• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጠ/ሚ/ር አብይ ከኪነ ጥበቡ ማህበረሰብ ጋር

June 27, 2018 08:49 pm by Editor 3 Comments

ዛሬ ሰኔ 20፣ 2010 ዓ.ም ጠቅላዩ ከአርቱ ማህበረሰብ ጋር በጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት አዳራሽ ከጠዋቱ 03፡00-05፡30 ድረስ በኪነ ጥበብ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። ምንም እንኳ ከባህልና ቱሪዝም ሚ/ር የታደለው የመጥሪያ ደብዳቤ “ሥልጠና” ቢልም፣ ነገሩ ስልጠና ሳይሆን ውይይት ነበር፤ የውይይት ጊዜ ቢያንስም። ዶ/ር አብይ የ”ሰተቴ” እና “እርካብና መንበር” መፃህፍቶች ደራሲ መሆናቸውንም ነግረውናል። የተወሰኑ ኮፒዎችንም በነፃ አድለዋል።

እውነቱን ለመናገር ዶ/ር አብይ የአርት ፅንሰ ሐሳብ ላይ ባላቸው ጥልቅ ግንዛቤ ተገርሜያለሁ። አርት በአሜሪካ የጥቁሮች የእኩልነት ትግል ውስጥ ያለውን ሚና ያሳዩበትና በማርከስ ጋርቬይ፣ በማልኮም ኤክስ፣ በማርቲን ሉተር ኪንግ፣ በፕ/ት ኬኔዲ እና በቦብ ማርሌ መካከል የነበረውን የመንፈስ ትስስር ያቀረቡበት መንገድ በጣም መሳጭ ነው፣ አንባቢነታቸውንም ያሳያል።

ውይይቱ በኪነ ጥበብ ዘርፎች (ሙዚቃ፣ ስዕል፣ ሥነ ፅሁፍ፣ ፊልም፣ ቲያትር ወዘተ) ውስጥ ያሉ 500 ባለሙያዎችን ያሳተፈ ሲሆን፣ እኔም በፀሐፊነቴ ከተጋበዙት ውስጥ ነበርኩ። ውይይቱን ጠቅላዩ ብቻቸውን የመሩት ሲሆን፣ የኪነ ጥበብ ፅንሰ ሐሳብና ፋይዳ ላይ የተፃፉ ከመቶ በላይ ስላይዶችን አዘጋጅተው ነበር የጠበቁን። ይሄም የሚያሳየው የሰውየውን ትጋት ብቻ ሳይሆን ለአርትም ያላቸውን ዝንባሌ ጭምር ነው። የሀገሪቱን አርት ለማጎልበት ሲባልም ለ50 ባለሙያዎች የአንድ ሳምንት የቻይና ጉዞና ጉብኝት (የልምድ ልውውጥ) እንደሚኖርም ተናግረዋል። አጠቃላይ ሐሳባቸውም የሚከተሉት ሲሆኑ ቅንፉ የኔ ጭማሬ ነው።

ኪነ ጥበብና ማህበረሰብ

ይህ ትውልድ በባለፈው ጥበብ የተሰራ ነው። የዕድገትና የስልጣኔ መለኪያው ህንፃ ሳይሆን አርት ነው። (ዶ/ር አብይ እዚህ ጋ የምዕራባውያንንና የመካከለኛው ምስራቅ ኪነ ህንፃዎችን በማሳየት የስልጣኔያቸውን ከፍታ አሳይተዋል) አርት ረቂቅ ሰብዓዊ ስሜቶችን የምንገልፅበት መሳሪያ ስለሆነ ጥበብ ያለበት ቦታ በተፈጥሮ ምድረ በዳ ቢሆን እንኳ ገነት ያደርገዋል። ጥበብ የሌለበት ቦታ ግን ገሀነም ነው። ለአካል ብርታትን፣ ለመንፈስም እድሳትን የሚሰጠው ጥበብ ነው።

ጥበብ ሚናዋን ስትጫወት ብቻ ነው ማህበራዊ ሽግግር የሚመጣው። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በዘረኝነት፣ በሃይማኖት … ቅርጫ ሆናለች። አርት እንዴት ከዚህ ጨለማ መውጣት እንደምንችል የሚያሳየን እንጂ ችግሩን እንደ ordinary ሰው የሚዘግብ አይደለም። አርቲስት በጨለማ ውስጥ ያለውን ጭላንጭል የብርሃን ተስፋ የሚያይና ለህ/ሰቡም የሚያሳይ እንጂ የድሮ መሪዎች እንዲህ አደረጉ እያለ ትውልዱን ባለፈ ነገር ውስጥ እንዲዘፈቅ የሚያደርግ አይደለም። አርቲስት ከእንደዚህ ዓይነት ችግር ትውልድን የሚያሻግር ነው። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በተሰባበረ ድልድይ ላይ ናት፤ ድልድዩን የሚሰራው አርቲስቱ ነው። አርት ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ የሚሆንና የማህበረሰቡን ህመሞች የሚያስተጋባ ነው።

ኪነ ጥበብና የኢትዮጵያ መንግስታት

የሀገራችን የቀድሞ መሪዎች ለምሳሌ አፄ ምኒሊክ፣ ጅማ አባ ጅፋር፣ አፄ ኃ/ስላሴ፣ አቶ መለስ የአርት ዝንባሌ ነበራቸው። ቤተ መንግስታቸውን የሚያሳምሩበት መንገድና ኪነ ህንፃው ይሄንን ይመሰክራል። ሆኖም ግን፣ መሪዎቹ አርትን የሚፈልጉት ሀገራዊ ችግር ሲገጥማቸው ብቻ ነው – በተድላ ዘመናቸው ግን አርትን ይረሳሉ። አርት የአንድ ማህበረሰብ ድምር የታሪክ ክምችት ማስቀመጫና social capital ስለሆነ ምንጊዜም ቢሆን መረሳት የለበትም። መሪዎች ራሳቸው የአርት ውጤት ቢሆኑም፣ ከኩራታቸው የተነሳ አሊያም ካለማወቅ ይሄንን ሀቅ አይናገሩም።

ኪነ ጥበብና ፈጠራ

ማንኛውም ዓይነት የቴክኖሎጂ ፈጠራ የጥበብ ውጤት ነው፤ (የፈጠራ ምናብ የሚሰፋው በጥበብ ነው)፤ መጀመሪያ በምናብ ያልተሰራን ነገር፣ በተግባር ማሳየት አይቻልም።

የኪነ ጥበብ ሚና

በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት ዓይነት አመለካከቶች አሉ። 1ኛ ጥበብ ለልማት፣ 2ኛ ጥበብ ለጥበብነቱ የሚል። (እንደሚታወቀው የአቶ መለስ የጥበብ አረዳድ የመጀመሪያው ሲሆን ዶ/ር አብይ በዚህ ጉዳይ ላይ አቋም አልወሰዱም፤ ይልቅስ ሁለት ግንዛቤዎች እንዳሉ ብቻ ነው ያስረዱት፤ ሁለቱ ሚናዎች ግን እርስበርስ የሚጣሉ እንዳልሆኑ ለማሳየት ሞክረዋል)።

የኢትዮጵያ አርቲስቶች በዶ/ር አብይ እይታ

በአሁኑ ጊዜ የአርቲስቶቻችን ችግር ጊዜ ሰጥተው ዕውቀታቸውን ለማሳደግ አለመጣራቸው ነው። በዚህም ሥራዎቻችሁ የቀጨጩና የአንድ ሳምንት ወሬ ብቻ ሆነው ይቀራሉ። እናንተ ከልባችሁ ስለማትሰሩ ትውልዱ እናንተን ትቶ ወደ በፊቶቹ ስራዎች እየተመለሰባችሁ ነው። በአንፃሩ የበፊቶቹ አርቲስቶች ለምሳሌ ፀጋዬ ገ/መድን፣ አሊ ቢራ፣ ጥላሁን፣ ሎሬት አፈወርቅ፣ ገ/ክርስቶስ፣ ሐዲስ፣ በዓሉ … ስራዎቻቸው ዘመን ተሻጋሪ ናቸው።

አርት ትውልድን መፍጠሪያ መሳሪያ ስለሆነ አርቲስቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ት/ቤቶች እየተዘዋወራችሁ ለተማሪዎች ታሪካችሁን ብትነግሯቸው በአእምሯቸው ውስጥ ትልቅ ራዕይን ታስቀምጣላችሁ።

ለምሳሌ እኔ ልጅ እያለሁ አረጋኸኝ ወራሽ በት/ቤታችን መጥቶ ግንባሬን ስሞኛል። አሁን አረጋኸኝ (ውይይቱ ላይ ነበር) ያንን አያስታውስም፣ ለኔ ግን ያ ነገር ትልቅ ትርጉም ነበረው።

(ዶ/ር አብይ ለፀጋዬ ገ/መድን ትልቅ አድናቆት እንዳላቸው ተናግረዋል)። ፀጋዬን ያልተጠቀምንበት፣ ያልተረዳነውና ያለ ዘመኑ የኖረ ሰው ነው። ፀጋዬን ከእኛ ይልቅ ውጭዎች ያደንቁታል። ፀጋዬ ኢትዮጵያን የሰፋበት መንገድ በጣም አስገራሚ ነው፤ እኛ ግን እሱ የሰፋውን እየፈታን እንገኛለን። ኢትዮጵያውያን ሰውን የምናጀግንበት መንገድ የአንበሳና የጦጣ – የገዳይና የብልጣብልጥ ቀማኛ – ዓይነት ነው። ይሄ የተሳሳተ እሳቤ ነው። ፀጋዬ ይሄንን ስህተት በማረም ነው አፄ ቴዎድሮስን በተለየ መንገድ – በንግድ ሂሳብ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ስሌት – ያጀገናቸው – ብዙ ቴዎድሮሶችን ለመፍጠር።

ስለ ሰኔ 16ቱ (2010) የግድያ ሙከራ

ኢትዮጵያ አሁን የለውጥ ፕሮጀክት ላይ ነች። ይሄንን ሪፎርም ደግሞ ብዙ ህዝብ ደግፎታል። ከአሁን በኋላ ኢትዮጵያን ከፍቅር፣ ከእኩልነት፣ ከፍትህ፣ ከዲሞክራሲ ውጭ ማስቀጠል አይቻልም። ሁሉም ብሄር ይሄንን ነው የሚፈልገው። የትግራይም ህዝብ ከዚህ ውጭ ፍላጎት የለውም፤ በተለየ ሁኔታ ተጠቅሟል እየተባለ የሚወራው ነገር ስህተት ነው፤ ሪፎርማችን እነዚህን እሴቶች ያካተተ ነው። አሁን ከዚህ ወደኋላ መመለስ አይቻልም፤ ጥይት የሚገለው ሪፎርመሩን እንጂ ሪፎርሙን አይደለም። (“እኔም ብሞት ሪፎርሙ ይቀጥላል” ማለታቸው ነው) ራዕያችን ከኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት አልፈን የምስራቅ አፍሪካ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መፍጠር ነው። አርቱም ሆነ ሚዲያው ይሄንን ርዕያችንን ቢያግዘን፡፡ (በቅርቡ ለ2011 አዲስ ዓመት በዓል ላይ የኢትዮጵያና የኤርትራ አርቲስቶች ዝግጅቶቻቸውን በሌላኛው ሀገር ላይ እንደሚያቀርቡ መዘገቡ ይታወሳል) ሚዲያ ያለ አርት የሚጮህ ቆርቆሮ ነው። መጪው ትውልድ አሁን ያለውን መከራና ችግር እንዳይወርስ በአርት በኩል በደንብ እንስራ።

(ከዚህ በኋላ ተወያዮቹ 40 ሔክታር ላይ ያረፈውን ግቢ እየተዘዋወርን ጎብኝተናል – ከአፄ ምኒሊክ ጀምሮ የነበሩ መንግስታት የኖሩባቸውን መኖሪያ ቤቶች፣ አፄ ኃ/ስላሴ በደርግ ታፍነው የተገደሉበትን ቤት፣ 5000 ሰው የሚይዘው የአፄ ምኒሊክ የእልፍኝ አዳራሽ ኮርኒሱ የተሰራው ከጠፍር ሲሆን፣ ጠፍሩ ቢቀጣጠል 8000 ኪሜ እንደሚሆን ጠቅላዩ በአድናቆት ነግረውናል። ከጉብኝቱ በኋላ የምሳ ግብዣ ተደርጎ ፕሮግራሙ ወደ 09:00 አካባቢ ተጠናቋል።)

(ብሩህ አለምነህ)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Literature, Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. አለም says

    June 28, 2018 05:36 pm at 5:36 pm

    ውድ ጎልጉል፣
    የኢትዮጵያ አርቲስቶች ትናንት መለስ ዜናዊን ሰማይ ድረስ ሲያወድሱ፣ የወርቅ ብዕር ሲሸልሙት የነበሩት ናቸው ወይስ ሌሎች?

    Reply
    • Editor says

      June 29, 2018 10:44 pm at 10:44 pm

      አለም፤

      ከሁሉም ዓይነት የተቀላቀለ ነው። ሁሉም ተደማሪ ለመሆን ይፈልግ የለ?!

      አርታኢ

      Reply
  2. Samson says

    July 4, 2018 09:26 am at 9:26 am

    Where is taddy afro?hachalu hundesa? Artist ayidelum kenezi wechi yalut they are just michraphones…..

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule