበቀል ላይ የተመሰረተው ፖለቲካ አካሄድ አደገኛነት ታይቶኝ በደፈናውም ቢሆን መብተክተኬ ግድ ሆነ …

በእኛ ሐገር ዲሞክራሲያዊ የበቀል ፖለቲካ ሰለባዎችን አሰብኩና በደስታየ መካከል ከፍቶኝ ቆዘምኩ ስለ ፍትሃዊ ፣  ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እየተለፈፈና እየተደሰኮረ መሬት ላይ ያለው እውነታ ሌላ ነው ። ባሳለፍናቸው ሁለት አስርት ቅርብ አመታት በስደቱ የሆነውን እውነት ስለተናገርን ብቻ ”  አይናችሁን ላፈር ” ከተባሉት መካከል አንዱና ቀዳሚው ብሆንም ነገር ላለመቀላቀል ብቻ የእኛ ነገር ልተወው  ፣ መነሻየ ስለሆነው በሐገር ውስጥ እየሆነ ስላለው ፣ በዴሞክራሲያዊ በቀል ፖለቲካው ዳፋ ተጠቂ ስለሆኑት ትንታግ ወጣት ጎልማሳዎቹ ጥቃት ጥቂት ላውሳ  ..

የሰሜኑ ኮከብ የምንለው  አብርሃም ደስታና መሰክ ወንድሞች በሰላማዊ መንገድ ” ሐገር አለን! ” ብለው  ሀሳባቸውን በተለያየ መንገድ ሲገልጹ የገዥው አካል የጥቃት ኢላማ መሆናቸውን አስታወስኩት … እርግጥ ነው ብዙዎች በሐገር ወገናቸው ድጋፍ ከፍተኛ ትምህርት ተምረው ፣  ለሐገር ወገናቸው የድርሻቸውን ማድረግ እንዳይችሉ መስራት የሚችሉበት እድሜያቸው ወህኒ እየበላው ነው … ለሃገራቸው ቀናኢ ሆነው ድምጻቸውን ባሰሙ በቀጥታና በስውር ተንኮል፣ በበቀል ፖለቲካ  እየተጠለፉ ነው … ቤተሰብና ቀሪ ዘመናቸው በፖለቲካ አረንቋ ውስጥ ተዘፍቆ በበቀል ሲገለሉና ሲሰቃዩ  ለመገኘቱ እውነት ማሳያ ታይተው የጠፉ ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞችና ልሂቃን ሞልተውናል !…

ለዲሞክራሲያዊው የበቀል ፖለቲካ አካሄድ ጥሩ ማሳያ ብዙ ወንድም እህቶች ቢኖሩም ህክምና ለማግኘት በስቃይ ላይ ሆኖ ደጅ የሚጠናው ጎልማሳ ፖለቲከኛ ሐብታሙ አያሌው በቅርብ የምናገኘው አስረጅ ማሳያ  ይመስለኛል! ከራሱ ከገዥው ፖለቲካ ፖርቲ ተፈልቅቆ የወጣው ሐብታሙ እውነትን ተከትሎ የተጓዘበት መንገድ ለወህኒ ዳርጎት ፣ በዚያው በወህኒ የተፈጸመበት በደል ህመም በሽታውን አባብሶበት፣ ከወንጀለኛነት ነጻ ተብሎ ሲለቀቅም የአቃቤ ህግ ይግባኝ ክስ የሀብታሙን የመንቀሳቀስ ህገ መንግስታዊ መብት አሳግዶታል! ሃብታሙ  በጸና ህመሞ አልጋ ላይ ሆኖ ነፍሱን እንዲታደጉ ደጋግሞ አቤቱታ ያቀረበላቸው የፍትህ አካላት የሃብታሙን የነፍስ አድን ጥያቄ ማስረጃ ተቀብለው ሳለ ውሳኔ ለመስጠት በቀጠሮው አልገኝ ብለው  ቸግሮናል! ይህ መሰሉ ግፍና በደል ስሙ ማን ይባላል  ? እስኪ ንገሩን?

በዜጋው ላይ የዘር መድልኦ ነግሶ ፣ ግፍ ልኩን አጥቶ ፣ ፍትህ ሲዛባ ፣ የወጣው ሐገር መመለስ ሞት መስሎት ፣ ሐገር ያለው ነፍሱ በሬ ሃገሩን ጥሎ መውጣት ሲሆን ሕልሙ ማየት የሚያመውን ያህል ህመም አለ አልልም!  ዲሞክራሲያዊው የበቀል ፖለቲካ አካሄድ ሃገሬውን ሐገር አልባ ስሜት አውርሶ ተስፋ ቢስ እያደረገው ነው ! በተለይ እንደ ምክያታዊው ወጣት ፖለቲከኛ እንደ  አብርሃ ደስታ ያሉት ወንድሞች ጥፋተኛ ተብለው  ያሳሰራቸው ጉዳይ አላሳምን ብሎን ፣ መታሰርን ስንቃወም ብንከርምም ፣  ሲፈቱ የምንደሰተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ስለተቀላቀሉ እንጅ የታሰሩበት ምክንያት አሳማኝ መረጃ ቀርቦና አሳምኖን አይደለም!

በእኛ ሐገር ፖለቲካ ቁማር ነው … ዘባተሎው ፖለቲካ ስልጡን መሪ አጥቷል  !  … ከሐገር እና ለወገን ጥቅም “ያገባናል ”  ያሉ ይጮሃሉ ፣ መንግስት ሰበብ አስባብ ፈልጎ ቀና ያሉትን አንገት ለመስበር ያሳድዳል ፣ ያስራል … ” ያገባናል ” ያሉት ጩኸት ላንዳፍታ ይነሳና ተራግቦ ይረሳል … ያነሱት የህዝብና የሐገር ጉዳይ ይረሳና ጀግኖቻችን “ፍቱልን”  ፣ ” አሳክሙልን! ” ብለን እንድንጮህ ያደርጉናል ፣ ሲፈልጉና ሲፈቅዱ አንገላተው ይፈቷቸዋል  ፣ የታመሙትንም ቢሆን ህመሙ በልቶ ሊጨርሳቸው ሲል ፈጣሪን ከፈሩ ህክምና ይሰጧቸዋል ፣ ፈጣሪን ካልፈሩ በበቀል አሽተው ይወረውሯቸውና እያለቀስን እንኖራለን

የሰሜኑ ኮከብ አብርሃም ደስታ ከዚህ መሰሉ የእኛ ፖለቲካ አዙሪት ገብተህ ከወህኒ በመውጣትህ ደስ ብሎኛል ፣ ደስ ብሎናል  ! እነሱም የሚፈልጉት የታሰርክበት ጉዳይ አስረስቶ ” እንኳንም ተፈታህ ”  እንድንል ቢሆንም ርቀህባቸው ስለተጎዱ ቤተሰቦች ፣ ስለዘመድ አዝማድና ወገን አፍቃሪዎችህ ሲባል እንኳንም ተፈታህ!

ወዳጅ የሐገር ልጅ አብርሽ አሽቃባጭ ሆነህ ከተደላደለው ወንበር እንዳሻህ መሆን ሲቻልህ ፣ ስለ እውነት ለወገኖችህ የከፈልከውን መስዋዕትነት ግን ማንም አይረሳውም!

እንወድሃለን!

ነቢዩ ሲራክ
ሐምሌ 2 ቀን 2008 ዓም

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule