• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጨነቀው “መንግስት”

November 16, 2017 07:44 pm by Editor Leave a Comment

እኔማ የዚህ መንግስት ባህርይ ከቶውንም ሊገባኝ አልቻለም፡፡ እንደ እኔ እንደኔ “መንግስት” ጃጅቷል ባይ ነኝ፡፡ በመጃጃት የሚታይ ስዕብና በዚህ መንግስት እያየሁ ነው፡፡ የአማራ ክልል መንግስት ጳጉሜ 3 ቀን 2009 ዓ.ም ምን እንደታየው በውል ባላውቅም ከመሬት ተነስቶ የመንግስት ተሸከርካሪ አያያዝ፣ አጠቃቀምና የንብረት አስተዳደር መመሪያ አሻሽያለሁ ብሎ በሌጣ ደብዳቤ ለመንግስት ተቋማት ሰርኩላር አስተላልፎ ነበር፡፡  በክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ተላላኪነት ለክልሉ ቢሮዎች የተላከው ደብዳቤ ከመስከረም 1 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ወይም የሥራ ኃላፊዎች ለሥራ ጉዳይ ክልሉን ለቀው ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ የሚመሩትን ተቋም ተሸከርካሪ ይዘው እንዳሄዱ የሚያሳስብና በተማከለ መንገድ በከተማው በሚዘጋጁ ተሸከርካሪዎች መጠቀም እንደሚችሉ የሚያሳውቅ ነበር፡፡

በተማከለ መንገድ በሚዘጋጁ ተሸከርካሪዎች መጠቀም የሚችሉ ብሎ ደብዳቤው ያሳወቃቸው የሥራ ኃላፊዎች የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ም/ርዕሰ መስተዳድርና በዚህ ደረጃ ያሉ ኃላፊዎች፣ የክልሉ ም/ቤት አፈ ጉባዔና ምክትል አፈ ጉባዔ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የካቢኔ አባላት የሆኑት የቢሮ ኃላፊዎች፣ ዋና ኦዲተር፣ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ ያሉ ኃላፊዎች የዞን ዋና አስተዳዳሪዎችና የሜትሮፖሊታን ከተማ ከንቲባዎች ናቸው፡፡

የተጠቀሱት ኃላፊዎች አዲስ አበባ ለሚደረጉ ማንኛውም ስብሰባዎች ወይም ሌሎች ሥራዎች ወደ አዲስ አበባ በአይሮፕላን የሚሄዱ ከሆነ ከአይሮፕላን ማረፊያ የሚቀበላቸውና በቆይታቸው ወቅት በማዕከል አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጁ ተሸከርካሪዎችን  ወይም በቀን 1200 ብር ያልበለጠ የመኪና ኪራይ በሕጋዊ ደረሰኝ መጠቀም እንደሚችሉ ያተተው ቀላጤው ለከተማ አገልግሎት ተጨማሪ ተሸከርካሪ ማንቀሳቀስ እንደሌለባቸው አስረድቷል፡፡

የተሽከርካሪ ስምሪትና የማስተዳደሩን ተግባር ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሥልጣን የሰጠው ይኸው መመሪያ በክልሉ የካብኔ አባላት የሆኑ ቢሮዎች ምክትል ቢሮ ኃላፊዎችና በምክትል ቢሮ ደረጃ የተሾሙ ሹማምንቶች ወደ አዲስ አበባ በአይሮፕላን የሚሄዱ ከሆነ በማዕከል በተዘጋጁ ተሸከርካሪዎች መጠቀም የማይችሉ ከሆነ በቀን ከብር 600 ያልበለጠ የመኪና ኪራይ በመጠቀም በህጋዊ ደረሰኝ ማወራረድ እንደሚችሉ ያትታል፡፡

በመመሪያው የተቀመጡትን ድንጋጌዎች ተላልፎ የተገኘ የሥራ ኃላፊ ከተፈቀደለት የገንዘብ መጠን በላይ ያለውን ወጪ በግሉ እንደሚሸፍንና በመመሪያው ከተፈቀደው ውጪ ሂሳብ ያወራረደ የመ/ቤቱ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደርም ተጠያቂ እንደሚሆን ያሳውቃል፡፡

ይህ ደብዳቤ በየተቋሙ ከደረሰ በኋላ መመሪያው የሚመለከታቸው የከፍተኛ አመራር ሹፌሮች ቅስማቸው በመሰበሩና መንግስት ጉሮሮአቸው ላይ በመቆሙ አለቆቻቸውን ከኤር ፖርት ለመቀበልና ለመሸኘት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ ከአንድ ተሳፋሪ ከባህር ዳር አዲስ አበባ 450 ብር የሚያገኙት የትራንስፖርት ገቢ ሲያጡ ቅሬታ አይሉት ሐዘን ኡኡታቸውን ባገኙት አጋጣሚ ማሰማት ጀመሩ፡፡

በቅሬታ መልክ የሚያስተጋቡት የተሻሻለው መመሪያ የአሽከርካሪዎች የሥራ ሁኔታ ያላገነዘበና ለይስሙላ የወጣ መመሪያ እንደሆነና ከመንግስት የሥራ ሰዓት ውጭ ከኃላፊዎች ጋር እስከ ምሽት እያመሸን፣ ቤተሰቦቻቸውን እያመላለስንና የቤት ወጪያቸውን እየገዛና ለምናደርስበት የትርፍ ሰዓት አገልግሎት አበል ሊታሰብልን ይገባል ብለዋል፡፡

የወጣው መመሪያ እርስ በርሱ እንደሚቃረን በክልሉ በየተቋማቱ ያሉ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች ቢናገሩም የክልሉ መንግስት ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል ህሳቤ መመሪያው ለመተግበር ሲነሳ በመመሪያው የተጠቀሱ ክልሉ ካብኔዎች በአገሪቱ መዲና አዲስ አበባ ከተማ በማዕከል ደረጃ በሚዘጋጀው የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ የተወከሉት የወያኔው ኤፈርት ድርጅት በሚያቀርባቸው ተሸከርካሪ መሆኑን የክልሉ መንግስት ሲያውቅ መመሪያውን ማሻሻል ገባ፡፡

ሰሞኑን በየተቋማቱ የተሠራጨው የማሻሻያ ደብዳቤ የክልሉን መንግስት መጨነቅ የሚያበስር ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ከክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በቁጥር አብክመ/ ገኢት/ክበ-01/450 በቀን 20/02/2010 ዓ.ም የተሠራጨው ደብዳቤ … በማዕከል ይዘጋጃሉ የተባሉት ተሸከርካሪዎች በግዥና በሌሎች ምክንያቶች ስለዘገዩ አመቻችተን በሌላ ደብዳቤ እስከምናሳውቃችሁ ድረስ ከዚህ በፊት በነበረው የተሽከርካሪ አጠቃቀም መመሪያ መሠረት እንዲፈጸም እናሳውቃለን ይላል፡፡

እኔን የገረመኝ ተሻሻለ የተባለው መመሪያ ሦስት ወራት ሳይሞላው ውድቅ መደረጉ ሳይሆን በማዕከል ይዘጋጃል የተባለው የትራንስፖርት አገልግሎት በወጉ ሳይቀርብ መመሪያ ለማሻሻል የገባው የአማራ ክልል ካብኔ ተግባር ነው፡፡

የክልሉ ካብኔ ውሳኔ አንድ አባባል አስታወሰኝ፡፡ አንዱ ባልንጀራውን የመጥረቢያ እጀታ በምን ተቆረጠ ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ተጠያቂው ባልንጀራም  በመጥረቢያ ስል መለሰ፡፡ ጠያቂውም መልሶ መጥረቢያ ከመፈጠሩ በፊት ኧረ ቀደም ቀደም ብሎ ቢጠይቀው ምላሽ አጣለት ይባላል፡፡ የክልሉ መንግስትስ ከነገረ ቀደም የመንግስት ተሸከርካሪ አያያዝ፣ አጠቃቀምና የንብረት አስተዳደር መመሪያ ማሻሻል ያስፈለገው ለምን ይሆን? የኔ ጥያቄ ነው፡፡ ምላሹ መንግስት ቢጨንቀው ነው፡፡ (ከኢንተርኔት የተገኘው ፎቶ የብአዴን ቢሮ ነው)

ጲላጦስ ከጣና ዳር (ummp4.20@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule