ሳውዲ አረቢያ ቢሻ እየተባለ የሚጠራ አነስተኛ ከተማ ውስጥ አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ በሳውዲያዊ አሰሪዋ ከተተኮሰባት ጥይት ከሞት መትረፏን ምንጮች አረጋገጡ። በዚህች ኢትዮጵያዊት ላይ ስለደረሰው የነፍስ ማጥፋት ጥቃት በኢህአዴግ ተመልምለው የተሰየሙት ዲፕሎማቶች ምንም ዓይነት መረጃ የላቸውም፡፡ አደጋው የደረሰባት ወጣት በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ መሆኗን የሚናገሩ የዜናው አቀባዮች ወጣቷ እንደተራራ የገዘፈውን ህይወት በመጋፈጥ ቤተስቦቿን ከችግር ለመታደግ በወቅቱ ከነበሩ የኤጀንሲ ደላላዎች ጋር ተዋውላ ሳውዲ አረቢያ ለስራ መምጣቷን ይናገራሉ። በተጠቀሰው ውል መስረት ወጣቷ አሰሪዋ የወር ደሞዝዋን በየወቅቱ እንዲከፍላት ለማስረዳት ብትሞክረም ከኢትዮጵያ ከመጣች ጀምሮ ላለፉት ሁለት አመት ያለደሞዝ ለመቆየት መገደዷን ለመረዳት ተችሏል። ሰሞኑን ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ … [Read more...] about በሳውዲ የኢትዮጵያዊቷ የደመወዝ ጥያቄ ሽጉጥ አስመዘዘ
News
ዜና
አቶ አንዳርጋቸው – 60ዓመት
ኢህአዴግ በ“አሸባሪነት” የከሰሳቸውና ከየመን ጠልፎ ወደ ኢትዮጵያ የወሰዳቸው የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ 60ኛ ዓመት የልደት በዓል ባለፈው ቅዳሜ በኦስሎ ኖርዌይ ተከብሯል፡፡ በሥፍራው የተገኘው ዳንኤል አለባቸው ለጎልጉል በኢሜይል በላከው መረጃና ፎቶ እንደገለጸው ዝግጅቱ የተደረገው እዚያው ኖርዌይ በሚገኝ “የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት” ነበር፡፡ በበዓሉ ወቅት የአቶ አንዳርጋቸውን ህይወት ታሪክና የትግል ዓመታት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ፎቶ (ስላይድ) የቀረበ ሲሆን ከኬክ መቁረሱ ሥነስርዓት በተጨማሪ ግጥምና የልደት መዝሙር ለበዓሉ ማድመቂያነት ቀርበው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ … [Read more...] about አቶ አንዳርጋቸው – 60ዓመት
“ልማት ስለሌለ ልጆቻችን ስደተኞች ሆነዋል”
የከምባታ ህዝብ ሆን ተብሎ መሰረተ ልማት እንዳይገነባለት በመደረጉና በተራድኦ ድርጅቶች የተሰሩት መሰረተ ልማቶች ስራ ላይ እንዳይወሉ በደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች እየተፈፀመበት የሚገኘውን በደል በመቃወም የካቲት 3/2007 ዓ.ም በዱራሜ ከተማ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉን የከምባታ ህዝቦች ኮንግረንስ ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በሰልፉ ወቅትም ነዋሪዎቹ መንግስት ለአካበቢው ምንም አይነት ትኩረት ባለመስጠቱ 10 ከተሞች ላይ መብራት በራሳቸው ገንዘብ ማስገባታቸውን፣ ትምህርት ቤቶችን ራሳቸው እንደሰሩ፣ ቴሌኮሚኒኬሽን የተዘረጋው በህዝቡ ወጭ መሆኑን፣ መንግስት ሰራሁት ያለው ውሃ ከሶስት ሳምንት በኋላ መበላሸቱ ሙስና እንደተበላበትና እንዳልተሰራ እንደሚያምኑ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ ሰልፈኞቹ "ልማት ስለሌለ ልጆቻችን ስደተኞች ሆነዋል፣ ስራ አጥተው … [Read more...] about “ልማት ስለሌለ ልጆቻችን ስደተኞች ሆነዋል”
ኢህአዴግ በጋራ ንቅናቄው መንበርከኩን አመነ!
* ኢንቨስተሮች “የደም ከፈን” ላለመግዛት ወሰኑ በኦሞ ሸለቆ ድሆችን ከመሬታቸው በማባረር የሚያመርተውን ጥጥ ወደ ውጭ ለመላክ ከስምምነት ደርሶ የነበረው ኢህአዴግ ባለፈው ሰሞን ያልጠበቀው ምላሽ ደርሶታል፡፡ ምላሹን ተከትሎ የጥጥ ግብይቱ የጨነገፈው በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) መሆኑን በገሃድ አመነ፡፡ በኢህአዴግ ስትራቴጂክ በሆኑ ቁልፍ አካሄዶች ላይ አስቀድሞ የመልስ ምት በመምታት ፈተናው ውስጥ የከተታቸው አኢጋን እና መሪው ኦባንግ ሜቶ መዋቅራቸው ሊገኝ አለመቻሉ ኢህዴግን እንዳስጨነቀው ተሰማ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በሰማሁት ተዝናንቻለሁ ብለዋል፡፡ በዛሬው ዕለት አቶ ኦባንግ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ አሜሪካ መከተል የሚገባትን አካሄድ በመዘርዘር ለፕሬዚዳንት ኦባማ ፖሊሲ ሊያስቀይር የሚችል ደብዳቤ ልከዋል፡፡ ኢህአዴግ ነዋሪዎችን እያፈናቀለ በቦታቸው ላይ ጥጥ … [Read more...] about ኢህአዴግ በጋራ ንቅናቄው መንበርከኩን አመነ!
አንድነትን “እናኝከዋለን፤ እንገድለዋለን” – ምርጫ ቦርድ
የዛሬ አስር ዓመት “የሕዝብ ሱናሚ” እያለ ሲምል ሲገዘት የነበረው ህወሃት ሱናሚው ወደ እርሱ እየጎረፈ ሲመጣ በረገገ፡፡ መፍትሔ በጠብመንጃ አፈሙዝና በብረት ብቻ እንደሆነ የሚያምነው ህወሃት በረሃ የለመደውን በትሩን አነሳ፤ ንጹሃንን ጨፈጨፈ፤ ደም አፈሰሰ፤ ኢትዮጵያን ወደ እስርቤትነት ቀየራት፡፡ ትዕዛዙን በቀጥታ የሰጡት “ባለራዕዩ” ለፍርድ ሳይቀርቡ “እንደጀመርን እንጨርሰዋለን” ያሉትን ሰፊውን ሕዝብ ሳይጨርሱት እንደ ክዳን ቆርኪ ተስፈነጠሩት፤ ላይመለሱ ሄዱ፡፡ የዛሬ አስር ዓመት የቅንጅት አካሄድ ያስፈራው ህወሃት ጉዳዩን ለራሱ ለፓርቲውና ለሕዝብ ከመስጠት ይልቅ ደም መቃባት ውስጥ ገባ፡፡ ፓርቲው የነበረበት የውስጥ ችግር እንዳለ ሆኖ የፈሪ በትር የዘረጋው ህወሃት የገደለውን ገድሎ ከጨረሰ እና የኢትዮጵያን መሬት በደምና በእናቶች እምባ እንደገና ካጨቀየ በኋላ ቅንጅትን የማፍረስ … [Read more...] about አንድነትን “እናኝከዋለን፤ እንገድለዋለን” – ምርጫ ቦርድ
አንድነት በደጋፊዎቹ ላይ “አረመኔያዊ” ያለው ድብደባ መፈፀሙን ተናገረ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አዲስ አበባ ላይ ሕጋዊ በሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ሊሣተፉ በወጡ አባሎቼና ደጋፊዎቼ ላይ በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ ሲል ከስሷል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አዲስ አበባ ላይ ሕጋዊ በሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ሊሣተፉ በወጡ አባሎቼና ደጋፊዎቼ ላይ በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ ሲል ከስሷል፡፡ ፓርቲው በሌሎች ከተሞች የጠራቸው ሰላማዊ ሰልፎች ንግ በስኬት መጠናቀቃቸውን ገልጿል፡፡ ከፖሊስ ምላሽ አለማግኘቱን አዲስ አበባ ላይ የተጠናቀረው የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ይናገራል፡፡ ለዝርዝሩ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ያቀናበረውን የድምፅ ፋይል እዚህ ላይ ያዳምጡ፡፡ የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ያጠናቀረውን ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ በሌላ በኩል አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ … [Read more...] about አንድነት በደጋፊዎቹ ላይ “አረመኔያዊ” ያለው ድብደባ መፈፀሙን ተናገረ
Xenophobic attacks escalate as feeling of hatred sweeps South Africa
“In Russia, bread riots led to a revolution, here (in South Africa) they lead to xenophobia.” Nomalanga Mikize, on Twitter A nation in cantankerous mood and truculent society baying for blood. The air is thick with terror and despair of foreign nationals living and working in one of the world’s racially intolerant nations, South Africa. Collectively known as Makwerekwere-a derogatory term for black African immigrants and Onomatopoeia-for other non-nationals who speak unintelligibly, life in … [Read more...] about Xenophobic attacks escalate as feeling of hatred sweeps South Africa
በኔፓል ፓርላማ “አንቀጽ 39 በእልልታ” አይጸድቅም!
የመናገር፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ ወዘተ መብቶች በሚከበሩባቸው አገራት በመጀመሪያ ደረጃ ፓርላማ የሚባል አካል ካላቸው ገዢው ፓርቲ የ99.6 በመቶ ወንበር አይዝም፤ በፓርላማው የተቀናቃኝ ፓርቲ አባልም አንድ ብቻ አይሆንም፡፡ ይህ ከሆነ ስብስቡ “ፓርላማ” ሳይሆን “የ… ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ” ነው የሚባለው፡፡ ከዚህ ሲያልፍ ረቂቅ ሕግጋትና ውሳኔዎች ሁሉ “በአክላሜሽን” ወይም በሙሉ ድምጽ ወይም “በእልልታ” አይደለም የሚጸድቁት፡፡ የተቀናቃኝ ፓርቲ አባላትም የአገርን ጉዳይ በተመለከተ “የሶስት ደቂቃ” የንግግር ገደብ አይጣልባቸውም፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በኔፓል ፓርላማ የደረሰው “የተከበሩ” የፓርላማ አባላት እንዲህም ያደርጋሉ እንዴ በማለት የሚያስጠይቅ ነው፡፡ ማክሰኞ ምሽት የአገሪቱን የተሻሻለ አዲስ የሕገመንግሥት ረቂቅ ለማጽደቅ የተሰበሰቡት የፓርላማ አባላት በጉዳዩ ላይ … [Read more...] about በኔፓል ፓርላማ “አንቀጽ 39 በእልልታ” አይጸድቅም!
የመኢአድ ም/ፕሬዝደንት የፖሊስ ልብስ በለበሱ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባቸው
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የፓርቲያቸው ምክትል ፕሬዝደንት እና የሰሜን ቀጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት እጅግ ዘግናኝ ድብደባ ደርሶባቸው ሲል ፓርቲው ጥር 15/2007 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ አስታወቀ፡፡ አቶ ዘመነ የመኢአድን ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ወደ መኖሪያቸው ጎንደር ከተማ ከተመለሱ በኋላ ከፍተኛ የደህንነት ክትትልና ጫና ይደረግባቸው እንደነበር ለፓርቲያቸው አሳውቀው ነበር ያለው ፓርቲው በ10/05/2007 ዓ.ም ጎንደር ከሚገኘው መኖሪያው ቤታቸው ከባቤታቸውና ከህጻን ልጃቸው ፊት የፖሊስ ልብስ በለበሱ አካላት ከፍተኛ ደብደባ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ግልጾአል፡፡ በአሁኑ ወቅት የፓርቲው አባላት ባደረጉት ክትትል አቶ ዘመነ አዘዞ የሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ውስጥ እንደሚኙ አረጋግጠናል ያለው መግለጫው የሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል ተብሎ የማይገመት … [Read more...] about የመኢአድ ም/ፕሬዝደንት የፖሊስ ልብስ በለበሱ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባቸው
“ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም”
የሰብዓዊ መብት ተመልካች የሆነው ድርጅት (ሂዩማን ራይትስ ዎች) “ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም” በሚል ርዕስ ያወጣል ተብሎ የተጠበቀውን ዘገባ ማምሻው ላይ ይፋ አድርጓል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ያለ ነጻ ሚዲያ – ምርጫ ወይስ ቁማር?” በሚል ርዕስ ባተመው ዜና ላይ ዘገባው እንደሚወጣ በተናገረው መሠረት ባለ 76 ገጽ ሪፖርቱ በሚዲያ አፈና ዙሪያ ዝርዝርና ወቅታዊ መረጃዎችን አውጥቷል፡፡ ኢህአዴግ በሚያደርስባቸው ስልታዊ አፈና፣ ማስፈራሪያ፣ ህይወት የማጥፋት ዛቻ፣ … ምክንያት በአሁኑ ጊዜ በትንሹ 22 የሚሆኑ ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙ፤ ከ30 በላይ የሚሆኑ ደግሞ አገር ጥለው መኮብለላቸውን በዘገባው ተጠቁሟል፡፡ እንዲህ ያለው ገለልተኛ ሚዲያን የሚያፍን እና ከሜዳው የሚያስወጣ አሠራር ከወራት በኋላ ይካሄዳል ከሚባለው “ምርጫ” አኳያ የውድድሩን ሜዳ … [Read more...] about “ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም”










