• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ወገናዊ ጥሪ ወገን ለሆነው የትግራይ ህዝብ

August 28, 2016 12:54 am by Editor 2 Comments

ይህን ፅሁፍ ነፃ አስተሳሰብን ከሚያውኩ ግላዊ ባህርያት ነፃ በመሆን ማንበብ ያስፈልጋል። የጎሳ፣ የብሄር ወይም የቋንቋ መለያ አጥር ውስጥ ከቆምን የፅሁፉ አላማም ሆነ ይዘት በውል ላይታየን ይችላል። ቢታየን እንኳን ምናልባት ግምገማችን ሊዛባ ይችላል። ምክንያቱም መልእክቱን ወይም አላማውን የምንገመግመው ከቋንቋችን፣ ከብሄር ማንነታችን ወይም ከትውልድ ቀያችን አንፃር ስለሚሆን ሚዛናችን ወይም ግንዛቤያችን ስህተት ይሆናልና ነው።  ሰው መቼም ሲያስብ፣ ሲወስንና እርምጃ ሲወስድ አስተሳሰቡን፣ አወሳሰኑንና እርምጃ አወሳሰዱን በስሜት ሀይል ከሆነ መነሻው፣ መንገዱም ሆነ ግቡ ስህተት መሆኑ አይቀርም። ውጤቱም ጥፋት እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ የገባችበት ቀውስ መነሻው ያስተሳሰብ፣ ያወሳሰንና የድግጊት መነሻችን ነፃ አእምሮ ሳይሆን ስሜት ብቻ ስለነበረ ይመስለኛል። ሰው በእውነቱ ሳይሆን በስሜቱ ከተመራ መደረሻው ውድቀት መሆኑ አይቀርም። እኔ የምደግፈው እገሌ የሰጠውን ሃሳብ ወይም የያዘውን አቋም ነው፦ ምክንያቱም ብሄሩ የኔ ስለሆነ፤ እንቶኔ የተባለው ፓርቲ ደጋፊ ነኝ፤ ምክንያቱም አባላቱ የኔ ብሄር አባላት ስለሆኑ  በሚል መስመር ብንሄድ የት እንደምንደርስ ለማወቅ ነጋሪ አያስፈልገንም። በጥቅሉ ያመለካከታችንና  የፍርዳችን ትክክለኝነት መስፈሪያው ነፃ መረጃ ወይም ነፃ አእምሮ መሆኑ ቀርቶ ያልተመረመረ ጭፍን ወገንተኝነት ከሆነ ውጤቱ የዘለአለም ጥፋት ነው። ጥፋቱም ከግልና ቡድን አልፎ ላገርና ህዝብ ይተርፋል። የዛሬይቱ ኢትዮጵያ አበሳና ፍዳ ምንቹ  ይህ ሳይሆን አይቀርም። ብዙዎቻችን እምነትና አቋም የምንይዘው፣ ውሳኔና ፍርድ የምንሰጠው በማስረጃ ሳይሆን በፍረጃ መሆኑ ስለሚታይ የፅሁፌ መልእክት የዚህ ክፉ አባዜ ሰለባ እንዳትሆን ሰግቼ በዋና ከማልወጣው የሃሳብ ባህር ውስጥ ገባሁ እንጂ አነሳሴ እንኳን ስለሰው ግንዛቤ ወይም ያስተሳሰብ ህግ ለመደስኮር አልነበረም። እናም ወደነጥቤ ልመለስ። ግን ለምወደው የትግራይ ህዝብ የምሰጠው ማሳሰቢያ አንባቢ ከቋንቋና የብሄር ማንነት ነፃ በሆነ አመለካከት እንዲመዝነው አደራ ማለቴን አልተውም።

ዛሬ በትግራይ ህዝብና በሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል የወደፊቱን ዘለአለማዊ ህይወት የሚወስን ታሪካዊ አጋጣሚ ተፈጥሯል። አጋጣሚው እንደሁኔታው ክፉም በጎም ሊሆን ይችላል፣ ይህን የሚወስነው የትግራይ ህዝብ ነው። የትግራይ ህዝብ ዛሬ ወሳኝ በሆነ የታሪክ ነጥብ ላይ ቆሟል። በዚህ ወሳን ነጥብ ላይ ቆሞ የሚሰጠውም ፍርድም ሆነ የሚወስደው ምርጫ ወንድሙ ከሆነው የቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚኖረውን የወደፊት ግንኙነት እስከወዳኛው ይወስናል። ምርጫውም በቋንቋና በዘር በሚመስሉት ጥቂት ግለሰቦችና በሌላው ኢትዮጵያዊ መካከል ነው። ምርጫው ቀላል ላይሆን ይችላል ግን ወሳን ነው።

በአንድ በኩል በብኼር ማንነትና በቋንቋ ሚዛን በጭካኔው ወደር የሌለውንና አንድ ሃሙስ የቀረውን የጥቂት አንባገነን ግለሰቦችን ቡድን መወገን ወይም ፍትህ ከተጓደለበት የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ቆሞ ለሃቀኛና አስተማማኝ ዲሞክራሲ አብሮ በመታገል ወንድም ከሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በማይበጠስ የታሪክ ገመድ ተሳስሮ ለዘለአለም መኖር ነው።  በዚህ ወሳን ወቅት ከቋንቋና ብሄር መጀሳሰል በቀር ባመለካከት ከማይወክሉት ጥቂት ገዢዎች ጋር መወገንና  ከብዙሀኑ ህዝብ ጋር መቆራረጥ እጅግ አስፈሪና አደገኛ ምርጫ ነው።

በእኔ አስተያየት አሳምሬ የማውቀውና ደጉ የትግራይ ህዝብ ብዙሃን ወንድሞቹን በጥቂት አንባገነኖች ይለውጣል ብዬ አልገምትም። የትግራይ ህዝብ እስከማውቀው ድረስ ሰላማዊና በኢትዮጵያዊነቱ ጥርጥር የሌለው ቅን ህዝብ ነው። እንደአለመታደል ሆኖ ክልሉ ለረጅም ጊዜ በጦርነት ቁም ስቅሉን ሲያይ የኖረ ህዝብ ቢሆንም በሌሎች ለደረሰበት መከራ ሁሉ የኢትዮጵያን ህዝ ተጠያቂ አድርጎ አያውቅም። በየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ከህዝብ ጋር ተስማምቶ ከመኖር በቀር ከማንኛውም ጎሳወይም ብሄር ጋር የተለየ ግጭት ውስጥ ገብቶ የሚያውቅ አይመስለኝም። የሚታወቀውም በሰላማዊነቱና ተግባቢነቱ ነው።

ይሁን እንጂ እንደማንኛውም ህዝብ ሲደርስበት የነበረውን ጭቆና ሰበብ በማድረግ በትከሻው ላይ ተንጠላጥለው ስልጣን ላይ የወጡ እፍኝ የማይሞሉ ብልጣብልጦች በስሙ በመነገድ ሌሎች ወንድሞቹ ከገዢዎች ጋር በአንድ አይን እንዲመለከቱት ያላደረጉት ጥረት የለም። በስሙ ገዝተዋል፣ ጨቁነዋል፣ ገድለዋልም። ለትግራይ ህዝብ ፍትህና ነፃነት የሞቱትን ሺዎች አፈር አልብሰውና ቃልኪዳናቸውን አጥፈው ለትግራይ ህዝብ ሳይሆን እፍኝ ለማይሞሉ ታማኝ ትግሬዎች፣ አማሮች፣ ዖሮሞዎች፣ ጉራጌዎችና ሌሎች አገልጋዮቻቸው ቀለብ ሰፋሪ ሆነዋል። የትግራይ ህዝብ ከህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ገዢ  ቡድን ያገኘው ጥቅም ስም ብቻ ነው። የግፍ አገዛዛቸው ሰለባ ከመሆንም አላመለጠም። ይባስ ብሎ ቋንቋውን በመናገርና በስሙ በመጨቆን በገዛ ወገኖቹ በክፉ አይን እንዲታይ አድርገውታል።

ይልቁንም ከመቼውም በባሰ ዛሬ በሚገኝበት አጣብቂኝ ውስጥ ከተውታል። በአንድ በኩል ከጥቂት ብልጣብልጦች በቀር እንደህዝብ ባላተረፈበት ስርአት እንደጨቋኝ ህዝብ ስለታየ ስርአቱ ቢፈርስ እጠቃ ይሆናል በሚል ስጋት ግፈኞቹን እስከነጉድፋቸው ለመደገፍ ሲያመነታ በሌላ በኩል ደግሞ በጠራራ ፀሃይ የፈጸሙት ግፍና መከራ ለፍትህና ዲሞክራሲ ቀናኢ  የሆነውን ህዝብ ሆድ ማሻከሩ አይቀርም። ለፍትህና ዲሞክራሲ፣ ለነፃነትና እኩልነት ልጆቹን የገበረው የትግራይ ህዝብ እኩልነትና ነፃነት የጠየቁ ሰላማዊና ለጋ ወጣቶች ደም  በየአደባባዩ ሲፈስ አበጀ የሚል አይመስለኝም።

የሆነው ሆኖ ዛሬ የትግራይ ህዝብ ከፊቱ ወሳን ምርጫ ቀርቦለታል። ምርጫው ከገዢው መደብ ጋር በማበር ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እስከወዳኛው መቆራረጥ ወይም ለፍትህና ዲሞክራሲ ደሙን እየገበረ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመወገን በታሪክ ሞገስና በህዝብ ዘንድ ዘለአለማዊ ፍቅርና ክብር መጎናፀፍ ነው። የትግራይ ህዝብ ምርጫ ፍትህ፣ ዲሞክራሲ፣ እኩልነትና ህዝባዊነት እንደሚሆን የምጠራጠርበት ምክንያት የለኝም። ለምን ቢባል በስልጣን ላይ ያለው ቡድን ከቋንቋውና ብሄርብሄሩ በቀር በምግባሩ የትግራይን ህዝብ ስለማይመስል ነው። ለምን ቢባል የትግራይ ህዝብ ወንድሙ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የፍትህ ጥያቄ በንፁህ ህሊና እንጂ በቋንቋና በብሄር ዳኝነት ይዳኘዋል የሚል እምነት ስለሌለኝ ነው። ለምን ቢባል የትግራይ ህዝብ እንደህዝብ የማይታረም የታሪክ ስህተት ለመስራት ይወስናል ብዬ ስለማላምን ነው። ለምን ቢባል የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ እንደቡድን የከዳውን የኢትዮጵያ ህዝብ የትግራይ ህዝብ እንደህዝብ ዳግም ይከዳዋል ብዬ ስለማላምን ነው። ስንት የታሪክ ፈተና በጽናት ያለፈው የትግራይ ህዝብ ይህን ልላ የታሪክ ፈተና  ይወድቃል ብዬ አልገምትም።

መልካሙን ለማየት ያብቃን።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Tadesse says

    September 6, 2016 10:43 am at 10:43 am

    A very nice idea,if if took the wrong way,it will surely be a disaster for the people of Tigray,a man with out history is like a tree with out roots.This is not our history,our history is Ethiopia under God.

    Reply
  2. Tadesse says

    September 6, 2016 11:15 am at 11:15 am

    Another thing is that we have no any relation with these brutals like Abay Weldu.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule